>
5:14 pm - Wednesday May 1, 9585

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ አርፍደው የደረሱበት እውነት!!! (ሀብታሙ አያሌው)

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ አርፍደው የደረሱበት እውነት!!!

ሀብታሙ አያሌው

ማንም ከማንም ጋር የሰውነት ጥል ሊኖረው አይችልም  የዕውቀት ጥል እንጂ። ቋንቋ የሚባልን ነገር ከመካከላችን አውጥተን ማሰብ ብንጀምር ዘረኝነት ሃሳብ ላይ እንጂ ደም ላይ እንደሌለ እንረዳለን።
  ሁላችንም ዘር አለን።ዘሩ ግን እኛ አይደለንም! እኛ ሰዎች ነን። ሰውነት ከመፈጠር እንጂ ከመወለድ አይጀምርምና ፈጣሪ ዘራችንን ኢትዮጵያ በምትባል ምድር ላይ ዘራው። ሲዘራው ኢትዮጵያ ማለት ሰዎች መሆኗን አወቅን። መነጣጠል እስከማንችል ተዋሃድን። ትላንት የሆነ የሰው ዲስኩር አንዳችን ካንዳችን ካልለየሁ እያለ ሥያሜ አበጀልን።ፈጣሪን ለማረም ይመስል እኛም ሆሆሆ ብለን ተቀበልን።
በህንድ 2032 ብሄረሰብ በሠላም እየኖረ በቻይና 499 ብሄረሰብ በሰላም እየኖረ ምነው እኛ(ሰማኒዊያን) መሸከም አቃተን ? ተራ በተራ መግዛታችንን ለበላይነት ተጠቀምንበት??
ማንም ከማንም ጋር የሰውነት ጥል ሊኖረው አይችልም የዕውቀት ጥል እንጂ ።ገና ስንወለድ ዘር ምን ይሁን ቋንቋ ምን ይሁን የምናውቀው ነገር አልነበረም። የዕውቀት ጥል ደግሞ በጠረጴዛ ዙሪያ እንጂ በጦር ሜዳ አይፈታም። ምክንያቱም ይቅርታ እንጂ በቀል ታሪክን አያርምምና።
ቋንቋ የሚባለው ነገር ከመካከላችን አውጥተን ማሰብ ብንጀምር ዘረኝነት ሃሳብ ላይ እንጂ ደም ላይ እንደሌለ እንረዳለን። እየጨፈርን የናድነውን ቤት እያለቀስን አንሰራውም። ሁልጊዜ ጥፋት ካደረስን በኋላ እንዳጠፋን ምንረዳ ከሆነ ዞሮ መልሶ አለማወቅ ይሆንብናል። በመቻቻል ሳይሆን በፍቅር እንኑር መቻቻል አንድ ቀን ያሰለቸናል። ታገስኩህን ቻልኩህን ያመጣል። ፍቅር ግን እስከፂሜጋ ይሸከማል።
ከሰውነት በላይ ምን ማንነት ኖሮ የሁላችንም መገኛ ያው አዳም ነው ዞሮ የማሻር ሽረን አይሆኑሽ ሆነናል የማይድን ስናክም የማይሞት ገለናል።
ኢትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው። ኢትዮጵያ ለሁላችንም በቂ ናት!!! እንዋደድ በፍቅር እንኑር !!!!
Filed in: Amharic