>
5:13 pm - Wednesday April 19, 0575

ጃዋር  በአዲሱ “ዓለም” ሆኖ ከፍርድ ሒደት ይልቅ ሽምግልናን ጠየቀ!!! (ጎልጉል)

ጃዋር  በአዲሱ “ዓለም” ሆኖ ከፍርድ ሒደት ይልቅ ሽምግልናን ጠየቀ!!!

ጎልጉል

ሐሙስ ዕለት በተለያዩ ወንጀሎች ተከስሶ ፍርድ ቤት የቀረበው ጃዋር የባህላዊ ሽምግልና እና ዕርቅ ከመደበኛው ፍርድ ቤት በፊት እንዲሞከር ጥያቄ አቀረበ። እጅግ መረን ከለቀቀና ከተደንደላቀቀ የቅምጥል ኑሮው ወጥቶ ወደ አዲስ “ዓለም” የገባው ጃዋር መሐመድ ያቀረበውን ጥያቄና ተማጽንዖ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ አድርጎ ክሱ እንዲቀጥል ቀጠሮ ሰጥቶ አሰናብቶታል።
ጃዋር በሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የሚያስጠረጥረውን በርካታ መረጃዎች ተከትሎ፤ በኔትወርክ ሊያደርግ ያሰበው የመንግሥት ለውጥ በመክሸፉ፤ በተለይም በአስከሬን ባለቤትነት የተፈጠረው ግብግብ ከፍተኛ ተቃውሞ ስላስነሳበት የሽምግልና አካሄድ እንደሚያዋጣው በመረዳት ጥያቄውን ሐሙስ ለዋለው ችሎት ማቅረቡን በቅርብ ሂደቱን የሚከታተሉ ለጎልጉል ተናግረዋል።
ጎልጉል ቀደም ሲል የሽምግልና ሃሳብ እንዳይጨናገፍ በማለት ያላተመውን ዜና ማስታወሱ አግባብ በመሆኑ ከዚሁ ርዕሰ ዜና ጋር አያይዘን ለመጠቆም እንወዳለን። ከሦስት ወር በፊት ጃዋር መሐመድ ከአቶ ድንቁ ደያስ ጋር በመምከር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር የዕርቅ ስምምነት ለማድረግ በአርሲ ተወላጅ ከፍተኛ ሽማግሌዎች አማካኝነት ዕርቅ ጠይቆ ነበር። ዶ/ር ዐቢይ በወቅቱ ሽማግሌዎቹን እንደሚያከብሩ፣ ለሽማግሌዎቹ ተነሳሽነት ልዩ ከበሬታ እንዳላቸው በመግለጽ በቤተመንግሥት አስፈላጊውን መስተንግዶ በማከናወን ጃዋር መሐመድና ተከታዮቹ በአገሪቱ ላይ እያደረጉ ያሉትን ጉዳዮች በሙሉ ለሽማግሌዎቹ በማስረዳት “ጃዋር ያላደረገው ነገር፤ ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም፤ ከዚህ በኋላ የሚቀረው የሕግ ጉዳይ” ነው፤ ከሰማይ በታች ማድረግ የሚችለውን ሁሉ አድርጓል በማለት ሽምግልና የመጡትን ሰዎች እውነትን አስጨብጠው ልከዋቸው ነበር።
ከህወሓት እና ህወሓት ከሚመራቸው ሚዲያዎች ጋር በመናበብ ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲካሂዱ የነበሩት የጃዋር መዋቅሮች በተደጋጋሚ በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት ለማስወገድ ዝግጅት እንዳላቸው ሲያስታውቁ ከርመዋል። ሰላማዊ ትግልን፤ የሚዲያ ነጻነትን፤ የመብት ትግልን፤ ማኅበራዊ ሚዲያን፤ የሃይማኖት አመራሮችን፤ ጥቅም የቀረባቸውን ነጋዴዎች፤ እንዲሁም በኢትዮጵያ ላይ ሥውር አጀንዳ ከሚራምዱ የውጭ አካላት ጋር በተወጠነ ሤራ መንግሥትን አሽመድምዶ ለመጣል ሲደረግ የነበረው ዘመቻ የመጨረሻው ነጥብ ላይ መድረሱን ከነጌታቸው ረዳ ጋር ባደረጉት ግምገማ ማረጋገጣቸውን ጎልጉል መረጃ ደርሶታል።
ይህንን ግምገማ ተከትሎ የማዕከላዊ መንግሥቱ ጠልሽቷል፤ ከሕዝብ ተነጥሏል፤ በከሃዲነትና አገር ሻጭነት ተመድቧል፤ በመጨረሻም ምርጫ አላካሂድም ብሏል በውጭም ከፍተኛ ጫና እየደረሰበት ነው ስለዚህ ጊዜው አሁን ነው በሚል በተሠራ የሤራ ፖለቲካ የሒሳብ ቀመር አዲስ አበባ ላይ ትርምስ ለመፍጠር ዕቅድ መነደፉን መንግሥት አስቀድሞ እንደሚውቅ ሰሞኑን አስታውቆ ነበር።
የአርቲስት ሃጫሉን ግድያ ተከትሎ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ፤ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነርና ምክትላቸው፤ የኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር እንዲሁም የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ፤ ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ራሳቸው እና አማካሪያቸው ሌንጮ ባቲ የመሳሰሉት አካላት እንዳረጋገጡት በአዲስ አበባ “ሊያጠፉህ መጥተዋል ራስህን ተከላከል” በሚል የአብያተክርስቲያናትን ደወል በማስደወል ከተማዋን በደም ለማጠብ የተደረወገው ሙከራ ከሽፏል።
ይህ ከሸፈ የተባለው ዕቅድ ከመንግሥት ወገን ብቻ በመነገሩ ሣይሆን እንደ ጸጋዬ አራርሣ ዓይነቱ ጽንፈኛ አሸባሪ የኦሮሞ ሕዝብ በአራቱም አቅጣጫ ተምሞ አዲሳስ አበባ እንዲገባ መናገሩ፤ እንደ ዳዊት ከበደ ዓይነቱ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ባለቤት የዓባይን አጀንዳ የሚስቀይር አጀንዳ ይከሰታል ማለቱ፤ የዲጂታል ወያኔዎች ቴዲ አፍሮን መቀሌ ተሸሸግ ማለታቸውን እንደ ዘጸዓት ዓይነት  (ትክክለኛ ስሙ ጎይቶም አርጋዊ በፌስቡክ ስሙ Ztseat Saveadna Ananya የሚባለው) የወያኔ አንደበቶች የዓመጽ ጥሪ ማሰማታቸው ከሁሉም በላይ ግን የሃጫሉ አስከሬን ላይ የተደረገው ኢሰብዓዊና ታሪክ የማይረሣው ሽፍጥ የመንግሥት ባለሥልጣናቱ የተናገሩትን በእውነተኝነት የሚያረጋግጥ አድርጎታል።
የሃጫሉ ሞቱ ሳይሆን አስከሬኑን ለመውረስ የተደረገው ግብግብ ዋና ምክንያት በቀብር ሰበብ አዲስ አበባ ተምሞ የሚገባውና ከያቅጣጫው የሚመጣውን ሕዝብ አስቀድሞ ወያኔ ካስገባቸው እና አዲስ አበባ ካሉ የወያኔ መዋቅሮች ጋር በማስተባበር በከተማዋ ነውጥ አስነስቶ ቤተመንግሥቱንና ቁልፍ የመንግሥት ቦታዎችን መቆጣጠር እና የኦሮሚያ ባለሥልጣናትን መግደል ነበር ዕቅዱ። አስከሬን አስታኮ ታይቶ የማይታወቅ ግብግብ ውስጥ ለመግባት የታሰበውም ለሃጫሉ ታስቦ ሳይሆን የሤራው ቀዳሚ ዕቅድ በመሆኑ ነበር።
ሰላማዊ ታጋይ ነኝ ባዩ በቀለ ገርባ ቤተሰቡን ጭኖ፣ ጃዋር ጠባቂዎቹ ከያዙት መሣሪያ በተጨማሪ በተሸከርካሪ ውስጥ ክላሽና ሽጉጥ ተሸክሞ የአስከሬን ባለቤትነት ጥያቄ ለማንሳት ቡራዩ ሲሄድ የተፈጠረውን አሣፋሪ አለመረጋጋት ፖሊስ በትዕግስት ለማብረድ ሲሞክር የጃዋር ደጋፊዎች በጭፍን ሁከቱን ሲያፋፍሙት ነበር።
ሐሙስ ዕለት ለቪኦኤ መግለጫ የሰጠው የሃጫሉ ወንድም ሃብታሙ ሁንዴሣ ይህንኑ የአስከሬን ቅርምት ተከትሎ ሲናገር “ያሳፍራል፤ ያሳዝናል፤ (ሃጫሉ) ባለትዳር ነው፤ ሚስቱ አምቦ እንዲቀበር ትፈልጋለች፤ ቤተሰብ አለው – ቤተሰቡ አምቦ እንዲቀበር ይፈልጋሉ፤ ወንድሞ አሉት – ወንድሞቹ አምቦ እንዲቀበር እንፈልጋለን፤ ሃጫሉ በሕይወት እያለ ስሞት ዕትብቴ በተቀበረበት አምቦ ቅበሩኝ ብሏል፤ ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ አስከሬኑ ላይ የሚደረገው ግብግብ ለምን እንደሆነ አይገባንም፤ ከሞቱ ይልቅ ያዋረዱት እዚህ ላይ ነው” ብሏል። ከወንድሙ ሞት በላይ አስከሬኑ ላይ ተደረገው ቅርምት እንዳሳፈረውም ተናግሯል። ለቅሶ እንኳን እንዳንቀመጥ አድርገውናል፤ ሰዉ ለምንድነው ይህንን የማይረዳው፤ ለምን ስሜታዊ ይሆናል ሲልም ጠይቋል።
ይህንን ሁሉ የሚከታተለው ጃዋር ሲራጅ መሐመድ ከተያዘበት መረጃ፤ ከገባበት ወጥመድ፤ ከዚህ በፊት ከሠራቸውና ካቀነባበራቸው ከፍተኛ የግድያ ወንጀሎች በአጠቃላይ በሕግ ፊት መቅረቡ እንደማይቀር በማረጋገጡ ሽምግልና ይሻላል ሲል ፍርድ ቤቱን ሊመክር ሞክሯል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ወኪል በላከው መረጃ ጃዋር በሽምግልና ጉዳዩ እንዲያልቅ በፍርድቤት ብቻ ሳይሆን ባልታሰሩት የመዋቅሩ አካላት አማካኝነት እየተወተ ይገኛል። የአገር ሽማግሌዎችንም ለመጠቀም እያስወተወተ ነው። እሱ ይህንን እያደረገ ባለበት ሁኔታ ከመንግሥት የተለያዩ ዕርከን ባለሥልጣናት የሚሰማው ግን የጃዋርና የጃዋር መዋቅር አካላት በህግ ብቻ የሚዳኙ መሆናቸውን የሚገልጽ ሆኗል።
ጃዋር በተደጋጋሚ በማዕከላዊ ኦሮሚያ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ለዚሁ ዓላማ ሲል ኦፌኮን መቀላቀሉን ጎልጉል ዘግቦ ነበር። በሌላ ዘገባ “የመረራን ፓርቲ የተቀላቀልኩት የሸዋን ድምጽ ለማግኘት ነው” ብሎ መናገሩን ጎልጉል ጠቅሶ ዘግቦ ነበር። በዚህ መስመር የሚችለውን አድርጎ ያልተሳካለት ጃዋር ጠቅላይ ሚኒስትሩን ዲቃላ በማለት በተስፋ መቁረጥ ወደ ዲቃላ ፖለቲካ ሲገባ ድምጹን ከነፈገው የኦሮሞ ህዝብ ጋር ያለው መካረር የመጨረሻ መጀመሪያ ተደርጎ ነበር የታየው። ጃዋር በጣም ተስፋ ካደረገባቸው ቦታዎች አንዱ በሆነው ጅማም ተመሳሳይ የኦፌኮ ቅስቀሳ ለማድረግና የሕዝቡን ይሁንታ ለማግኘት የሞከረ ቢሆንም በኦፌኮ ስም የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ ወደ ከተማችን እንዳይመጣ፤ “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” በማለት የአገር ሽማግሌዎች ከወጣቱ ጋር በመሆን መግለጫ አውጥተው መድረሻ ቢስ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው። የእነዚህ ሁሉ ድምር ክስረቶች ጃዋርን ወደመጨረሻውና ከኦሮሞ ሕዝብ ጋር በተለይም ከማዕከላዊው ኦሮሚያ ሕዝብ ጋር መቼም እንደማይገናኝ ሆኖ ያፋታውን ተግባር ወደመፈጸም የነዳው የሚሉ አስተያየቶች ይሰማሉ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የጃዋር የከፍተኛ የገንዘብ ምንጭና አዘዋዋሪ የሆነው ድንቁ ደያስ በክፍያ ያሰማራቸው ታጣቂዎች ተለቅመው መታሰራቸውን ጎልጉል ሰምቷል። የጎልጉል የመረጃ አቀባዮች እንዳሉት ከሆነ መንግሥት ባመረረ ማግስት አብዛኛዎቹን በቁጥጥር ለማዋል የቻለው እንቅስቃሴው አስቀድሞ የታወቀና ክትትል ይደረግበት ስለነበረ ነው ብለዋል። እነጃዋር መንግሥት ሲሆኑ የድንቁን የግብር ዕዳ የሚሰርዙ ብቻ ሳይሆኑ በተለይ ሚድሮክ ወርቅን በሽያጭ እንደሚያስተላልፉለትና ከሽያጩ ተካፋዮች እንደሚሆኑ ከብዙዎቹ ቀቢጸ ተስፋዎች አንዱ ሆኖ ይጠቀሳል።
በከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ሌብነትና ዕዳ የሚፈለገው፣ ከአገር የኮበለለውና ራሱን “እኔ መንግሥት ነኝ” በማለት የሰየመው ድንቁ ደያስ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ፍርዱን እንዲቀበል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሁለት አባላት ያሉት የመርማሪ ቡድን ወደ አሜሪካ መላኩ ታውቋል። ሁለቱ ሰዎች ወደ አሜሪካ የሄዱት ከጽሁፍ መረጃ ልውውጥና ከአስፈላጊ አካላት ጋር ንግግር ከተደረገ በኋላ መሆኑ ለመረዳት ተችሏል። ከሶዶሬ ሪዞርት ጋር በተያያዘ ከ157 ሚሊዮን ብር በላይ የሊዝና የመሬት ክፍያ የሚፈለገው ድንቁ ደያስ መያዝ ለነጃዋር የፍርድ ሂደት ትልቅ እማኝ ምስክር ሆኖ እንደሚቀርብ ይጠበቃል።
Filed in: Amharic