አቶ አብዲሣ ዛሬ የሃጫሉ ቀብር ሥነስርአት አምቦ እየተካሄደ ባለበት ወቅት በOBN ያደረገው ንግግር
አቤል ብርሀኑ
* ሃጫሉ “አንድ ቀን ይገድሉኛል እንዳለ አለፈ”
* ሃጫሉን አንዴ ሳይሆን ሶስት ጊዜ ነው የገደሉት
ሃጫሉን አንድ ግዜ ብቻ አይደለም የገደሉት አስከሬኑ ወደቤተሰቦቹ እየተሸኘ ሳለ መሣሪያ የታጠቁ አስከሬኑን ነጥቀው ወደ አዲስ አበባ መለሱት ፣ ህዝብ በተኩስ ለውጥ እንዳይጎዳ ብለን ዝም አልናቸው ፣ ይህም አንሶ የብልፅግና ፅ/ቤት ድረስ ዘልቀው ሥራ ላይ የነበረውን ሰው በመግደል ግጭት ለመቀስቀስ ሞከሩ፣ ያንንም በትዕግሥት አለፍነው ፣ በትናንትናው እለት ደግሞ ኦነግ ሸኔና የወያኔ ታጣቂዎች በቅንጅት ወላጆቹ ቤት ድረስ ዘምተው አጎቱን በጭካኔ ገደሉት፣ ይህ ለሃጫሉ 3ኛ ሞት ነው ።
ለሃጫሉ ግድያ ተጠየቂዎቹ ኦነግ ሸኔ ወያኔና በህዝብ ትግል ገብተው እዚህ አዲስ አበባ ቁጭ ብለው ህዝብ የሚያምሱ ናቸው ፣ ሃጫሉን ለእርድ ያዘጋጁት የግዲያው ተባባሪዎች ከሳምንት በፊት ሚዲያቸው ላይ አቅርበውት ምን እንደጠየቁት ማንም ሰው የሚያውቀው ነው፣ ያ ቃለመጠይቅ የተዘጋጀው ለሴራቸው ስኬት ህዝብን ከህዝብ ለማባላት በማሰብ እንደነበር ግልጽ ሆኖአል። ከጥያቄያቸው አንዱ ትግራይ ሂዶ ከወያኔ ጋር መነጋገር እንዴት ወንጀል ነው ትላለህ ? ድሮ ድሮ ኦሮሞ ኦሮሞ ትል ነበር አሁን ቋንቋህን ቀይረሃልም ነበር ያሉት ።
ሃጫሉ እነርሱ የግል ህይወታቸውን ሲያደላድሉ ከጠላት ጋር ግንባሩን ሰጥቶ ስተናነቅ የኖረና ጨቋኝ ሥርአት ለማንኮታኮት መስዋእት የከፈለ ጀግና ነው ፣ በነፃነት ወደ አገራቸው ሲመለሱ አክብረን የተቀበልናቸው ግን ለህልፈቱ ተባባሪ ሆኑ ።
ከአሁን ቦሃላ ትዕግሥታችን ተሟጦአል። ያሳየነው ትእግሥትና ፍቅር ከፍርሃት የመነጨ አይደለም። ወያኔ፣ ኦነግ ሸኔና አዲስ አበባ ሆኖ ውጥረት የሚያመርተው ቡድንና ከግብፅ ጋር ተባብረው አገራችንን እንዲያተራምሱ የሚፈልጉ ሃይሎች አላማቸው አይሳካላቸውም ፣ ክልላችን ሰላም እየነሱ ያሉ እነዚህን ሃይሎች የገቡበት ገብተን ከክልላችንን እናጠራቸዋለን።
ከበሰበሰው ሥልጣን ጠራርገን ያባረርነው ወንጀለኞች እርስ በርስ አባልተውን ዳግም ወደሥልጣን ሊመለስ አይችልም ። ኦሮሞ ግንድ ነው፣ አባት ነው ፣ታላቅ ነው በኖረው ባህልህ ከሁሉም ህዝብ ጋር በፍቅር መኖርህን ቀጥልበት። እርስ በርስ በመባላት ለጠላቶቻችን ሴራ እንዳንመች አደራ እላለሁ ……”