>

አርቲስቱን የገደሉት ... (ጉዱ ካሳ)

አርቲስቱን የገደሉት …

 

ጉዱ ካሳ

• የዓቢይን መንግሥት ለመጣል ኦሮሚያን ለሁለት የሚሰነጥቅ ሃሳብ ታሰበ ። እሱም አርቲስት ሃጫሉ በሁሉም የኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ስላለው ፣ እሱ ቢወገድ በኦሮሚያ ምድር ከፍተኛ ተቃውሞ እንደሚነሳና ከበፊቱ የበለጠ ድጋፍ እንደሚያገኙ ታመነበት።
•  የታሰበው ሃሳቡ የበለጠ ፍሬ እንዲያፈራ ፣ ይህ የረቀቀ ፖለቲካዊ ጨዋታ፣ ኦሮሞን ከአማራ ህዝብ ጋር የሚለያይ መሆን ስላመኑበት ፣ ምስኪኑ አርቲስት ነገሩ ሳይገባው በ-OMN በኩል ፕሮግራም ተዘጋጅቶለት አማራን እንዲሳደብ ተደረገ ።
•  ይህ ወጣት የተሰጠውን አጀንዳ አስተላልፎና ተሳድቦ ሳምንት ሳይሞላው ነገሩ እንደተቀጣጠለ በፍጥነት እንዲገደል ተደረገ ።
• እንዳሰቡት ጉዳዩ በሙሉ ባይሳካም ፣ ከህወሓት ጋር በመሆን የጀመሩትን ግብ ለማድረስ ፣ ህዝቡን እየቀሰቀሱ እና ነፍጠኛ ገደለው ማስባል ጀምረዋል ።
•  ከዚህ ተንኮል ጀርባ ያሉት #ግብጽ እና #ህወሃት ፣  #ኦነግ_ሸኔ እና የኦፌኮ ጥቂት አመራሮች ከ-OMN ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር በጥምረት ተሳትፈውበታል ።
• የወጣቱ መሞት በተግባር እንደተፈፀመ :-
➡ ጃዋር በፌስቡክ ገፁ ላይ እኔ የአንተን ሞት ሺ ጊዜ
      ልሙት አለ ።
➡ በቀለ ገርባ ስለ ምኒልክ በመናገሩ ተገደለ ስለዚህ
      የምኒልክን ሃውልት አፍርሱ ብሎ ጥሪ አስተላልፏል።
➡ ፀጋየ አራርሳ ነፍጠኛ ገደለው። የምኒልክን ሃውልት
     አፍርሱ ሲል እሱም በተመሳሳይ ጥሪውን አቅርቧል።
➡ OMN ቴሌቪዥን ጣቢያ በበኩሉ #የገደለህን_ግደል
     የሚል መልእክት ለወጣቶች አስተላለፈ።ይኸው ብዙ ሰዎች እየተገደሉ ነው።
 ለማጠቃለል⤵
የሚኒሊክን ሃውልት ለማፍረስና የአዲስ አበባን ውርስ ለማስፈፀም አክራሪ ኦሮሞች ብዙ ጥረዋል ። እንደ ቴዲ አፍሮ ያለውን ሰው ለመብላት ብዙ ሞክረዋል። ሞክረው ፣ መክረው ያገኙት ብቸኛ መንገድ የራሳቸው የሆነውን ሰው በመብላትና ህዝቡን ለአመፅ ማነሳሳት ነው። ሃጫሉ በቅርቡ ስለ አፄ ሚኒልክ አስተያየት መስጠትና የህዝቡን ቁጣ መነሳት ተከትሎ ፣ በነ ጃዋር ፖለቲካዊ ስሌት ሃጫሉን ገድሎ ያጡትን ተሰሚነት ዳግም ለማስመለስ ፣ በእነ ዓቢይ እየተዋጠ የመጣውን የቄሮ ትግል እንዲንሰራራ ስላመኑበት ገደሉት ።
በማንም ሰው ሞት አንደሰትም። ሃጫሉ ነፍጠኛን ግደል ብሎ ሲዘፍን የነበረ ልጅ ቢሆንም ሰው ሞሁኑንና ሞትም ለሱ የማይቀር መሆኑን አይተናል ። አዝነናል ። ተናደናል ። ቂም ይዘናል ። ነገር ግን እንደሰው ይቅር ብለናል።
ይች አገር አደጋ ውስጥ ነች ። ወደማያባራ እልቅት የሚወስዱን በስልጣን ግብግብ ውስጥ የገቡት የራሳቸው ልጆች ናቸው ። ችግሩ የውስጥ ነው ። ከዚህ ሁሉ ጀርባ ግን ህወሓት ፤ ግብፅ እና ኦነግ  ስለመኖራቸው  አንዳች ጥርጥር የለኝም ።
 ነፍስ ይማር❗
Filed in: Amharic