>

ከአቶ ጃዋር መሐመድ ጋራ 35 ሰዎች ታሰሩ (ቪኦኤ)

  • ከአቶ ጃዋር መሐመድ ጋራ 35 ሰዎች ታሰሩ

ቪኦኤ


አቶ ጃዋር መሐመድ እና ሌሎች ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ እና የኦሮሚያ ፖሊስ በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ።

አቶ ጃዋር መሐመድ እና ሌሎች ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ እና የኦሮሚያ ፖሊስ በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ። ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሰጡትን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል እንደሻው ጣሰውን እና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንን ቃል ጠቅሰው ማብራሪያ የሰጡን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ጀላን አብዲ፤ በዛሬው ዕለት የ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን አስክሬን በማጓጓዝ ሂደት ውስጥ አንድ ፖሊስ መገደሉን ጠቅሰው፤ ይህ ፖሊስ የተገደለው ከአቶ ጃዋር መሐመድ ጋር በነበረ ሰው አማካኝነት ነው ብለዋል። ከእዚህና ሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ አምስት አቶ ጃዋር እና አምስት ጠባቂዎቻቸውን ጨምሮ ሌሎች ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አቶ ጀላን ተናግረዋል። (ዝርዝሩን ጥቂት ቆይቶ እናቀርባለን)

Filed in: Amharic