>
5:13 pm - Wednesday April 19, 3617

የዲሞግራፊ ቅየራ ፉከራ  በኮንደሚኒየም እና መሬት ቅርምት ብቻ ይቆም ይሆን?!?  (ህብር ራድዮ)

የዲሞግራፊ ቅየራ ፉከራ  በኮንደሚኒየም እና መሬት ቅርምት ብቻ ይቆም ይሆን?!? 

ህብር ራድዮ 

የአዲስ አበባ ሕዝብ ስልጣን የለውም። የአዲስ አበባ ሕዝብ መስተዳድር ምክር ቤት የሚባለው ላይስሙላ ነው። ስለዚህ የከተማው አስተዳደር በጠቅላይ ሚኒስትሩ መዳፍ ስር ነው። የአንድ ፓርቲ ንብረት። ይሄ ትላንት ከትግራይ የመጡ መሪዎች እና ደጋፊዎቻቸው እንደ ልብ ሲፈነጩበት የነበረን ከተማ እነ አብይ በተረኝነት በፍጥነት ቀጥለውታል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፈለገ የከተማ አስተዳደሩን የመበተን ስልጣን አለው። አዲስ አበባ ቤቴ የሚለው ለዘፈን ካልሆነ ትላንት ከትግራይ ለመጡ ሽፍቶች መጫወቻ የሆነው ከተማ ዛሬ ከኦሮሚያ ለመጡ ባለጊዜዎች በር እንደሌለው ቤት እንደ ልብ እየተዘረፈ ነው። አቤት ቢባል ማን ይሰማል?
በለውጡ ማግስት እንዴት ነው ሥልጣናችን የሚቀጥለው ብለው ቤተ መንግስት የኦሮሞ ፖለቲከኞች በድብቅ መክረው ነበር።ሰብሳቢዎቹ ለማ እና አብይ ነበሩ።  የዲሞግራፊ ቅየራ እናዳርጋለን የተባለበት የለማ መገርሳ ፉከራ አንዱም መሬት ጠብ አላለም። ለአብይ እየዘፈንክ አዲስ አበባ ቤቴ ስትል ከከተማዋ ሊነቅልህ ሌት ከቀን እየሰራልህ ነው። አቦ ይመቸው የእሱን ፎቶ ስትቀባበል ኣንዱ ውርጋጥ ጊዜው ሰጥቶት የተናገረውን ይዘህ ስትራቃቅ ውስጥ  ውስጡን የሚሰራው ያውቃል ። አብይን ዋናውን አስቀምጠህ ታዛዡን  ታከለ ኡማን ስታወግዝ አብረው ይስቁብሃል። ታኬን ለቀቅ አለቃውን ጠበቅ አድርገው። አብይ ሳያውቅ ይሄ ሁሉ እየተሰራ ነው የምትል የዋህ እዚያው ተነጠፍ። ጊዜው ከተለጣፊ ወደ ተነጣፊ ሆኗል።
ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉትን  በአስቸኳይ እንደ ጥሩ አጋጣሚ ወስደን  ቶሎ እናስፍራቸው ነገ የአዲስ አበባን ዲሞግራፊ ይቀይራል ያሉት አቶ ለማ መገርሳ ያቦኩትን ሴራ ተናገሩት እንጂ የተባለው አንድ በአንድ እየተፈጸመ ነው። ምን ቀረ?
 ከምርጫ 97 ዋዜማ ጀምሮ ለኮንደሚኒየም የተመዘገቡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ዕጣ የደረሳቸው ጥቂቶች ብቻ ሳይሄኑ በተስፋ የሚጠብቁትም ለእነ አብይ እቃ ናቸው። የማይናገሩ፣መብታቸውን የማይጠይቁ፣ወያኔ የፈለገውን ሲሰራ እያዩ እንዳላዩ እንደሆኑት ዛሬም ያው ናቸው ብለው ያስባሉ።
 ስለዚህ ከበሻሻ የመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር እና ፓርቲያቸው በገዛ አገርህ ሁለተኛ ዜጋ ሆነህ ቆጥበህ የሰራኸውን ቤት ዐይንህ እያየ አዲስ አበባን አይቷት የማያውቅ ካድሬ ሁሉ እየተጠራራ ኮንደሚኒየሙን ይሻማልሃል። ተረጋጋ እድሜ ለአቢቹ እንደ ቀረቤታቸው ከአንድ በላይ የደረሳቸው እና ሌላ እያላቸው የተቀበሉ ለኪራይ ያወጡልሃል። ምን አስቸኮለህ። ጠብቅ።ለውጡ እንዳይቀለበስብህ እስክንድርን እና ባልደራስን ማን ይክሰስልህ?
 ምርጫ ሲደርስ እንደሁ ዛሬ ቆመህ ኮንደሚኒየም የታደለው የቤቱ አከራይ በዚህኛውም ቤት ይመርጣል፣በዛኛው ቤት ይመረጣል። ዲሞግራፊ መቀየር አለበት የሚባለው እውን መሆኑን ይህን አይተኽ ካልገባህ የኢንቨስተሩን ድምጣዊ ባለ አህያውን ሚሊየነር ጠይቀው። ኦሮሞ ካልሆነ እዚህ አገር ላይ ከእንግዲህ አይገዛም ያለህም ለዚህ ነው። ተረጋጋ። አብይን ክፉ አይንካብህ። ታከለን ያኑርልህ።ገና ይነቅልሃል። ጠብቅ።ቂቂቂ ድንቄም ለውጥ የህዝብን ትግል እግር ስር ተነጥፈህ በተካነት ካስረከብክ በሁዋላ የምን መናፋረቅ ነው?
አንዳንድ ሰው ይሉኝታ ብጤ የለውም። ጋይስ ይሄ እኮ የሮኬት ሳይንስ አይደለም። አንተ እድሜ ልክህን ቆጥበህ ከወገንህ ጋር እጣ ተጣጥለህ ዛሬ ገብቼበት ነገ ስትል የነበረውን ኮንደሚኒየም ብቻ ሳይሆን ኦሮሞ ካልሆንክ የከተማው አስተዳደር ውስጥ አትቀጠርም ተባለ ሲባል ግድ ሳይሰጥህ ዛሬ ምን ያስጮኽሃል?  ነገም  ለኔ ድምጽህን ትሰጣለህ እንጂ አትመርጥም እያለህ ነው። እባክህ ለውጡ እንዳይደናቀፍ ለቅሶህ እንዳይሰማ አደራ?
እንግዳ ሲሰነብት ባለቤት ይመስለዋል የሚባለው ይሄው ነው። ቦረናን ለቆ ተስፋፍቶ ፊንፊኔ የኔ ናት ለማለት ሁለት መቶ ዓመት ያልፈጀበትን ኦሮሞ በሳይንሳዊ መንገድ ጥቅሙን አስከብራለሁ ያሉት ሳይንቲስቱ ዶ/ር አብይ የሚመሩት ፓርቲ እና ሹሞች ከእነ ጭፍራቸው ፊትህ ተገትሮ ካድሬ በሰልፍ ሲታደለው የባነንከው ኮንደሚኒየም ስለሆነ እንጂ ንግድ ባንክን በአጥንቱ እንዳስቀሩት ማን ይንገርህ !? ጉምሩክን የሚወርሰው እና የሚቀርጠው ለመንግስት ከሚገባው የበለጠው ለአዲሱ አብይ ኦሮሙማ ዳይናስቲ እየገባ አገር እየተዘረፈ ነው ሲባል ጆሮህ ላይ ተኝተህ ካልሆነ የት ነበርክ።ገቢዎችን እግዚኦ ሙስና እንዳስባሉት ማን በነገረህ።
አንተ ወያኔ ላይ ስታላዝን ወያኔን በብልግናውም በዝርፊያውም የሚያስከነዱ ተፈጥረውልሃል ሲባል የት ነበርክ? ለሁሉም ለቅሶህም እንዲያምር ያው ይደርሰኛል ብለህ ለምትጠብቀው ኮንደሚኒየም ባንክ ተሳልፈህ መክፈልህን እንዳትረሳ። ተስፋ ጥሩ ነው። ለካድሬ እየታደለ መሆኑን አልሰማህም አሉ።ብትሰማስ ከለውጥ ይበልጣል? ድሮም ከተራበው ጅብ የጠገበው ጅብ ይሻላል የሚባለው ለዚህ አልነበር። ከአቢቹ ጋር ወደፊት ኮንደሚኒየም ለኦሮሚያ ካድሬ እና የካድሬ ቤተሰብ ወሬ እና ተስፋው ላንተ ።ጽናቱን ይስጥህ አዲስ አበቤ።  ከእባብ እንቁላል እርግብ እየጠበቅ ዘላለም በባርነት እንድትኖር ተፈርዶብህ ይሆን ? ራስህን ጠይቅ ።አበቃሁ።
ባይተዋር ከሆንኩባት ከተማ
Filed in: Amharic