>
5:14 pm - Sunday April 20, 3519

አጀንዳ ሲሰጡህ - ሌላ አጀንዳ አላቸው...!!! (ሀብታሙ አያሌው)

አጀንዳ ሲሰጡህ – ሌላ አጀንዳ አላቸው…!!!

ሀብታሙ አያሌው

ሱሌይማን ደደፎ ከኢመሬት ፤ ሀጫሉ ሁንዴሳ ከOMN አቧራ ሲያስነሱ… ተረኞቹ የኦሮሙማ አዝማቾች በአጀንዳ ጠምደውን አንድ ፕሮጀክታቸውን ሊያስፈፅሙ እንደሆነ አልተጠራጠርኩም። እንደተለመደው ዱካቸውን ተከተልኩ የፈረደበት አዲስ አበባ ላይ ተከለ ኡማን ከነ አፓርታይዳዊ እንቅስቃሴው አገኘሁት..!
ውስጥ ውስጡን ሲያብላለ ካቆያቸው የኦሮሙማ ፕሮጀክት ዛሬ  አንዱን ወደ ተግባር አሸጋግሮታል።  ዛሬ ሰኔ 16 ቀን/2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ላሉ የኦሮሚያ ሰራተኞች በሚል ሠንጋ ተራ ከሚገኘው 40/60 ኮንደሚንየም እና ቦሌ ቡልቡላ ከሚገኘው 20/80 የአዲስ አበባ ህዝብ እየቆጠበ ከሰራቸው ኮንደሚንየም ቤቶች 13 ሺህ ቤቶች እንዲታደሉ ለኦሮሞ ተወላጆች ብቻ እንዲታደሉ ተወስኖ የቤት ዝውውሩ እየተጣደፈ ነው።
ታከለ ኡማ ከዓመት በፊት በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በገላን አካባቢ በአዲስ አበባ ነዋሪ ለሆኑ ለኦሮሚያ ሰራተኞች የቤት መሥሪያ በሚል መሬት ሸንሽኖ ማከፋፈሉ አይዘነጋም።  በዚህ ከዓመት በፊት በተሰጠው ቦታ ላይ መንግሥት መሠረቱን አውጥቶላቸው ቤቶቹ እየተገነቡ ያሉ ሲሆን  ኮንደሚኒየም እደላው  በተጨማሪነት የተወሰነ  ነው።
ቤቱን እየተረከቡ ላሉት ተረኞች የተሰጣቸው ሽፋን  20% ቅድመ ክፍያ  ይከፍላሉ የሚል ሲሆን  “በኦሮሚያ ህንፃዎች አስተዳደር”  በተከፈተ  ጊዚያዊ ቢሮ ይሄንን ፕሮጀክት የሚያስፈፅሙ አካላት በታከለ ኡማ እንዲመደቡ ተደርጓል ።
Filed in: Amharic