>
5:13 pm - Sunday April 18, 1120

"መቆሚያ ያጣዉ የኦሮሞ ብሄርተኞች ስርአት አልበኝነት!!!" (አዲስ አበባ ባልደራስ)

“መቆሚያ ያጣዉ የኦሮሞ ብሄርተኞች ስርአት አልበኝነት!!!”

አዲስ አበባ ባልደራስ

* ህገ-ወጡ ከንቲባ ህግ ጥሶ ወደስልጣን እንደመጣ ሁሉ መመሪያ በመጣስ ህገ-ወጥ መሬት መቸርቸረን ተያይዞታል!!!

* በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12  ሰዎች ተደበደቡ መንገድ በመዝጋት የመብራት ኃይል ትራንስፎርመር ጭምር የሚያጥር መሬት ወራሪ ከአካባቢው ነዋሪ ጋር ተጋጭቷል፤ ፖሊስ ለወራሪዎቹ ጥበቃ ያደርጋል!”
..”ዛሬ ጠዋት ሰኔ 17 /2012 ዓም በቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 40/60 ኮንዶሚኒዬም አካባቢ ወጥረት ተፈጥሯል ህገወጡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ ተደራጅቶ ባሰማራዉ የልዩ ጥቅም ተቧዳኝ  በከተማችን ላይ በሚፈጥረው የመሬት ወረራ ተባብሷል። ቦሌ ቡልቡላ ጉዳዩ ያሳሰባቸው የአካባቢው ወጣቶች ለማስቆም ባደረጉት መኩራ ግጭት ተፈጥሯል።
በማን አለብኝነት መሬት የሚቀራመተው ህገወጡ ቡድን በሚያነሳው ፀብ-ጫሪነት ምክንያት ፖሊስ ጣልቃ አልገባም መብታቸው ነው በማለት ሰዎች እየተጎዱ ነው።
 ይህ ሁኔታ አንድ ቦታ መቆሚያ ካልተበጀለት ወደ ከፍተኛ ቀውስ ሊያመራ እንደሚችል የአዲስ አበባ ነዋሪ እየገለጹ ይገኛል።
 በከተማ አስተዳደሩ እገዛ እና የጸጥታ ሃይል የተባባሪነት ጥበቃ ለህገወጦች በመስጠት እራሱን ቄሮ ብሎ የሚጠራው ቡድን በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የመሬት ወረራ እየፈጸመ እንደሚገኝ ይታወቃል።
በመሬት አሰጣጥ ህጉ  የከተማ መሬት የሚሰጠው በሊዝ እና ምደባ ብቻ ነው ይላል። ዘርዘር አድርጎም ብዙ መስፈርት ያስቀምጣል።  ታዲያ ይሄ ህገወጥ አካሄድ እንኳንስ ሊወቀስ በወንጀል ሊያስቀጣ ይችል ነበር የሚሉት የቦሌ ነዋሪች በአዋጅ ቁጥር 721/2011 እንዲህ ያለ ነገር  አላከተተም።
ህገ ወጥ ከንቲባ ህግ ጥሶ ወደስልጣን እንደመጣ ሁሉ መመሪያ በመጣስ ህገወጥ መሬት መቸርቸር ተያይዘዉታል ብለዋል።
 በቦሌ ቡልቡላ የተፈጸመ አስነዋሪ ድርጊት ዝርዝር መረጃ ሙሉ የቪዲዮ ምስል በእጃችን ይገኛል።
Filed in: Amharic