>

ከ" አገራዊ የውይይት መድረክ" ይልቅ በክልል ደረጃ "መድረክ" ተፈጥሮ መነጋገሩ ይቅደም!!! (አብርሃ ደስታ - የአረና ሊቀመንበር)

አገራዊ መድረክ ማዘጋጀት እንጂ ከህወሓት ጋር በድብቅ የሚደረግ ውይይትን አንቀበልም!!

!ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር)

ከ” አገራዊ የውይይት መድረክ” ይልቅ በክልል ደረጃ “መድረክ” ተፈጥሮ መነጋገሩ ይቅደም!!!

አብርሃ ደስታ የአረና ሊቀመንበር
አገራዊ መግባባት ለመፍጠር ሁሉም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ኃይሎች የሚሳተፉበት አገራዊ መድረክ ማዘጋጀት እንጂ ከህወሓት ጋር በድብቅ የሚደረግ ውይይትን አንቀበልም ሲሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) መናገራቸው ተሰማ።
ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ ይህንን ማለታቸውን የገለጸው የክልሉ ኮሚዪኒኬሽን ቢሮ ሲሆን ይህም በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መስተዳደር መካከል ላለው አለመግባባት መፍትሔ ለማበጀት ዛሬ ወደ መቀለ ከተጓዙት የሐይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ጋር በተወያዩበት ወቅት መሆኑን አመልክቷል።
የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች መማክርት፣ ከትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት ማድጋቸውን ያመለከተው የክልሉ ኮሚዪኒኬሽን ቢሮ መግለጫ ሁለቱ ወገኖች ተቀራርበው በመነጋገር ያሉ ችግሮችን ለመፍታት በአስቸኳይ ግንኙነት እንዲጀምሩ በውይይቱ ወቅት ማሳሰባቸውን አመልክቷል።
ለዚህ ሃሳብ ማብራሪያ የሰጡት የህወሓት ሊቀ መንበርና የትግራይ ክልል መንግሥት ምክትል ርዕስ መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ውይይቱ የተናጠል ሳይሆን ሁሉንም አካላት ማካተት እንዳለበት መናገራቸውን ጠቅሷል።
“የውውይት መድረክ መፈጠር ካለበት ሁሉም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድርጅቶች፣ ብሔር ብሔረሰቦችን የሚወክሉ ፌደራሊስት ኃይሎች የሚሳተፉበት አገራዊ መድረክ መዘጋጀት አለበት እንጂ ከህወሓት/ከትግራይ መንግሥት ጋር በድብቅ የሚደረግ ውይይት አንቀበልም፤ ትርጉምም አያመጣም” ማለታቸውን ቢሮው ገልጿል።
ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ “ውይይቱ በመጨረሻ ሰዓት የተጀመረ ቢሆንም መሞከሩ ግን ጥሩ ነው” ያሉ ሲሆን ጨምረውም “የአገሪቱን ችግር ለመፍታት የሚንቀሳቀስ አካል ችግሩ የተፈጠረው ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ በአገሪቱ አምባገነናዊ ሥርዓት ለመገንባት እየተሯሯጠ በሚገኘው ብልፅግና የተሰኘው ቡድንና በኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እንጂ በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መካከል ብቻ የተፈጠረ አለመግባባት አድርጎ መመልከት አይገባም” ብለዋል።
የሐይማኖት አባቶቹና የአገር ሽማግሌዎች ስለጦርነት አላስፈላጊነት መስበካቸውና ስለሰላምና ውይይት መናገራቸው ልክ መሆኑን ያመለከቱት ደብረፅዮን (ዶ/ር)፣ ነገር ግን “ይህ መባል ያለበት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በማክበር ምርጫ አድርጋለሁ ባለው ክልል ላይ የጦር አዋጅ ለሚያውጀው የፌደራል መንግሥት ነው” ሲሉ ከሰዋል።
በዛሬው የሽምግልና ውይይት ላይ ስለተነሱ ጉዳዮች በተለይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ባነሷቸው ጉዳዮች ላይ አተኩሮ መግለጫ ያወጣው የትግራይ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ እንዳለው፤ መፍትሔ ለማምጣት ተፈልጎ ከሆነ ቢያንስ በክልሉ የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ ሌሎችም መሳተፍ እንደነበረባቸው መናገራቸውን ገልጿል።
ከዚሁ በተጨማሪም የመገናኛ ብዙሃን እንዳይገባ የተፈለገበት ምክንያትም ልክ እንዳልሆነ ተናግረዋል የተባሉት ደብረፅዮን (ዶ/ር) “ወደፊትም ቢሆን መደባበቁ ችግሩን ከማባባስ ውጪ መፍትሄ አይሆንም” ብለዋል።
በውይይቱ ወቅት በርካታ ጥያቄዎችና ሃሳቦች ከተሳታፊዎቹ ለሽምግልና ቡድኑ መቅረቡ የተነገረ ሲሆን፤ እነሱም የተነሱ ጉዳዮችን ይዘው ወደ ፌደራሉ መንግሥት እንደሚቀርቡ ተናግረዋል ሲል የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ መግለጫ ጠቅሷል።
 ጥሪው ጅብ የሚያውቀውም አገር ሔዶ ቁርበት አንጥፉልኝ እንደማለት ይሆን!?
ተቃውሞ እና የልዩነት ሀሳብን እንደ ሽብር እና ሽብርተኛ የሚቆጥረው ሕወሓት ከዚህ ቀደም በጉዋዳ  የፈለገውን ምስክር እንዳልኖረ ሁሉን አቀፍ ውይይት ጥሪ አድርጓል። ነገሩ ጅብ የማያውቁት አገር ሔዶ ቁርበት አንጥፉልኝ አለ እንዳይባልም ግራ ያጋባል። አንዳንዶቹ ሽማግሌዎች ትላንት የህወሓት ኢህአዴግ አድተዳደር ሽማግሌዎች ስለሆኑ ይተዋወቃሉ። ስለዚህ የዛሬ የኢትዮጵያ የሀይማኖት አባቶች ጉባዔን ወኪሎች በተለመደው የዱርዬነት ጠባያቸው አስተናግደዋቸዋል። አንዳንዶች እነዚህ ነበሩ 27 ዓመት አገር መራን የሚሉት ሲሉ ማዘናቸው እየተሰማ ነው።
“ዶር ደብረፅዮን “አገራዊ መግባባት ለመፍጠር ሁሉም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ኃይሎች የሚሳተፉበት አገራዊ መድረክ ይዘጋጅ” ብለዋል። የሚደገፍ ሐሳብ ነው። እኔም በተደጋጋሚ ስለው የነበረ ነው። ግን ህወሓት ይህንን  ሐሳብ ምትደግፍና ምታምንበት ከሆነ ለምን መጀመርያ በክልል ደረጃ “መድረክ” ተፈጥሮ ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች  ተገናኝተው እንዲነጋገሩ አይደረግም? ከዛ ወደ ሀገር ደረጃ እናሳድገዋለን። ወይስ ሐሳብዎ በሀገር ደረጃ እንጂ በክልል ደረጃ አይሰራም? መጀመርያ ራስን መፈተሽ መልካም ነው።”
Filed in: Amharic