>

ግራ አጋቢው የኮሮና ጠባይ !!   (ዘመድኩን በቀለ )

ግራ አጋቢው የኮሮና ጠባይ !!

 ዘመድኩን በቀለ
እኔምለው ጤፍ ግን ስንት ገባ ?

•••
ቀደም ባለው ወራት አንድ በኮሮና የተያዘ ሰው ተገኘ ተብሎ ዜናው ወሬው ከተሰማ ሀገር ሙሉ ዝግ ይሆን ነበር። በሰማይም፣ በየብስም፣ በባህርም እንቅስቃሴ አይኖርም ነበር። ጦር ሰራዊት አየር ሀይል፣ ምድር ጦር በተጠንቀቅ ይቆም ነበር። ነበር ነው ያልኩት።
•••
የሰው ልጅ ከቤቱ እንዳይወጣ፣ በአደባባይ እንዳይታይ፣ እጁን በሳሙና እንዲታጠብ፣ ሳኒታይዘር እንደ እምነት እንዲቀባ፣ እንዲተሻሽ ይደረግም ነበር። በግድም፣ በዱላ በጥፊም ከቤቱ ይቀመጥ ዘንድ ይታዘዝ ነበር። አፍህን ሸፍን፣ ርቀትህንም ጠብቅ ትእዛዙ ገራሚ ነበር።
•••
ትምህርት ቤቶች ይዘጉ፣ ትራንስፖርት ይጠረቀም፣ ሆተል፣ ኪዮስክ፣ መዝናኛ፣ መገናኛው ሁሉ ይጠረቀም ነበር። ( በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤት እስከአሁን ዝግ ነው። ቡናቤት ግን ለአዲስአበባ ፖሊስ የቀን ገቢውን በጉቦ መልክ እያካፈለ እስከአሁን ክፍት ናቸው አሉ። ፖሊሶች የአዲስ አበባ ቡናቤቶችን በየወረዳው ተከፋፍለው የቀን ገቢ ይከፋፈላሉ አሉ። ደካማ መንግሥት መገለጫው ፖሊሱ ሌባና ያገኘውን ወጋሪ፣ ቀማኛ ይሆናል። )
•••
በቀደመው ወራት የኮሮና ሟቾች የዜናቸው ብዛት ለሰሚው ያስደነግጥ ነበር። የሟቾች ቀብራቸው ባይታይም የሟቾቹ ቁጥራቸውግን አስደንጋጭ ነበር። የኦሎምፒክ ውድድር ይመስል ነበር። ቻይና አንደኛ፣ ጣልያን አንደኛ፣ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካ አንደኛ 50 ሺ፣ መቶ፣ ሺ ሲባል ለሰሚው ያስደነግጥ ነበር። በሽታው አለ። የሞቱም፣ የታመሙም፣ የዳኑም አሉ። ነገር ግን ኡን ምንተገኝቶ ይሆን? ቀዝቀዝ ያሉት እነ አማሪካ።
•••
ጸሎቱም ልዩ ነበር። እንባ የተቀላቀለበት፣ መንበርከክ ያለበት፣ ደረት እየተደቃ፣ እየወደቀ እየተነሣ ጸሎት ይደረግ ነበር። ቴሌቭዥን ሬድዮኑ ሁሉ ጸሎት፣ ንስሐ ያውጅ ነበር። ቤተሰብ ከመኝታ በፊት አደግድጎ ለጸሎት ይቆም ነበር። ያው ነበር ነው እንግዲህ።
አሁንስ?
•••
በአማሪካ ሰዉ ከቤቱ ተቀምጦ ይነገር የነበረው የሞት መርዶ አሁን ሰዉ ለሰልፍ ከቤት ወደ ደጅ ወጠቶ በደጅ ውሎ እያደረ፣ ከፖሊስ ጋር ሲተሻሽ፣ ሲተቃቀፍ ውሎ እያደረ፣ የሟች ዜና መጥፋቱ፣ የኮሮና ዜና ቁጥሩ መቀነሱ፣ ጭራሽ ዜናው ያለመኖሩን ስታይ የሆነ ነገር ጠርጥር ጠርጥር ያሰኝሃል። መድኃኒቱ ሰልፍ ነበር እንዴ? ሆሆይ!!
•••
በኢትዮጵያም እንደዚያው ነው። የቀደመው ፍርሃት ጠፍቷል። የቀደመውም የሚድያ የጸሎት መርሀግብርም በወሀቢይ እስላም ድንቁርናና ጥጋብ ሌሎች ሃይማኖቶችን በስብከት ስም በመሳደቡ ምክንያት አሁን ቆሟል፣ ተቋርጧል። ይቅርታም አልጠይቅም ብሎ ሁሉን ነገር እኔ ከሞትክ ሰርዶ አይብቀል ብሎ አፈር ከደቼ አብልቶታል።
•••
በኮሮና የተያዙ ሰዎች የሞት ቁጥር በዜና ሲነገር እያየን ነው። ቁጥሩ በአዲስ አበባ ከፍ ብሏል። አሻቅቧል። ሟቾቹ በቁማቸው ሳይመረመሩ አስከሬናቸው እየተመረመረ በኮሮና የመያዛቸው ዜና መነገሩ ደግሞ የበለጠ አስቂኝ፣ አስገራሚም ነገር ሆኗል። ይታያችሁ አስከሬን መርምረህ ሀገር ምድሩን ስታሸማቅቅ። በቁም ሳትመረምር አስከሬን እየመረመረች መርዶ የምታረዳ ብቸኛ የምድራችን ጉደኛ ሀገርም ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን አትቀርም።
•••
ደግሞም ደግሞ የታከለ ኡማን አፉን ሳይሸፍን በድፍረት በከተማዋ ውስጥ መንቀሳቀስ ስታይ፣ የዐቢይ አሕመድን 5ቢልዮን ችግኝ ትከሉ ማለትን ስታይ፣ የህወሓትን ማንአባቱ ያገባዋል? ምርጫ በክልሌ አደርጋለሁ የምን ኮረና ነው ማለቷን፣ እስቲ የሚናገረኝን አያለሁ ማለቷን ስታይ፣ ( ለምርጫ መስፈጸሚያ ብሩ እንኳን አላት። አይቸግራትም። በኮንቴነር አይደል እንዴ የምታስቀምጠው። ብሩ ከተቀየረ ነው ህወሓት የምትከስረው። እንጂ አሁን እንኳ በፈረንካ በኩል ችግር የለባትም።) እናም ይሄን ይሄን ስታይ ኮረና የለም እንዴ? ትልና ጠርጥር ጠርጥር ያሰኝሃል።
•••
እዚህ ባለሁበት በሀገረ ጀርመን ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በቀር ሁሉ ነገር እንደ ድሮው ነው። መስክ የሚደረገው እንኳ ትራንስፖርትና ሱፐር ማርኬት ሲገባ ብቻ ነው። በባለፈው ሳምንት ከአንድ ጓደኛዬ ጋር በምንኖርበት ከተማ ወደ አንዲት ፒዛ ቤት ገብተን ነበር። እናም ሁሉም ነገር እንደድሮው ነው። ወይ ኮሮና።
•••
ለማንኛውም በአማሪካ፣ በአውሮጳ፣ በካናዳ ከባድ ሰልፎች ተደርገዋል። በአሜሪካ እስከአሁንም ሰልፉ አልቆመም። የኮሮና ዜና ግን ቆሟል? በኢትዮጵያ በኮሮና የሚያዘው ሰው ዜና ከፍ ብሏል። በኢትዮጵያ ሟቾች በኮሮና መሞታቸው የሚታወቀው አስከሬን ሲመረመር ብቻ ነው። እንደ ዜናው አዲስ አበባ የኮሮና ማከፋፈያ ሳትሆን አልቀረችም።
•••
እስቲ የዛሬውን የአዲስ አበባ የኮሮና ዜና እንመልከት። ደግሞ የሟቾች ስም አይነገርም። ዕድሜና ጾታ ብቻ ነው። እንዴት እንደሚቀበሩም አይታወቅም መሰለኝ።
በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 47 ደረሰ!
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የሰባት (7) ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸውና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 47 ደርሷል።
ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦
1. የ75 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።
2. የ70 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው።
3. የ80 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው።
4. የ29 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት።
5. የ48 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘበት።
6. የ85 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው።
7. የ21 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት።
• ለማንኛውም፦
• ጸሎቱ አይቋረጥ።
• ንስሐ እንግባ
• እጃችንን በሳሙና እንታጠብ
• ርቀታችንን እንጠብቅ
• አፋችንን እንሸፍን።
ፈ   ቀ   ቅ   ታ  !!
•••
ሻሎም  !   ሰላም  !
Filed in: Amharic