>

የጤና ባለሙያው የጤናችን ጠንቅ ሆነ!!! (የታማሚዋ መድሀኒት ገ/መድህን ገጠመኞች)

የጤና ባለሙያው የጤናችን ጠንቅ ሆነ!!!

(የታማሚዋ መድሀኒት ገ/መድህን ገጠመኞች)


 

* ቫይረሱን አስታቅፎን ሲጠባበቀው ወደ ነበረው አምበላንሱ ሄደ …!!!

የሰፈራችን ልጅ ነው አሉ። በነርስት አንድ ሆስፒታል ያገለግላል። ሆኖም በአንድ ክስተት ሆስፒታላቸው ውስጥ የሞቱት ሴትዮ ምርመራ ሲደረግላቸው የሞቱበት ምክንያት በኮሮና ስለሆነ በሚል ከልጁም ሳምፕል ተወስዶ ውጤቱ እስከሚታወቅ ከሰው ጋር አትንቀሳቀስ ይባላል፡፡

አራዳነት ይሁን የልብ ክፋት አልያም የተባለውን ዘንግቶ ከሰፈር ልጆች ጋር እሁድን ኳስ ለመጫወት መጣ፤ በበቃኝ ሳያልቅ በአምቡላንስ በአስፈሪ ጩህት ወደ ሜዳው መጣ በተከለካይነት ሲጫወት የነበረውን ነርስ ይዞት ሄደ፤ በቀጣይ  ሌሎቹንም ንክኪ ይኖር ይሆናል በሚል የተወሰደው ሳምፕል ከሁለት ቀናት በዋላ ተባለ፤ ውጤቱ ደረሰ 3 ልጆች ተወሰዱ፤ በዚህም አላቆመም  የወንድሜን ሁለት ጉደኞች በኮሮና መያዛቸው ተረጋገጠ ፡፡ ልጆቹ በተደጋጋሚ ወንድሜንና የጎረቤታችንን ልጅ ብለው ይመጡ ስለነበር እንደ ቤተሰብ ነን ድንጋጤ ፍርሀት ሽብር ተነዛብን፤  በቃ አለ አይደል ወንድ የሆነ ያለ ማስክ እኛ ቤት ይገባል ነውርም አይደል ፤ደሞም እኮ ሳኒታይዘርም እናስጠቅማልን፡፡

ብቻ ምን አለፋቹ ይህ በሽታ እኛ ቤት እንዳይገባ የሩቅ እንግዳ ስናባርር ለካንስ ቀድሞን ገብቶ ኖሯል፡፡ ሳምንት ሳይሞላ የወንድሜ ጎደኛ ላይ ምልክቶቹን ማየት ጀመርን ከትኩሳት የጀመረው ህመም ብርድ ብርድ ፤ማስቀመጥ፤ አለፍ አለፍ ያለ ሳል ፤ድካም ብቻ ስለበሽታው የሚነገረን ምልክት በሙሉ ታየበት ፡፡ ጤና ጥበቃ በመደወል እንዲታይ ጠየቅንና ከወንድሜና ጎደኛው ጋር በመሆን ይዘውት ሄዱ ታዲያ እሱንም ይዘውት የሄዱትንም ጨምረው ማቆያ አስቀመጡዋቸው እያለ ውጤት ሲመጣ ፖዘቲቭ መሆኑን ተረጋገጠ ቀስ እያለ ወደ አምስት ሰው ተወሰደ ሁሉም በየተራ አለባቹ እየተባሉ ተወሰዱ ይሄን ግዜ ነው መሸሽ ትላለች አያቴ ፡፡

ከዛማ እቤት ውስጥ ያለነውና ጎረቤት ያለነው ወደ አስር ሰዎች በንክኪ ሰበብ ተመረመርን እናም በ 72 ሰዓት ውስጥ ይደወልላቹሀል ተብለን ወደቤታችን ተመለስን፡፡ አዲስ ቁጥር ወደስልካችን በጠራ ቁጥር ፍርሀቱ አይጣል ነው፡፡ መድረሱ አይቀር ከኛ ቤት ለኔ ከጎረቤታችን ደሞ ለመቅዲ ተደወለላት በህይወቴ እንደዛ ደንግጬ አላውቅም ቤተሰቦቻችን በሀዘን ጉም ሆኑ በብዙ ታናሼ ስለሆነች ለሶ ስል ጠነከርኩ ቀድመው የወጡት ወንድሞቻችን ሳይመለሱ እኛ ተከተልን፡፡

ትልቁ ህመም። በዛ ሀገሪቱን ሁሉ ያዙኝ ልቀቁኝ በሚል አምፖላንስ መሄድ ነው፡፡ የማይደርስ የለም ሽብሩን እያሸበረ እኛን ለመውሰድ መጣ። ማንንነታችን ተረጋግጦ አምፖላንስ ስር እስከምንገባ የከበበንን ህዝብ ማመን ከሚያቅተን በላይ ተባዛ፤ እትዬ እንትና እራሱ የዛ ቀን መራመደድ ችለው እኛን ማየት ቻሉ። ትልቅ ሀጢያት እንደሰራ ሰው ህዝቡ ሁሉ እየተጠቁቆመብን ወደ አምፖላንስ ውስጥ ገባን፡፡ ከውስጥ ሁለት ሰዎች ቁጭ ብለዋል መንገድ ላይ እያሉ ተደውሎላቸው ከመንገድ ነው የተወሰዱት አንዳችም ልብስ አልያዙምም እነሱን ሳይ ተጽናናው፡፡

ከውስጥ ያገኘናቸውም እኔና መቅዲም ምንም ምልክትም ህመምም አልነበረብንም ሆኖም እላያችን ላይ የተለቀቀው ኬሚካል ከጭንቀታችን ጋር ተደምሮ ህመም ህመም ቢጤ ይለን ጀመረ። እራስምታት ለቀቀብኝ በዛ ላይ ያለንበት አምፖላንስ ወደውጪ አያሳይም በተጨማሪም ከሃላችን ከሚያንቦርቁት ሁለት አምፖላንሶች ውጪ የትና ወደየት እየሄድን እንዳለን ምንም የምናውቀው ነገር አልነበረም፡፡

እኔን ያልገባኝ ምንም አይነት አስጨናቂ ሁኒታ ውስጥ ያለ ታማሚ አልነበረም አምፖላንሶቻችን እንደዚ ታማሚንም ህዝብንም ማሸበር ለምን አስፈለገ? ያለምንም የድምጽ ብክለት እኮ መውሰድ ይቻላል። በበሽታው ያን ያህል እውቀት የሌለውን ህብረተሰብ ለምን ማሸበር አስፈለገ?

በመጨረሻም የማይደርስ የለም ሽሮ ሜዳ ጋር ወዳለው ቅዱስ ፔጥሮስ ደረስን ኮተቤም ስለሞላ በእኛ መጀመሩ ነው፡፡ ዝግጅት ስለሚጎላቸው እየተደነባበሩ ወንድና ሴቶችን እንድ ላይ ደባለቁን፡፡ ጀማዎቻችን ስናገኝ ፈጣን ትውውቅ አደረግን ስድስት ሰው ባለበት ክፍል ውስጥ አንድ ብቻ በ40 ዎቹ የሚጠጉ ኦክስጅን የሚጠቀሙ አባት አገኘን። እኛን ሲያዩ ቀለል ቀለል ይላቸው ጀመር፡፡

ሳናስበው ሁላችንም የቴሌ ኦፕሬተርነት ማዓረግን ተቀላቀልን በላይ በላይ ስልካችን ይጠራል። ሄሎ አቤት፤ሄሎ አቤት ብዙ ሄሎ አቤቶች፡፡ ይህቺን አጋጣሚ ተጠቅሞ ስልክክን አጊንቶ እዛ ሰፈር ያለው ጎረምሳ እራሱ ይደውልልሀል። ሊጠይቅክ ደውሎ እኔን እኔን እያለ ሲያምልልክ ይውላል። ደሞ አሉ ሰፈር ወሬዎችን አፕዴት የሚያረጉ እነሱ ከደወሉልክ ሰፈር ላይ እንዲወራ የፈለከውን ነገር ለሳቸው እየገነርክ አስመስለክ ታወራላቸዋለክ እንደደረሰ ለማወቅ ብዙም አይፈጅብክም ሌላኛው ሊጠይቅክ አስመስሎ ወሬውን እንድታረጋግጥለት ይጠይቅሀል ፕሩፍም ታረጋለህ። ጉድ እኮ ነው

ክፍላችን ውስጥ ያሉት አባት ቀለል ስላላቸው ኦክስጅኑ ተነቀለላቸው ወዲያው ልጃቸው ጋር ደወሉላት ምንም ህመም የሌላቸው መስለው አወሩ እገባለው ብላ ፍርሀት ተሰምቶታል መሰለኝ በይ ከመጣሽ እዚ ቆንጆ ቆንጆ ልጆች ስላሉ ሜካፕሽን ይዘሽ ነይ ብለው ቀለዱ እኛንም ፈገግ አስደረጉን ትንሽም ሳይቆይ ወንድና ሴት ይለይ ተብሎ ተለየን፤ አባባን ተሰናብተን ሄድን አባባም ከሁለት አስቸገሪ ቀናት በሆላ ማረፋቸውን ሰማን

ከባለስድሰት ክላስ ሶስት ሰው ወደሚይዘው ክላስ ገባን የሺ የምትባል ልጅ ተቀላቀለችን ገና መግባቶ ስለነበር ተደናግጣለች ተጫዋች ቢጤ ስለሆንን በጫወታ አስረሳናት ከስራ ቦታ ወደ ቤቶ ኮካ ስትሄድ አሜን ሆስፒታል ጋር ሳምፕል ሲሰጥ አይታ አብራት ከነበረቸው ጋር የተመረመረችው፡፡ ምን ህመም የለብን ለምን እንሰጣለን እያለቻት የተመረመችው ልጅም የሺም አለባቹ ተብለው የተጠሩት ይህን ስታይ አዲስ አበባ ላይ ምን ያህል እንደተሰራጨ ትመለከታክ

ህመም ከሌለብክ ምንም አይነት ህክምና አይደረግልክም ባይሆን የምትጠራጠረው ህመም ካለብክ በዚ አጋጣሚ ወገቤን ልቤን እያልክ ቼክአፕ ትደረጋለህ። ያለወጪ ህክምና አገኘክም አይደል ምግብ ላይ ያለው እንክብካቤ አይጣል ነው ቺክን ነው፣ ስጋ ነው። ሳላድ በቃ ጥጋብ ነው የኔ ጌታ እቤት ትደውልና ምን ዘንድሮም ሽሮ ነው ብለክ ታላግጣለክ።

ኢትዮጵያ ሀገርክ ላይ ሆነክ በናይጄርያ ሙዚቃ ከጎረቤት ትቀሰቀሳለክ ዳንሱን በስፖርት ሰበብ ያስነኩታል በቃ የናይጄርያ ዘፈን ይመቸኛል ትላለክ ያው አባቴ እንዳትቀላቀል ጸሎት ማድረግ አለብክ እራስክን ገዘተክ ለፈጣሪ ጸሎት ታደርጋለህ። ሴጣን ሳታስበው የራከውን አምላክክን ያስታውስክካል

በመሀል ለህክምና የሚመጣው ህዝብ ሲበዛ ህመም የሚታይበት ሰው ሆስፒታሉ ሊቆይ እኛ ደሞ ሚሊኒየም ልንወሰድ ደምድመው መጡ የሚገርመው ዶከተርና ጽዳት እራሱ የምትለየው መወልወያ ሲይዙ ብቻ ነው፡ ማን የለመደውን ቤት ይለቃል፤ እንደሌባ በለሊት መጥተው ከበቡን እራሳቸውን እነደኮሚቴ የመደቡት ሰዎች አሳምነውልን ቀረን፡፡ እኛ እኮ ሚሊኒየም ላለመሄድ ህዝብ ተሰልፎ ሽንት ቤት ነው የሚጠቀመው። ሻወርማ ጉድ ነው ከቀኑ ሶስት ሰዓት ለመግባት ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ ነው የሚሰለፉት እያልን ከኮሚቴው ጋር ተማከርን። እራሳችንን የተሻለ ቦታ ላይ አደረግን።

የበቀል መነሻ የሆነች ቀን:- የተሻለ ሀሳብ አመጣን ብለው ጊቢ ውስጥ ወዳለው አዲስ ህንጻ ሊያሻግሩን ተስማማን በንጋታው ብርድልብስና አንሶላችንን ሳይቀር ተሸክመን ወደ አዲሱ ህንጻ ለመሄድ ጉዞ ጀመርን፡ ለካ ህዝቡዬ ታቦት ሲወጣ ዳር ዳር አንደሚቆሙት፣ የሆስፒታሉ ሰራተኛ በሙሉ ወጥቶ በታጠቀ ፖሊስ ተከበን እኛ የሀጺያት ቀምበራችንን ተሸክመን መሀል መሀል ይዘን መሄዳችንን ቀጠልን፡፡

በሰፈራችን የሰቀጠጠንን ከበባ እዚ ባሰብን ሆ ብለው ወጥተው ተጠቋቆሙብን:-

ሆስፒታል ውሰጥ አገልግሎት የሚሰጡ ዶክተሮች ነርሶች ጽዳቶች አስተዳደሮች ተሰብስበው እየተጠቆቆሙ አገለሉን፡፡ እኛን ያየ አበል ይከፈለዋል የተባለ ይመስል ዳር እስከ ዳር ጥጋቸውን ይዘው ጠበቁን ፤በስህተት በመንገዳችን የገባው ሰው በአንድነት ዞር በል፣ዞር በል እያሉ ተጮጮሁብን። ሁሉም ታማሚ በአንድ ልብ የቂምና የክፋት ስሜት ተሰማው፤ በቁስላችን ላይ ያክሙናል ያልናቸው እንጨት ሰደዱብን ባር ባር አለን። ሁሉንም ቤት የሚያንኮኮ በሽታ መሆኑን ዘንግተው እኛን ተጠየፉን ፡፡

ይሄ ሁሉ አልፎ ከኮረና ነጻ ነሽ ተባልኩ። የወንድሜን ወደቤት መግባት በሰማው በንጋታው ዛሬ ከሀጢያትሽ ቀምበር ነጽተሻልን ወደቤትሽ ተመለሽ ተባልኩ፡፡ የማይቻለውን ሀሉ የቻልክ አምላኬ ሆይ ክብር ምስጋና ይገባሀል። እናቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ግዜ ሁሉ አጠገቤ ለኔ እንደነበርሽ በጭንቅ ስላሉት በሙሉ ድረሽላቸው ሀገራችንን ሰላም ይሁንልን፡፡ በጸሎት ላሰባችሁኝ በሙሉ አመሰግናለው፡፡

Filed in: Amharic