>

የCOVID-19) ክትባት እና ማይክሮችፕ!!! (በቃሉ አበራ)

የCOVID-19) ክትባት እና ማይክሮችፕ!!!

በቃሉ አበ

ለማይክሮ ችፕ ምንነት ለጓዴኞቻችሁ አሳውቁ። ወገናችንን እናትርፍ። ጉዳዩ እጅግ እጅግ መፍጠንን ይጠይቃል ነጮቹ  በኮሮና ቫይረስ (#COVID-19) ክትባት አስመስለው ዓለምን በማይክሮ-ችፕ ሊያጥለቀልቁት ነው በእውነት። ስለ እኛ መንግስት በቂ መረጃ ባይኖረኝም የብዙ ሀገራት መሪዎች ጉዳዩን አሜን ብለው ተቀብለውታል። 
 ይሄን ጽሁፍ የጻፍኩበት ምክንያት ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ዛሬ ረፋድ ስለወቅታዊ ጉዳይ እያወራን ስለ አውሬው ቁጥር 666 ወይም ደግሞ የማይክሮ-ችፕ ቴክኖሎጅ ብለው ሊያጠፍን ስላመጡብን ነገር ስናወራ በሚገርም ሁኔታ ምንም ግንዛቤው የለውም። ላስረዳው ሞከርኩ ምን አለኝ መሰላችሁ “እኔ ምን አገባኝ የዓለም ህዝብ ካደረገው እኔ ማን ነኝና ነው እምቢ የምለው ደግሞ እግዚአብሔር አምላክም ቢሆን ይሄን ሁሉ ህዝብ እንደት ሊያጠፋ ይችላል” አለኝ።
አምላክ ህዝቤ ባለማወቅ ጠፋ ያለውኮ ነገሮችን አውቀን እንዲንድን ነው አይደል።  እንግዲህ ይሄን ያለኝ ሰው በዘመናዊ ትምህርት ዝግጅቱ የማስተርስ ዲግሪ ያለው ነው። ሌክቸረርም ነው። አያችሁ ክፍተታችንን? አሁን ይሄ ሰው ቴክኖሎጂ ነው ብሎ ከተቀበለው ያልተማሩትስ? አስቡት። ምናልባት የሚድኑት የሃይማኖት ትምህርቱንና ወንጌልን በደንብ ብልት ያደረጉ ከእነዚህም የፀኑ ብቻ ይሆናሉ ማለት ነው።
~~~~
በዚህ ባለፈው ሳምንት የዚህ ማይክሮ-ችፕ ክትባት ቅስቀሳውን በእስራኤል ሀገር ጀምረውታል? ይህም የተደረገው የኮሮና ቫይረስን መስፋፋት በቴክኖሎጅው ክትባት (Vaccine) አማካኝነት ለመቆጣጠርና የህዝቡንም ሰላምና ደህንነት ለመቆጣጠር ነው ተብሏል።
~
ታዳ ለምን ቅስቀሳው ከሀገረ እስራኤል ጀመረ ? ለሚለው:-
እውነቱ ሌላ ቢሆንም የዓለም ህዝብ የሚያስበው ሀገረ እስራኤል የክርስቲያን (ኦርቶዶክስ ተዋህዶ) ሀገር እንደሆነች ነው። ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደባት ስለሆነች።  በዚህም መሰረት መጽሐፍ ቅዱስ የሚከለክለውን የማይሮ-ችፕ (የአውሬው ምልክት) ማድረግ የእስራኤል ህዝብ ከተቀበለው ችግር የለውም ማለት ነው የሚለውን እሳቤ የዓለም ህዝብ ይወስደዋል እናም ብዙም ቻለንጅ የሚያደርገን አይኖርም በሚል እሳቤ ነው።
ይህን በእነርሱ የረቀቀ ቴክኖሎጅ (ማይክሮ-ችፕ) በእኛ የአውሬው ምልክት 666 በዓለም ህዝብ ላይ ለመግጠም (ለማድረግ) የመጀመሪያ እንቅስቃሴያቸውን በኮሮና ባይረስ COVID-19 አማካኝነት ለማስቀበል አስበው ተነስተዋል ይሄውም በእስራኤል ሀገር ባለፈው  በ12 በእኛ ግንቦት 4 ማለት ነው መንግስታቸው አውጇል።
 በመጀነሪያ በውደታ (በፍቅር) ይሆናል። ከዚያ ግን ግደታ ነው (It’s mandatory for alive)። አልቀበልም የሚል ሁሉ ይገደላል። ከሲስተማቸውም ውስጥ አናስገባም በማለት እርቦት ጠምቶት እንድሞት ይደረጋል። ምክንያቱም እያንዳንዱ አገልግሎት ማለትም ትምህርት፣ ጤና፣ መብራት፣ ውሃ፣ ባንክ (ATM ካርድ አያገለግልም)፣ ትራንስፖርት፣ ገበያ … ማንኛውም አገልግሎት በዚህ ውስጥ ያልፋል ማለት ነው። ስለዚህ ይሄንን ሲስተም አልቀበል ያለ ከዚህና መሰል ሁሉ አገልግሎቶች ይገደብና ነፍሱን ይዞ ወደ አምላኩ ይሄዳል (ይገደላል) ማለት ነው። ጽድቅንና ሰማዕትነትን ለሚሹ ሰርግ ናት በርግጥ። ስለሃይማኖት ተሰቃይቶ መሞት ደስ ለሚለው ይለዋል።
 ቴክኖሎጅ ነው ብሎ የሚቀበል ካለ ደግሞ ገና ሲቀበርበት በእነርሱ ቁጥጥር ስር ይወድቃል ማለት ነው። የራሴ ሚስጥር (Privacy) የሚባል ነገር ያበቃለታል(ያከትምለታል) የእኛና የቤተሰቤ ብቻ የምንላቸው ምንም ነገሮቻችን ሁሉ በእነርሱ እጅ ላይ ትሆናለች ማለት ነው። እያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን፣ የምንሰራው የምንከውነው ሁሉ ጭምር ።
ምን ይሄ ብቻ ይሄና ደህና የሚያስጠላው ነገር ሰውዬው እነርሱ የፈለጉትንም እንዲያደርግ ያስገዲዱታል። ለምሳሌ ከቤተሰቦቹ ጋር፣ ከእንስሳት ጋር ከግዑዝ ነገሮች ጋር ከማንኛውም ፍጥረት ጋር ሳይቀር ግብረ ስጋ ግንኙነት እንድፈጽም ያደርጉታል። ሞት ማለት ይሄ ነው እንጅ ማይክሮ ችፕ አላስደርግም ብሎ መስዋዕትነትን መቀበል ከየት መጣሽልኝ የምትባል ቅመም የሆነች ስጦታ ናት ለብልህና ፀልዮ አምላክ ለረዳው ሰው። እንደት እንደዚህ ለሚሉት ሰዎች ደግሞ ምን መሰላችሁ ማይክሮ ችፕ ማለት ሲስተም ነው። የራሱ የሆነ የህዝቡን ኢንፎርሜሽን የሚይዝ ዳታቤዝ አለው እናም ሰውዬውን እራሱን ማንነቱን እንደ ባንክ ሀክ ሁላ እያደረጉ እንደፈለጉ ያደርጋሉ ማለት ነው። ሰው እንደት ነው ምኑንስ ነው ሀክ የሚደረገው ከተባለ ደግሞ ለምሳሌ:- ያንን ማይክሮ ችፕ የተቀበረበት ሰው እነሱ ወደፈለጉት ቦታ እንዲንቀሳቀስ ያደርጉታል ከዚያን ከሰውነት ክፍሉ ኩላሊት ምናምን የፈለጉትን እየወሰዱ መለዋወጫ ያደርጉታል።
ይሄን ለምን ይሰራሉ? የሚል ካለ ደግሞ ዓላማቸው ነው። እነርሱ የሚፈልጉት የዓለምን ህዝብ ከእግዚአብሔር አምላክ መንገድ አውጥተው ነፍስንም ለዳቢሎስ ማስረከብ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ  በአምሳሉ የፈጠረውንና የሞተለትን ክቡሩን የሰው ልጅ ማጥፋት ማለት በነፍስ ማጥፋት ነው። ጽድቅን ማሳጣት ማለት ነው።
~~~~
~
ለበለጠ መረጃ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 13ን አንብቡት በዚህ ምዕራፍ ቁጥር 15-18 ላይ ቁልጭ ብሎ ተቀምጧል።
Filed in: Amharic