>

"ህወሓት አንድ ነን እንደሚለው፤ ህወሓትንና የትግራይ ህዝብን አንድ አይደሉም !!!"  (አቶ ደረጀ በቀለ) 

“ህወሓት አንድ ነን እንደሚለው፤ ህወሓትንና የትግራይ ህዝብን አንድ አይደሉም !!!”

 አቶ ደረጀ በቀለ 

•”በተጨባጭ እንዳየሁት የትግራይ ህዝብ መፈናፈኛ ስላጣ ዝም ብሏል” 
•”ህወሓት በከተማ ውስጥ እንጂ በገጠር የለም። ይሄንንም ከመቐሌ እስከ ደደቢት እና ዛላንበሳን ተጉዤ ተመልክቻለሁ”
•”ትግሬ ሁሉ የተጠቀመ፤ ትግሬ ሁሉ የህወሓት አባል የሆነ አድርጌ ሳይ የነበረበት ሁኔት የተሳሳተ መሆኑን አይቻለሁ”
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፦ ህወሓትንና የትግራይ ህዝብን በአንድ ላይ ማየት የተሳሳተ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ሊቀመንበር አስታወቁ። ህወሓት/ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ/ የበላይነቱን ለማንጸባረቅ ብቻ የሚንቀሳቀስ ቡድን መሆኑን አመለከቱ።
ሊቀመንበሩ አቶ ደረጀ በቀለ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳመለከቱት ፣ህወሓት አንድ ነን እንደሚለው፤ ህወሓትንና የትግራይ ህዝብን በአንድ ላይ ማየት የተሳሳተ ነው።
ቀደም ባለው ጊዜ እኔም ከህወሓት አመራሮች ትርክት ተነስቼ የትግራይ ህዝብና ህወሓት አንድ ናቸው ብዬ አስብ ነበር ያሉት ኃላፉው ፣አሁን ውስጡ ገብቼ እንዳየሁት ግን በጣም የተራራቁ ናቸው። የህዝቡ ኑሮ ከእጅ ወደ አፍ ሲሆን ጥቂት የህወሓት አመራሮችና እነርሱን ተጠግተው ያሉ ግን በጣሙን ከህዝቡ የራቀና ሊነጻጸርም በማይችል የናጠጠ ኑሮ ውስጥ እንደሚኖሩ አመልክተዋል።
እኔም ትግሬ ሁሉ የተጠቀመ፤ ትግሬ ሁሉ የህወሓት አባል የሆነ አድርጌ ሳይ የነበረበት ሁኔት የተሳሳተ መሆኑን አይቼ ታርሜአለህ የሚሉት አቶ ደረጀ፣ ይሄን ምስል ያስያዘኝ የህወሓት አሳሳች የሴራ ምስል መሆኑን በተግባር አረጋግጫለሁ ብለዋል።
“ህወሓት በከተማ ውስጥ እንጂ በገጠር የለም። ይሄንንም ከመቐሌ እስከ ደደቢት እና ዛላንበሳን ጨምሮ ሌሎችም የትግራይ ክልል ክፍሎችን ባስጎበኙኝ ወቅት ተመልክቼ ተገንዝቤያለሁ። በእነዚህ የክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች በነበረኝ ጉብኝት የተመለከትኩት እና አንዳንዴም አማርኛ የሚናገሩ/የሚችሉ ሰዎችን አነጋግሬ እንደተረዳሁት፤ ህወሓት ከህዝቡ ጋር የለም። ምናልባት የተወሰነ ህዝብ ነው ከህወሓት ጋር ያለው” ብለዋል።
“ይሄ የተወሰነ ህዝብ ደግሞ በመቐሌ ከተማ እና ዙሪያዋ ያሉ ጥቂት ሰዎችን የሚመለከት ሲሆን፤ ሌላው ቀርቶ ወደ አድዋና አክሱም ስንሄድ እውነት ለመናገር ህዝቡ የሚያሳዝን ህዝብ ነው። ምክንያቱም ሰፊው የትግራይ ህዝብ አንደኛ፣ በአሁን ጊዜ በዚህ ዘመን ለእግሩ እንኳን ጫማ የሌለው ህዝብ ነው። ልብስ በረከሰበት በዚህ ወቅት ልብስ እንኳን መልበስ ያልቻለ ህዝብ ነው። ይህ ደግሞ ጥቂት የህወሓት አመራሮችና አባላት ገንዝቡንም ለራሳቸው፤ አገሩንም የራሳቸው አድርገው እንደያዙት የሚያሳይ እንደሆነም አመልክተዋል
“በተጨባጭ እንዳየሁት የትግራይ ህዝብ መፈናፈኛ ስላጣ ዝም ብሏል። ለዚህ ደግሞ ወደ ዛላንበሳ በሄድኩበት ወቅት ያነጋገርኳቸው አንድ አዛውንት ያጫወቱኝ ትልቅ አብነት ነው። እኚህ አዛውንት እንዳጫወቱኝ፣ እዚሁ ተወልጄ የኖርኩ ነኝ፤ ነገር ግን ስርዓቱ ወይም የህወሓት አስተዳደር ለእኔም ሆነ ለአካባቢው ምንም ያደረገው ነገር ስለሌለ አብዛኛው በችግር ውስጥ ያለ፤ በዕድሜ መግፋት ምክንያት ከቤት የማትወጣው ባለቤቴም ሆነች እኔም በቤተ ክርስቲያን ዕርዳታ ኑሮዬን እየገፋሁ የምንኖር ህዝቦች ነን ነበር ያሉኝ። በህወሓት አገዛዝ ምክንያትም በርካታ ወጣቶች ከአገር ለመውጣትና ለመሰደድ ስለመብቃታቸውም ነው ያጫወቱኝ። “
Filed in: Amharic