>

ትግራይ ውስጥ ለሚፈጸመው የመብት ጥሰት መንግስት ኃላፊነት አለበት!(ያሬድ ሀይለማርያም)

ትግራይ ውስጥ ለሚፈጸመው የመብት ጥሰት መንግስት ኃላፊነት አለበት!

ያሬድ ሀይለማርያም

ትግራይ ክልል ውስጥ የተቃዋሚ ፖርቲዎች አመራር አባላት ላይ እና የተቃውሞ ሰልፍ በሚያካሂዱ ዜጎች ላይ ህውኃት እየፈጸመ ያለውን ከፍተኛ የመብት ጥሰት ማስቆም የፌዴራል መንግስት ኃላፊነት ነው። ህውኃት በመብት ጥሰት አለም ያወቀው ድርጅት ስለሆነ ለህውሃት ጥሪ ማድረግ ፋይዳ አይኖረውም ይሆናል። መንግስት ግን ልክ በሌሎች የአገሪቱ ክልሎች ለሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂ እንደሚሆነው ሁሉ በትግራይም ሕዝብ ላይ በክልሉ መንግስት ለሚፈጸመው የመብት ጥሰት ቀጥተኛ ኃላፊነት በመውሰድ የንጹሃን ዜጎችን ህይወት የቀጠፉ እና የመብት ጥሰት የፈጸሙ ባለስልጣናትን ተጠያቂ ማድረግ አለበት።
ትግራይ ውስጥ የሚፈጸም የመብት ጥሰት በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ እንደተፈጸመ ነው የሚቆጠረው። የፌደራል መንግስቱ ከህውኃት ጋር ያለው ጥሩ ያልሆነ ግንኙነት እና በክልሉ ውስጥ ያለው ጣልቃ የመግባት አቅም ከተጠያቂነት አያድነውም። የትግራይን ሕዝብ ከአፈና መታደግ እንደ ሀገር የመንግሥት ኃላፊነት ነው። በሕገ መንግስቱ እና በአለም አቀፍ ሕጎች የተደነገጉትን የሰብዓዊ መብት ግዴታዎች በአገሪቱ ግዛት ውስጥ የማክበርም ሆነ የማስከበር ኃላፊነት በዋናነት የሚወድቀው በፌደራል መንግስቱ ላይ ነው።
Filed in: Amharic