>
5:14 pm - Friday April 20, 6429

የቀድሞውን መሪ ኮ/ል መንግስቱን "ይቅርታ አርገንላቸው ወደሀገራቸው ቢገቡስ?" (የቀድሞ ጦር ሰራዊት)

የቀድሞውን መሪ ኮ/ል መንግስቱን “ይቅርታ አርገንላቸው ወደሀገራቸው ቢገቡስ?”

የቀድሞ ጦር ሰራዊት
  🛑 ” እኔም ሆንኩ በመንግሥት ሥልጣን ላይ የነበሩ ጓዶቼ በዘረፋ አንታማም:: ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው:: የኢትዮጵያ ሕዝብ ይመሰክርልናል:: “
ግንቦት 13 ቀን 1983 ዓ.ም የዛሬ 27 የሆነዉ እንዲህ ነው ፤ ግንቦት 10 ቀን 1983 ዓ.ም ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማሪያም በመኖራያ ቤታቸው ለከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸው የእራት ግብዣ አደረጉ ፤ ግብዣው ሲጠናቀቅ ፕሬዘዳንቱ ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ ሁሉንም ተጋባዥ እንግዶች እበራፋቸው ላይ በመሆን አንድ ባንድ እየጨበጡ ሸኙዋቸው ።
ማክሰኛ ግንቦት 13 የፕሬዘዳንቱ ልዮ ረዳት ሻምበል መንግስቱ ፤ ብላቴ ማሰልጠኛ ጣቢያ ደርሶ ከዚያም ወደ አስመራ ደርሶ መልስ የሚበቃ ነዳጅ የሞላ አንድ ዳሽ 5 አውሮፓላን እንዲዘጋጅ ትእዛዝ አስተላለፋ ። ፕሬዘዳንቱ ከተመረጡ አጃቢዋች እንደዚሁም ከሶስተኛ ክፍለጦር የመጣና የቅርብ አጃቢያቸው ከነበረው ከሻንበል ደመቀ ባንጃው ጋር በመሆን በኮ/ል ተስፋዬ መሪነት ቦሌ አውሮፓላን ማረፊያ በመድረስ ተዘጋጅታ ትጠብቅ ከነበረችው አውሮፓላን ተሳፈሩ ። ግንቦት 13 ቀን 1983 ፕሬዘዳንት መንግስቱ የ 17 አመት ስልጣናቸውን ለቀው ወደ ዚንባቡዌ አመሩ ።
ፕሬዘደንት መንግስቱ ከሃገር ከወጡ በኋላ ተገንጣይ እና አስገንጣይ ወንበዴዎች በእሳቸው ላይ በሰፊው ያስነገሩት ወሬ የሃገር ሀብት ዘርፈው እንደሸሹ ነው ፤ በወቅቱ በሚታተሙ ጋዜጦች እና መጽሔቶች እንዲሁም በመፅሐፉም በማሳተም የሐሰት ወሬ በሰፊው ተነግሯል ፤ እውነታው ግን በኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማሪያም እንዲህ ይነገራል ።
” ከኢትዮጵያ ስወጣ አደለም ገንዘብ ልይዝ ቀርቶ … ከፈለግሽ አሳይሻለሁ ይዤ የወጣሁትን:: በትረ መኮንኔንና የደንብ ልብስ ላይ የደረብኩትን የሚሊታሪ ጃኬት ብቻ ነው ይዤ የወጣሁት:: ከኢትዮጵያ ስወጣ ብቻዬን አይደለም የወጣሁት:: አብረውኝ የነበሩ ሰዎች ገንዘብ ጭኜ ወጥቼ እንደሆነ መመስከር ይችላሉ:: ራቁቴን ነው የወጣሁት:: የገንዘብ ሰው ብሆን ኖሮ ያንን በመሰለ ቀውጢ ጊዜ ሳይሆን 17 ዓመት በስልጣን ላይ በነበርኩበት ወቅት የፈለገኝን ማድረግ እችል ነበር:: ሀገሬን ለመልቀቅ ከመገደዴ ጥቂት ሳምንታት በፊት የኩዌት መንግስት በስሜ ለግሌ የላከውን 20 ሚሊዮን ዶላር ትቼ ነው የወጣሁት::
ከዚያ ጥቂት ዓመታት ቀደም ሲል የሊቢያው ኮሎኔል ጋዳፊ አሁንም በስሜ የላከውን 150 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አድርጌ ላገር ግንባታ ውሏል:: እኔ ለአገሬ ገንዘብ አምጪ እንጂ ገንዘብ ዘራፊ አይደለሁም:: …..እኔም ሆንኩ በመንግሥት ሥልጣን ላይ የነበሩ ጓዶቼ በዘረፋ አንታማም:: ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው:: የኢትዮጵያ ሕዝብ ይመሰክርልናል:: ” በማለት ኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማሪያም በራሳቸው ላይ ምስክርነት ሰጥተዋል ።
እርግጥ ነው በኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማሪያም የስልጣን ዘመን የተፈጸመ ስህተት አልነበረም ፣ እሳቸው እና በወቅቱ የነበሩት የመንግስት ባለስልጣናት የፈጸሙት በደል የለም ለማለት አይቻልም ። ነገር ግን በጋራ ይሁን በተናጥል ያጠፉት ጥፋት እንዳለ ሆኖ እጅግ በጣም የሚደነቅ እና አንድአንዴም ከስህተታቸው በላይ ከፍ ብሎ ታሪካ ሁሌም በበጎ የሚዘክራቸው መልካም ስራዎችን ሰርተዋል !  አዲሱ  ዶ/ር አብይ አህመድ  የቀድሞውን መሪ ኮ/ል መንግስቱን “ይቅርታ አርገንላቸው ወደሀገራቸው ይግቡ ” የሚል ሀሳብ መናገራቸውን የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። የነገውን ማን ያውቃል ?!
ኮሎኔል መንግቱ ሐይለማርያም በብዙ እንደሚነገረው እንደ ጨካኝና ጨፍጫፊነታቸው ለሀገር የሰሯቸው ብዙ ጥሩ ነገሮች አሉ :-
•   ሰፊውን የአገሪቱን ገበሬ ከጭሰኝነት ነጻ በማውጣት ባለመሬት በማድረጋቸው ይወደሳሉ
• አንድ ዓመት በሆነ ግዜ ውስጥ ብቻ ወደ 4 ሚሊዮን የሚጠጋ የሀገሪቱን ህዝብ ከመሀይምነት በማላቀቅ በሀገሪቱ የወቅቱ
የትምህርት ሁኔታ ላይ አሻራ ጥለው ማለፍ የቻሉ መሪ ናቸው።
• በሀገሪቱ ላለው የእምነት እኩልነት በተለይም በሁለቱ በርካታ ተከታዮች ባላቸው የክርስትና እና የእስልምና እምነቶች መካከል ላለው መከባበር እና መቻቻል የማይናቅ ሚና ተጫውተዋል።
• ደሞዛቸውና ጥቅማጥቅማቸውን ሳይቀር ለአገር እና የህዝብ አገልግሎት እንዲውል በማሰብ ለመንግስት ገቢ በማድረግ አገራቸውን በፍጹም ንጽህና እንዳገለገሉ ይነገራል።
• በአገራቸው አንድነት ላይ ለሰከንድ እንኳ የማይደራደሩ መሪ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል። በ17 ዓመት የስልጣን ዘመናቸው በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ተነስተው ከነበሩ የተገንጣይ አስተሳሰብ አራማጆች ጋር በመፋለም አሳልፈዋል።
• ኢትዮጲያን ኢንደስትራላዊት ሀገር ለማድረግ በርካታ ፋብሪካዎችን በየቦታው እንዳቋቋሙ  ይታወቃል።
• ወላጅ አልባ ህጻናት ሜዳ ላይ እንዳይወድቁ በማሰብ ከአፍሪካ ትልቁን አሳዳጊ ያጡ ህጻናት ተንከባካቢ ድርጅት መስርተው ለሺህዎች አባት መሆን ችለዋል።
• የህዝቡን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት በ1 ብር በ2 ብር ሂሳብ ቤቶችን ለደሀው ህብረተሰብ እንዲሰጥ አድርገዋል ። መጠነኛ አቅም ላለው ሰው ደግሞ መሬት በነጻ ከነባንክ ብድሩ አመቻችተዋል ።
•ከዘረኝነት ነጻ ሆነው ሁሉም ኢትዮጲያዊ በእኩል አይንና እንዳስተዳደሩ ይነገራል ።
• በሙስና ላይ የነበራቸው አቋም ከፍተኛ በመሆኑ በሥልጣን ዘመናቸው ሙሰኞችን ነቅተው በማደን ይታወቃሉ።
Filed in: Amharic