>

ያልተዘመረለት ዋርካ... (አትክልት አሰፋ)

ያልተዘመረለት ዋርካ…

አትክልት አሰፋ

ኢንተርኔት ትጠቀማላችሁ?… ጋዜጠኛ ኢንተርኔት ተጠቅሞ መዝገብ አለበት… ኢንተርኔት…! …. ጋሽ ክፍሌ አልቻለም እናም ተነሳ … አሁን ኢንተርኔት የእኛ ዋነኛ ጉዳይ አይደለም። እኛ አፍሪካውያን ጋዜጠኞች ያለብን ችግር እሱ አይደለም። እሱ ቅንጦት ነው።  በነፃነት መጻፍ የማንችለው እናንተ በምትለግሷቸው አምባገነኖች ምክንያት ነው። ጋዜጠኞች እየታሰሩ.. እየተገደሉ እየተሰቃዩ ነው ያሉት…
—-
– በዚህ ሰው ብርታት የነፃ ፕሬስ ማህበር አንደገና አንሰራርቷል
– በዚህ ሰው ቆራጥ መሪነት ህወሓት/ኢህአዴግ ከአመታት በኋላ ሳትወድ በግድ ለነጻ ፕሬስ ማህበር ፍቃድ ሰጥታለች
– በጋሽ ክፍሌ ትጋት የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የአለም አቀፍ ተቋማት ዋና አባል ሆነዋል CPJ, IFJ
– ሌላም አለ… የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ማህበር ከ100 በላይ አባል ማህበራት ያሉት IFEX አባል ሆኗል
– በአንድ ጊዜ የታሰሩ 27 ጋዜጠኞች በአለማቀፍ ተቋማት እንዲጎበኙ፣ እንዲረዱ፣  እንዲፈቱም ጭምር በሙግት የተሳካለት እሱ ጋሽ ክፍሌ ነበር።
– የሚገርመው እሱም ሶስት ወር ሲታሰር ደግሞም ሲፈታ እንደገና ሲታሰር… በሚያገኛት  ቀዳዳ በመጠቀም ነበር ይህን የሚያደርገው።
ጋሽ ክፍሌ የነጻው ፕሬስ አንሰራርቶ ቆሞ እንዲሄድ ካደረጉ በርታዎች ሁሉ ራስ ነው። ከብዙ በጥቂቱ ይሄው ነው።
2001/2002 አካባቢ ነው። ኬንያ በአንድ ሆቴል በአለም ታላላቅ የሚባሉ ጋዜጠኞች ሴሚናር ላይ ናቸው። ስመጥር የተባሉ አለማቀፍ የዜና አውታሮች ሁሉ ዝነኛ የተባሉ ጋዜጠኞች ልከዋል። አንዲት አሜሪካዊት በሙያው እጅግ የተካነች ሴት ሴሚናሩን እየሰጠች ነው። ኢንተርኔት ትጠቀማላችሁ?… ጋዜጠኛ ኢንተርኔት ተጠቅሞ መዝገብ አለበት… ኢንተርኔት…። ጋሽ ክፍሌ አልቻለም እናም ተነሳ አናም አለ… አሁን ኢንተርኔት የእኛ ዋነኛ ጉዳይ አይደለም። እኛ አፍሪካውያን ጋዜጠኞች ያለብን ችግር እሱ አይደለም። እሱ ቅንጦት ነው።  በነፃነት መጻፍ የማንችለው እናንተ በምትለግሷቸው አምባገነኖች ምክንያት ነው። ጋዜጠኞች እየታሰሩ.. እየተገደሉ እየተሰቃዩ ነው ያሉት… ብቻ ብዙ መናገር ያለበትን ብሎ ዝም አለ። አዳራሽ በጭብጨባ አስተጋባ። ሴትየዋ ደንግጣ ቀረች። ዋና አስተባባሪው  ሳምቡሬ የሚባል ኬንያዊ ተነስቶ ሚስተር ክፍሌ የኛ የአፍሪካውያን ጋዜጠኞች ጀግና ነው። የምናከብረው ጀግኖችን ነው… ማውራት አልቻለም በጭብጨባ ተቋረጠ..  እናም ይህንን የአፍሪካውያን ጋዜጠኞች ጀግና እንለዋለን…።
Filed in: Amharic