>

የጀግናው ጀነራል ታሪክ ዓባይን በጭልፋ!!! (ታዬ ቦጋለ አረጋ)

የጀግናው ጀነራል ታሪክ ዓባይን በጭልፋ!!!

ታዬ ቦጋለ አረጋ
*   እኛ “ኦሮሞዎች ተበድለናል” ለሚሉት አክራሪዎች ጄነራሉ ምላሽ አላቸው:-
  መነሻ
ነጌሌ ቦረና ከገዳ እምብርት ሥፍራዎች በግምባር ቀደምነት የምትሰለፍ ሲሆን፤ በርካታ ጀግኖችንና የአመራር ጠቢባንን አፍርታለች።
ከእነዚህም መሀከል በአ/አ/ዩ ኤፍ/ቢ/ኢ ግቢ ውስጥ የመታወሻ ህንፃ በስማቸው ከተሰየመላቸው፦ የምጣኔ ሀብት ጠቢብ ዶክተር እሸቱ ጮሌ ጀምሮ =  በወያኔ ምሥጢራዊ አገዳደል ዘዴ የግፍ ሰለባ እስከሆነው ወልደማርያም ዋቆ ድረስ መጥቀስ ይቻላል። የአብዬ ጎዳና ቱኒ እና የኦብ ኢሉ ባነታ ታላቅነትም ሊወሳ ይችላል። አያሌ ተመራማሪዎች፣ የጦር መሪዎች፣ የሙዚቃ ሰዎች፣ ጠበብት… በሀገር ግንባታ ታላቅ ድርሻ አላቸው።
*
ነጌሌ ቦረና ከምንም በላይ በፍቅር ምድርነት የምትታወቅና ፍቅርን የምታመነጭ እንድትሆን ያስቻላት የመጀመሪያው ምሥጢር = የቦረና እና የጉጂ ገዳ ስርአቶች የፈጠሩት ታላቅ እሳቤ ሲሆን =  ከዚሁ መሳ ለመሳ የከተማዋ ነዋሪ የዘመናት የፍቅር ህብር ቀዳሚው ነው።
*
እለታዊ ቁምነገር
*
ወያኔ በአንድም ጦር ሜዳ ፊትለፊት ልትገጥማቸው ከማይዳዳት የኢትዮጵያ ሠራዊት የቁርጥ ቀን ልጆች ታንከኛውን በመምራት ጠላትን ድባቅ የሚመቱት ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ =  ቦረና ካፈራቻቸው ፈርጦች መሀከል በቀዳሚው ረድፍ  ይሰለፋሉ።
አባታቸው አባባ ጨመዳ በነጌሌ ቦረና ከተማ በወቅቱ አቻ የማይገኝላቸው ቁንጮ ገበሬ እንደነበሩ ነጌሌ ትመሰክራለች። ጀግና ጀግናን መውለዱ የሚጠበቅ ነውና እኚህን ትንታግ ለኢትዮጵያ አበረከቱ።
ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ፦ ዛሬም በየመድረኩና በሄዱበት ሥፍራ ሁሉ ኢትዮጵያዊነትን ከማድመቅ ለአፍታ አይቦዝኑም።
(ማስተያያ፦ ከአሜሪካውያን መሀከል የትመጣቸው የሚፃፍ በርካቶች ሲሆኑ ሁሉም ያለልዩነት የሚያስቀድሙት አሜሪካን ነው። ሀገራቸውን ለአፍታ ከአንደበታቸው አይነጥሏትም።
ይህንን ራሱን አስችለን እንመጣበታለን።)
*
አንዳንድ እውነታዎች፦
1. የኢትዮጵያ ባጠቃላይና የነጌሌ ቦረና ዕንቁ ናቸው።
2. በትምህርታቸው የላቁ ተማሪዎች ተመርጠው ይማሩበት በነበረው የበዕደማርያም ትምህርት ቤት Lab School ; AAU ተማሪ ነበሩ።
3. በስመ ጥር  ወታደራዊ አካዳሚ = ሐረር አካዳሚ በመኮንንነት ተመርቀዋል።
4.  በአሜሪካው ‘ፎርትኖክስ እና በራሺያው ቬስትራንፊልድ አካዳሚ የሚሰጡ ትምርቶችን በስኬት አጠናቀዋል።
5. ለተወሰነ ጊዜ የበረራ ደህንነት ሠራተኛ ሆነው አገልግለዋል።
6. በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገሉ ሲሆን የአዋሽ አርባ ሜካናይዝድ ማሠልጠኛ ኃላፊ የነበሩ መሆናቸውን መጥቀስ ይበቃል።
7. በምሥራቁ ጦር ግንባርና ለረጂም ጊዜ በሰሜኑ  የኢትዮጵያ ክፍል በበርካታ ዐውደ ውጊያዎች የላቀ የአመራር ብቃታቸውንና ጀግንነታቸውን አስመስክረዋል።
8. በዝነኛውና ተወርዋሪው “ሰንጥቅ ሜካናይዝድ ብርጌድ’ አደራጅነትና አዛዥነት ለዝርዝር የሚያታክት ገድል ፈፅመዋል። ለአኩሪ ተግባራቸውም የላቀ የጦር ሜዳ ኒሻን/ ሜዳሊያ በክብር ተሸልመዋል።
9.  ለእናት ሀገራቸው ኢትዮጵያ  ክብርና አንድነት በጦር ሜዳ ውሎ ደጋግመው ቆስለዋል። በሞት ጥላ ስር አልፈዋል። ዛሬም በጀግንነት ለሀገር ይተጋሉ።
10.  በአመራር ችሎታቸውና በጀግንነታቸው በፈጣን የማእረግ እድገት(Fast acceleration) በኢትዮጵያ  ሠራዊት በለጋ እድሚያቸው ጀነራል ማእረግ መድረስ ችለዋል።
10. በግንቦት 8/1981 መፈንቅለ መንግስት  ተጠርጥረው ያለ አግባብ ሁለት ዓመታትን በእስር አሳልፈዋል።
11. በወያኔ መንግሥት  ያለ ክስና ፍርድ (የታወቀ ነው)
ሰባት ወራት በእስር አሳልፈዋል።
12. የህብረተሰባዊት ኢትዮጵያ የላቀ የጀግና ሜዳይ ተሸላሚ  ናቸው።
13. “የጦር ሜዳ ውሎ ከምሥራቅ እስከ ሰሜን” የሚል አውቶባዮግራፊ ፅፈው ለህትመት አብቅተዋል።
14. ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላቸውና በቀላሉ ተግባቢ የማይኮፈሱ ጀግና ናቸው።
ቆፍጣናው ወታደራዊ አለባበስም ሆነ ሽክ ያለ አለባበስ ግርማ ሞገሣቸውን የሚያጎላ ሲሆን ከወታደራዊ ዩኒፎርም አንዱ (ፋቲግ) እንዲህ ላህይ ያሳምራል።
እኛ “ኦሮሞዎች ተበድለናል” ለሚሉት ጄነራሉ ምላሽ አላቸው:-
(ከተለያዩ ምንጮችና ከክምችት ክፍላችን)
*
ለጀግኖቻችን ክብር እንስጥ!
ለትውልዱ የመልካም ታሪካችንን ገፆች እናካፍል።
ዛሬም ከማረሚያ ቤቶች ጀምሮ በተለያዩ መድረኮች ስለስነምግባርና አብሮነት ልምዳቸውን ያካፍላሉ።
ረጂም እድሜና ጤናን እንመኝልዎታለን።
Filed in: Amharic