>

የግብፅ ሴራ በሱዳን፤  "ጥቋቁሮቹ በጎች!!!" (አቤል ዘመነ)

የግብፅ ሴራ በሱዳን፤  “ጥቋቁሮቹ በጎች!!!”

አቤል ዘመነ
ኢትዮጵያ ለሱዳን የግድቡን ቅድመ የውሀ ሙሌት በተመለከተ ትስማማ ዘንድ ያቀረበችውን ሀሳብ ስዳን አልፈርምም አልስማማ ማለቱዋን ሰምተናል።
የጠበቁት ነው ሱዳን በሁለት ስሌት የምትበላ አገር ናት የግብፅ ፖለቲካ ሲዳካም ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሲዳከም የግብፅ የመጫወቻዋ ዋና ቀመር ሆኖ ቆይቶዋል።
በተለይም ኢትዮየያ ከለውጥ ወዲህ በምድሩዋ የፖለቲካው ሁኔታ ለተወሰኑ ወራት ወደ አንድ ጠንካራ ሀሳብ ወደመምጣት መንገድ ጀምሮ ነበር ይህም ለኢትዮጵያ ትልቅ ተቀባይነት እና የቀጠናውን ተሰሚነት ጨምሮላት ነበር ።
ይህ የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ስኬት በአይነቁራኛ የምታየው ግብፅ በብዙ መንገዶች ለማደናቀፍ ስትጥር ቆይታለች።
ግብፅ ስኬታማ አገር ያደረጋት የፖለቲከኞቹዋ የፖርቲወቹዋ አቋም በአገራቸው ጉዳይ አንድ መሆን ነው ።
በሀሳብ ቢለያዩም በውይይት እርስ በርስ ቢፋተጉም በግብፅ አገራቸው ግን ሁሉም አንድ ናቸው ። በዚህም በአለም አቀፍ አገራቸው ትሰማ ዘንድ ትልቅ ድጋፍ ያደርጋሉ። የግብፅ ፖለቲከኞች ከፕረዘዳንት አልሲሲ ጋር ከባድ አተካራ ውስጥ ናቸው ሲበዛ የሚቃወሙ አሉ ሆኖም በአገራቸው ግብፅ ጉዳይ ግን አንዲትም ስንዝር ልዩነት የላቸውም።
ኢትዮጵያ ግን በዚህ አልታደለችም ፖለቲከኞቹዋ ከአለም የተለዩ ናቸው በሀሳብ መለያየት እንደ ግብፅ ፖርቲወች እና ፖለቲከኞች አይነት ያደገ አመለካከት የላቸውም በገንዘብ አገራቸውን ይሸጡዋታል ከአገራቸው ተቃርኖ ከጠላት አገር ጋር ይቆማሉ በሀሳብ ልዩነት ከማመን ይልቅ አገራቸውን ለዚህ እርድ የሰዋታል። በዚህም የፈረኦን አገር ግብፅ ለኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች “ጥቋቁሮቹ በጎች” ሲሉ ይጠሩዋቸዋል።
ግብፃውያን በብዙ ሀሳብ ቢለያዩ የቱንም ያህል መንግስታቸው ጋር ችግር ይኑር አገራቸውን ግብፅ እንደ ኢትዮጵያውያን አሳልፈው አይሸጡም ። ግብፅ ለነሱ ግብፅ ናት በገንዘብም በምንም አይሸጡዋትም። አገራቸው ግብፅም ለዚህ ምህረት የላትም ግብፅን ልካድ ያለ ዜጋዋ ከተገኘ በበረሀማው አሸዋ እስከወዲያኛው ይሸኛል ።ግብፅን በግብፃውያን መክዳት እንደ ቀላል ከቶም አይታይም።
ኢትዮጵያውያን በዚህ ትልቅ ከአለም ህዝብ የተለየ አመለካከት አላቸው በዚህም ሁዋላቀርነት ስም ያሰጠን ዋናው ችግራችን ሆኖዋል።
አብይን መጥላት በፖለቲካ መከራከር መወያየት መጨቃጨቀ ለለውጥ መጣር በአገራችን ይቻላል ሆኖም ይህን ከአገራችን በላይ ማስበለጥ በጣም ፀያፍ ሆኖ ይታየኛል። ይህም ደካማ ህግ እና ጠንካራ ነገር ካለመኖር ጋር የመጣ ነው ። የቱንም ያህል በአለም ዲሞክራሲ አላት የምትባለው አገር አሜሪካ ዜጎቹዋ የአገር ክህደት ከፈፀሙ የሚጠብቃቸው ቅጣት አደገኛ ነው ከዚህ ቀደም ለሩሲያ የአገሩን አሜሪካ ሚስጥር ሰቶ ያን ዜጋ ለመያዝ አገሪቱ እስከምን ድረስ እንደሄደች የምናስታውሰው ነው ። በሀሳብ በምንም መከራከር መፋተግ መጨቃጨቅ መሰዳደብ የተለመደ ነው ሆኖም አሜሪካዊ አገሩን ለሌላ አሳልፎ መስጠት ከቶም አይደፍርም።
ጥቋቁር በጎች ብላ የምትጠራን ግብፅ በሰሞኑ ፓርቲወቹዋ በይፋ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞቹን በገንዘብ እንደገዙ እና ከዛም አልፎ ሰነድ የፈረሙ እንዳሉ እየገለፁ ነው ። የሱዳን መልስ ብዙ ትርጉም አለው ።
የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ፖርቲወች የቤታቸውን ጓዳ እንደ ግብፃውያን በአገራቸው ጓዳ አይዙም ይልቁንም አገራቸውን ወደውጭ አሳልፉው ችግሩዋን ሁሉን ይዘረግፋሉ ። በራሳቸው አገር በአንድነት ቢቆሙ የአፍሪካ ሁለተኛ ህዝብ ቁጥር ያላት አገራቸው ተሰሚነቱዋ ከፍተኛ በሆነ ነበር ።
ከፕረዘዳንት አልሲሲ ጋር አለመስማማት ለግብፅ ፖለቲከኞች ፖለቲካ ነው ከሱ ጋር አለመስማማታቸው ግን አንድም ቀን በአገራቸው አቋም ልዩነት የለም ግብፅ ግብፅ ናት ። ለኢትዮጵያውያን ፓርቲወች እና ፖለቲከኞች ደግሞ ሁዋላ ቀርነት ስላለ ከአብይ መንግስት ጋር አለመስማማት አገራቸውን አሳልፎ እስከመስጠት የደረሰ ከአለም አገራት ዜጎች የተለየ ትክክለኛም ጥቋቁር በግነት ይታይባቸዋል።
በምድር ላይ አስገራሚ ዜጎች በፖለቲካ ልዩነት አገራቸውን ለእርድ ለጥላቻ የሚያቀርቡ ።
This is sad መቸ ይሆን መለወጥ የሚቻለው አይታወቅም። የግብፅ ፖለቲከኞች በልጠዋችሁ ሲያንጠባጥቡዋችሁ እና ሲያንቋሽሹዋችሁ ከአገራችሁ ጎን አለመቆማችሁ እጅግ ያሳፍራል። ተመልከቱዋቸው የግብፅን ፖለቲከኞች ፓርቲወች ከፕረዘዳንቱ ጋ ችግር ቢኖር በሀሳብ ቢለያዩም እንኩዋን በአለም አደባባይ በአለም የዜና አውታሮች እየቀረቡ አገራቸው ግብፅ የዲፕሎማሲ የበላይነት እንድታገኝ ሲያደርጉ።
እናንተ ግን
ይቅር ብቻ
አምናለሁ ሱዳንም አትፈርም ግብፅም ጫና ትፍጠር አልሲሲ ፖለቲከኞቹን ፓርቲወቹን ወዘተ ተጠቅሞ ጫና ያሳድር አብይ ብቻውን እንኩዋን ቢሆን ተስፋ አለኝ አሁን የወሰደውን አቋም ይዞ ግድቡ ሙሌት እንደሚጀምር ።
እንዴት በዚህ ጉዳይ ከአብይ ጋር አለመቆማችሁ ለትውልድ እና ለአገራችሁ ያላችሁን ንቀት ያለመሰልጠን ችግር ያሳያል ።ቢያንስ ከግብፃውያን አትማሩም ሰው እኮ ከጠላቱም ይማራል ስንት ከአልሲሲ ጋር ትንቅንቅ ውስጥ ያሉ የግብፅ ፖለቲከኞች በአገራቸው ጉዳይ አንድ ሆነው ለተከታታት ስድስት ቀናት መከሩ በአገራቸው ጉዳይ ልዩነት የለም ። እናንተ ግን ብቻውን አብይን ተዋችሁት ሸም አይዛችሁም። እንዴት ቢያንስ በህብረት አንድ አቋም አትይዙም “የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲወች በጋራ ያወጡት መግለጫ በአባይ ግድብ ዘሪያ ከአገራቸው ጎን እንደሚቆሙ እና ግድቡ ከመሞላት የሚያስቆመው አይኖርም ሲሉ ገለፁ ” የሚለው ዜና በግብፅ ዲፕሎማሲ ምን ያክል ተፅኖ እንደሚፈጥር አታውቁም?
Filed in: Amharic