>

" የማይፃፍ ገድል " (ዶ/ር በድሉ ወቅጅራ)

” የማይፃፍ ገድል ” 

ዶ/ር በድሉ ወቅጅራ
.
በንጋት ጀምበር መከራህም ውበት አለው!!!
.
” …. ወጣት ከሆንክ የቀጠፍከው የፅጌሬዳ እንቡጥ እጅህ ላይ ሊፈካ ይችላል ። ወጣት ከሆንክ ልትተክለው ያዘጋጀኸውን የቡርቱካን ችግኝ የበሰለ ፍሬ ልትበላ ትችላለህ ። ……. ወጣት ከሆንክ አለም አይገዛህም ፤ ትገዛዋለህ ። ሕይወት አይበይንህም ፤ ትበይነዋለህ ። ዘመን አይቃኝህም ፤ ትቃኘዋለህ ።
ታዲያ ይህ ሁሉ የሚሆነው የወጣት ልብ ከታደልክ ነው ። የወጣት ልብ ድርና ማጉ ጉጉትና ፍቅር ነው ። ጉጉትና ፍቅር ተዋህደው የሚፈጥሩት ብርሃን ነው ወጣትነት ። ወጣትነት የምትጠልቅ ጀምበር ተቀላቅሎት እንደተዋበ አድማስ ሟች ውበት ሳይሆን ገና ከአድማስ ማሕፀን መውጣት የጀመረች የንጋት ጀምበር የምትነድፈው ብርሃን ነው ። በንጋት ብርሃን ዓለም ሁልጊዜ አዲስ ናት ሕይወትም እንዲሁ ። ተሲአት ላይ ሀሩሩ እስኪያነድህ አመሻሽ ላይ ሸክሙ እስኪያጎብጥህ ድረስ፤ በንጋት ጀምበር መከራህም ውበት አለው ።
.
በቃ ወጣት ከሆንክ ያገጠጠብህ መከራ መሮ ጥርሱ ሳይሆን ለስላሳው ከንፈሩ ቀድሞ ይታይሃል ። …..” ፍቅር ተዋህደው የሚፈጥሩት ብርሃን ነው ወጣትነት ። ወጣትነት የምትጠልቅ ጀምበር ተቀላቅሎት እንደተዋበ አድማስ ሟች ውበት ሳይሆን ገና ከአድማስ ማሕፀን መውጣት የጀመረች የንጋት ጀምበር የምትነድፈው ብርሃን ነው ። በንጋት ብርሃን ዓለም ሁልጊዜ አዲስ ናት ሕይወትም እንዲሁ ። ተሲአት ላይ ሀሩሩ እስኪያነድህ አመሻሽ ላይ ሸክሙ እስኪያጎብጥህ
ድረስ በንጋት ጀምበር መከራህም ውበት አለው ።
.
በቃ ወጣት ከሆንክ ያገጠጠብህ መከራ መሮ ጥርሱ ሳይሆን ለስላሳው ከንፈሩ ቀድሞ ይታይሃል ። …..”
Filed in: Amharic