>
5:13 pm - Monday April 20, 9435

ሕገ መንግሥታዊነትና ምርጫ (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም)

ሕገ መንግሥታዊነትና ምርጫ

 

 

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

 

 

የምንኖረው ኢትዮጵያ በምትባል አገር ነው፤ ከ1923 ዓ.ም. ጀምሮ ቢያንስ አራት ሕገ መንግሥቶችና አንድ የከሸፈ ሕገ መንግሥት አይተናል፤ ይህ ሁሉ የሆነው ሰማንያ ዓመታት በሚያህል ጊዜ ውስጥ ነው፤ በዚሁ ዘመን ውሰጥ ያለፉና የሚኖሩ የሥልጣን ተፎካካሪዎች ዛሬ ስለምርጫና ሕገ መንግሥታዊነት የጦፈ ክርክር እያነሡ አገርንና ሕዝብን የሚያበጣብጥ ውዝግብ የሚፈጠረው ለምንድን ነው? ከተከራካሪዎቹ መሀከል ቢያንስ ሦስት ሕገ መንግሥቶች የማያውቅ ያለ አይመስለኝም፤ ዛሬ በድንገት ሕጋዊነት እንዲህ እየተራቀቀ ከመስከረም 30 በኋላ ይህ ይሆናል ያኛው አይሆንም እየተባለ የሚተነበየው በምን ዓይነት የታሪክ ትንታኔ? በምን ዓይነት የፖሊቲካ ትንታኔ? ወይስ በምን ዓይነት የሕግ አስተሳሰብ ትንታኔ ነው? አንድ የሞተ ባሕር ውስጥ ሆነው ውሀ የሚራጩ ሰዎች ይመስሉኛል፤ በሥልጣን ላይ ያለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዙሪያም ሆነ በተፎካካሪዎች ጎራ የሚጠወልግ እንጂ የሚለመልም አይታይም፡፡

Filed in: Amharic