>

የወያኔ አጨብጫቢዎች የነበሩ...!!! (ኤርሚያስ ቶኩማ)

የወያኔ አጨብጫቢዎች የነበሩ…!!!

ኤርሚያስ ቶኩማ
ልክ የዛሬ 23 ዓመት ሚያዚያ 30 ቀን 1989 ዓ.ም አቶ አሰፋ ማሩ ከቤቱ በሰላም ወጥቶ ወደ ሥራ በመሔድ ላይ እያለ በአዲስ አበባ ሐምሌ 19 የሕዝብ መናፈሸ አካባቢ በጠራራ ጸሐይ በህወሃት ነፍሰ ገዳይ ፖሊሶች የጥይት እሩምታ ሰለባ የሆነ ጀግና ኢትዮጵያዊ ነው።
   አቶ አሰፋ ማሩ በጊዜው በወሎ ክፍለሀገር በላስታ አውራጃ መቄት ወረዳ በ1951ዓ.ም ተወለደ። በመምህርነት ሙያ ከማገልገሉም ባሻገር በሙያ ማህበሩ የአመራር አባል በመሆንም የመምህራንን መብትና ጥቅም ለማስከበር ፣ የትምህርቱን ጥራት ለማስጠበቅ በሚደረገው ትግል በግምባር ቀደምትነት ከሚታገሉት አንዱ ሆኖ ሕይወቱ በግፈኞች እስካለፈበት ዕለት በጽናት ቆሞ ቆይቷል።
   በወቅቱ በነበረው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤም በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት የላቀ ድርሻ አበርክቷል።
በዚህ በኩል ኢመማ ለሙያው ክብር ፣ለትምህርት ጥራትና በእኩልነት መዳረስ፣ በነፃ ለመደራጃት፣ ለሰብአዊ መብቶች መጠበቅ ፣ ለፍትሕና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መስፈን በአጠቃላይ ለአገር ሁለንተናዊ ዕድገት ታግለው እያታገሉ መሰዋዕትነት የከፈሉ በርካታ ጀግኖችን አፍርቷል።
   አቶ ሺመልስ ዘውዴ በህወሃት ፖሊስ ጣቢያ ለአንድ ወር ያህል ታስሮ በነበረበት ጊዜ ለከፋ ብርድ ሕመም በመጋለጡ፣ ሕክምና ባለመግኘቱና በደረሰበት እንግልት ከእስር ከተፈታ በኋላ ወዲያውኑ ሕይወቱ አልፏል። አቶ ከበደ ደስታ በኢመማ ሥር የአባት መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት የነበሩትም ታሰረው ሕይወታቸው እስር ቤት እንዳሉ አልፏል።
   አቶ አወቀ ሙሉጌታ የኢመማ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና በጥንካሬው የምናደንቀው የኢመማን ጽ/ቤት ለተላጣፊ ለአለመስጠት የሙጥኝ እንዳለ አሟሟቱ በግልፅ ሳይታወቅ በመጋቢት ወር 1999 ዓ.ም መንገድ ላይ ሞቶ ተገኝቷል። አቶ ሰርዶ ቶላ፣ አቶ ፈቃዱ ፍርዴና ሌሎችም ኢመማ ካፈራቸውና በዕምነነታቸው ጸንተው ካለፉት ጀግኖች ቀዳሚዎች ናቸው።
   በቅርቡ በሕዳር ወር 2004 ዓ.ም ደግሞ ፍትሕ በሌለበት አገር መኖር ባዶ ሕይወት ነው በማለት ራሱን በጋዝ አንድዶ መስዋዕት የሆነው መምህር የኔ ሰው ገብሬ ቆራጥነቱ ሕዝቡን ያስደመመ ሆኖ አልፏል።
   በነገራችን ላይ እነአሰፋ ማሩ ሲገደሉ የገዳዩ አጋፋሪ የነበሩና ዋነኛ የወያኔ አጨብጫቢዎቹ ዛሬ አይናቸውን በጨው አጥበው ምንም እንደማያውቁ ወያኔን እየተቹ የኢትዮጵያዊነት ጠበቃ ነን በማለት በየሚዲያው ሲንበዛበዙ የሚውሉ መምህር ነን ባዮች የተፈጠሩበት ዘመን ላይ ደርሰናል።
Filed in: Amharic