>

በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ስትራቴጂክ ጠላት ሕወሓት እና ባላሜንጫው  ወይስ የኤርትራ መንግሥት  !? (ቬሮኒካ መላኩ) 

በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ስትራቴጂክ ጠላት ሕወሓት እና ባላሜንጫው  ወይስ የኤርትራ መንግሥት  !?

ቬሮኒካ መላኩ
ብዙው ሰው  ለዘመናዊው  የፖለቲካ ውስብስብ ሴራና ደባ አንጎሉ እንግዳና ድንግል ነው፡፡ፖለቲካ ቋሚ ስትራቴጂም ቋሚ ታክቲክም ይዞ ሁሌ አይጓዝም!!
ትናንት ጠላት የነበረ ዛሬም ጠላት ነው የሚል ስሌት ውጤቱ ዜሮ ነው፡፡ ሁሌም በፖለቲካ ሀይሎች ላይ የማይቀየረው የህዝብና የአገር ዘላቂ ጥቅም ብቻ ነው፡፡ ትናንት ጣሊያን ሁለት ጊዜ የወረረችን ጠላታችን ነበረች ዛሬ ግን በሊቢያ አቋርጠው ባህር ተሻግረው የደከሙ  በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ  ዜጎቻችንን የምታስጠጋና ለአገራችንም የልማት አጋር የሆነች ወዳጃችን ነች፡፡ ፖለቲካ እንደዚህ ውስብስብ  ነው፡፡
ሻቢያ ትናንት ጠላት ነበር ዛሬም ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ከእነ ህውሃትና Covid 86 (ጃዌ)  የበለጠ ጠላት ነው የሚለው ድምዳሜ የሆነ ጊዜ ላይ ግሪስ ጨርሶ ስታክ ካደረገ አንጎል የሚፈልቅ ፎልስ ኮንክሉዥን ነው፡፡
ለምሳሌ የአማራን ህዝብ በየቀኑ ” ነፍጠኛ” እያሉ የሚገድሉት ፡ የሚያስገድሉት ፡” ክልልህ አይደለም ውጣ!” በማለት ቤት ንብረቱን እያቃጠሉ የሚያፈናቅሉት ፡ ወደፊትም መስከረም 30ን ጠብቀው ለመግደል ለማስገደል ለማፈናቀል ሜንጫ ከሚስሉት የኮቪድ 86 ሀይሎች የበለጠ ኢሳያስ ጠላት የሚሆንበት ምንም አሳማኝ ምክንያት የለም፡፡
የአማራ ህዝብ ትናንት በሻቢያ  ከተደረገበት   የበለጠ ዛሬ በእነጃዋርና ደበረፂዮን አቀነባባሪነት የሚደርስበት ግፍ የበለጠ ነው፡፡
አንድ ባሌ ፡ ሐረርጌ ፡አርሲ ፡ወለጋ ጉጅ ገጠር ውስጥ የሚኖር ምንም ፖለቲካ የማይመለከታቸው  የአማራ አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው የሚያስጨንቃቸው ጃዋር ወይም በቀለ ገርባ በሚዲያ ወይም ፌስቡክ ላይ “ምን መርዝ ተናግሮ  ልጆቼ ይጎዱብኝ  ይሆን?” የሚለው እንጅ የሚያሳስበው  ኢሳያስ አፈወርቂ  አይደለም፡፡
በተጨማሪም የትናንቱ የሻቢያ ጠላትነት እንደተጠበቀ ቢያንስ  ዛሬ ሸአቢያ “ወልቃይትና ራያ በጉልበት የተወሰዱ የአማራ መሬቶች ናቸው ፡፡” በማለት አቋሙን የገለፀና በወልቃይትና ሁመራ በኩል ከትግሬ ጋር ሳይሆን ጉርብትናየ ከጎንደር ጋር ነው በማለት ጎንደርን የጎበኘና የፋሲል ስፖርት ክለብን ሁሉ የወዳጅነት ጨዋታ እንድደረግ አስመራ የጋበዘ ሀይል ነው፡፡
ለዚህም ነው ልደቱ አያሌው ” ከኢሳያስ ይለቅ  ጃዋር መሀመድና ደብረፂዮን ይቀርቡኛል”  በማለት የተናገራት  ውጯ  ቼኮላት እንደሰጡት ህፃን በደስታ የምታፍለቀልቅ ውስጧ ግን መርዝ የሆነችን አባባል የሚገዛት የፖለቲካና የእውቀት ደሀ የስሜትና የወሬ ቱጃር የሆነ ብቻ ነው በተረፈ ” ሻቢያ የትናንት አቋሙ  ዛሬ አለ የለም ?” ለሚለው ስነልቡናዊ, ፖለቲካዊ, የጥቅም እንዲሁም የህልውና ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ እየሰጡ በመተንተን የሚያስረዱ ምሁራን ያስፈልጉናል  እንጅ የፊደል ሆሄያትን ብቻ ማንበብና መፃፍ ስለቻለ ፌስቡክ ላይ መጥቶ ሲቸከችክ የሚውል  የፌስቡክ ቀፋይ  አንጎል ምንም ጠብ የሚል ነገር አይኖርም፡ በዚህም መሰረት ሻቢያ፡ እንደፖለቲካ ሀይልነቱ እንደ ጥቅሙና እንደህልውናው አሁን እንዳለንበትም ነባራዊ ሁኔታ እንዲሁም የአለምና የአካባቢው የሀይል ሚዛን አሰላለፍ አቅዋሙም ሊለዋወጥ ይችላል በማለት በጥንቃቄ እያሰሉ የአገርንና የህዝብን ጥቅም እያስቀደሙ ፖለቲካን መስራት አዋጭ ነው ::
Filed in: Amharic