>

በኦርቶዶክስ አብያተ ቤተ ክርስቲያናት ብቻ ልዩ የፌዴራል ፖሊሲ ጥበቃ ሀይል ማቆም ለምን አስፈለገ? (አበበ ሀረገወይን)

በኦርቶዶክስ አብያተ ቤተ ክርስቲያናት ብቻ ልዩ የፌዴራል ፖሊሲ ጥበቃ ሀይል ማቆም ለምን አስፈለገ?

አበበ ሀረገወይን
* ትንኮሳው ፣ ዛቻውና ፣ ብልግናው ተገቢ ነውን?
በዛሬው ባርበኞች ቀን መንገድ ላይ ብዙ ሰው ስላልነበረ ፣ ማስኬን አጥልቄ የእግር መንገድ ጀመርኩ ። አፍሪካ ሕብረት ባሻገር ባለው ሚካኤል ቤተ ክርሰቲያን ካለው የገመድ ገደብ ውጭ ሆኜ አማትቤና የሕሊና ጸሎት አድርሼ እታች የሚታየውን ፎተግፍ በሴል ፎኔ ሳነሳ ፣ በሩ ላይ የነበረ የፌደራል ፖሊሲ ሚስማር የተሰካበት ትልቅ አጠና ወደ ላይ አንስቶ ፣ ደም ለብሶና ደም ጎርሶ ፣ ፎተግራፍ ማንሳት አይቻልም አለኝ። ለምን አልኩት ፣ አይይቻልም! ማለት አይቻልም ነው ፣ ሂድ ከዚህ ብዬሃለሁ አለኝ። መቼም ባገራችን እንኳን በግዜያዊ አዋጅ ሙሉ ስልጣን ተሰቶት ያፈቀደውን ማድረግ ከሚችል ጋር ምንም አቅም ስለ ሌለኝ እያረርኩ መንገዴን ቀጠልኩ።
ቀደም ብሎ አነድ ትልቅ የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን ሳልፍ ምንም የፌደራል ፖሊስ ጥበቃ አልነበረም ፣ በኋላም ያለፎኳቸው ፣ ሁለት መስጊዶች እንዲሁ ምንም የፖሊስ ጥበቃ አላየሁም ። ሌሎች የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያኖች ሁሉ በገመድ ተከበው በፖሊሶች ይጠበቃሉ ። ግራ ያጋባል ። ከጥቂት ቀናት በፊት መካኒሳ አቦ ከሚጠብቁት ፖሊሶች አንዱ የቤተ ክርስያኑን ግምብ ተደግፎ ጥርሱን እየፋቀ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ግምብ ዞር አያለ ግምቡ ላይ ሲተፋ እኔና ሌሎች ሁለት ምእመናን አይተን አማትበን ከማለፍ ሌላ ምንም አቅም እነደ ሌለን አውቀን እየተያየን አዝነን አልፈናል።
የተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ልዩ ጥበቃ የኮሮናን ስርጭት ለመቆጣጠር መሆኑ ግለጽ ነው። ነገር ግን የጠባቂዎች የአማኞችን አላስፈላጊ ንቀትና ማካለብና ፣ በእምነቱ አሰከፊ የሆነ የመትፋትና ፣ ሰላማዊ አማንያንን በዱላ ማስፈራራት ተገቢ ብቻ ሳይሆን ምንም ጊዜያዊ አዋጅ ቢኖር ኢሰብአዊ ነው። ባህላችንም ታሪካችንም ይህን ክፋት አይፈቅዱም ። የተዋህዶ አማንያን ከሌሎች የተለየ ሕገ ወጥነት የላቸውም ። አገር ወዳድና ሕግ አክባሪዎች ናቸው ። ሞኞችም አይደሉም ፣ በትእግስት ይታዘባሉ ። ሳያመረቅዝ መንግስት ይህን ጉዳይ ቢያስብበትና ቢያስተካክል ጥሩ ነው ።
ባለጊዜዎቹ ሰው ቢሆኑ የሚሆነው ሁሉ አይሆንም ነበር።  አንዳቸው ካንዳቸው ቢሻሉም የገዛ ስራቸው ሊያሳፍራቸውና አንገታቸውን ሊያስደፋቸው ይገባ ነበር።  ነገር ግን ጨርሶ የማያስተውሉና የማያመዛዝኑ በመሆናቸው ሁሉም በሚባል ደረጃ ያገኙትን ትንሽ ቀዳዳ ተጠቅመው የዘመናት ጥማቸውን እያረኩ ይገኛሉ።  ይህን ማድረጋቸው ከጊዜያዊ ጀብደኝነትና ታሪክ የማይፍቀው ስህተት ከመፈጸም ውጭ የሚያስገኝላቸው ትርፍ እንደሌለ፣ በአማኙም ሆነ በእምነቱ ላይ የሚያመጡት አንዳች ለውጥ እንደሌለና እንደማይኖር የማያውቁ፣ ለማወቅም ያልተፈጠሩ፣ ባጠቃላይ የሚሰሩትን የማያውቁ ናቸው።  ይህን ሁሉ በማድረጋቸው ስራ የሰሩና ያሰሩ የሚመስላቸው፣ አክሳሪዎችና ራሳቸውም ኪሳራዎች ናቸው።  ምግባራቸው የሚገልጻቸው!!!
አምላካችን ሆይ እባክህን ጥንታዊ ቤትህን የተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችንን ከክፉ ጥቃት ሁሉ ጠብቅልን ። አሜን!!!
Filed in: Amharic