>

የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኮሮና ቫይረስ ወቅት የዜጎችን ቤት ማፍረስ እንዲቆም ጠየቀ!!! (ሕብር ሬዲዮ) 

የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኮሮና ቫይረስ ወቅት የዜጎችን ቤት ማፍረስ እንዲቆም ጠየቀ!!!

 
(ሕብር ሬዲዮ) 
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መደበኛ ባልሆነ መንገድ የቤት ግንባታ መስፋፋት አዲስ አበባን ጨምሮ በብዙ ከተሞች ትልቅ ችግር መሆኑን ጠቁሞ ይህን ችግር አስታኮ በአሁኑ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ህጻናት እና ሴቶችን ጨምሮ ዜጎችን በኃይል ከመኖሪያ ቤት ማስወጣት እንዲቆም ጠየቀ።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ(ዶ/ር) ዛሬ ይፋ እንዳደረጉት አጭር መግለጫ ወረርሽኙን ተከትሎ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት መደበኛ ባይሆኑም ነባር ነዋሪዎችን ከመኖሪያቸው በሃይል ማፈናቀል ለጊዜው እንዲቆም ኮሚሽኑ መጠየቁን በገጻቸው ይፋ አድርገዋል።
የኮሚሽኑ አጭር መግለጫ 
 
‹‹መደበኛ ያልሆነ የመሬት አያያዝ እና የቤት ግንባታ መስፋፋት አዲስ አበባን ጨምሮ በብዙ ከተሞች ትልቅ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ነው፡፡ ሆኖም በአሁኑ #ኮቪድ19 ወቅት ቤተሰቦችን በሃይል ከመኖሪያቸው ማስወጣት ሴቶችና ሕጻናትን ጨምሮ በተለይ ለመብት ጥሰት ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ትልቅ አደጋ አለው፡፡ አዳዲስ መደበኛ ያልሆነ የመሬት አያያዝ እና መደበኛ ያልሆነ የቤት ግንባታን መከላከል ያስፈልጋል። ነገር ግን በዚህ የአስቸካይ ጊዜ ወቅት መደበኛም ባይሆኑም ነባር ነዋሪዎችን ከመኖሪያቸው በሃይል ማስወጣት ለጊዜው እንዲታቀብ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጥሪ ያቀርባል።››
“Informal settlement is a major socio-economic problem in most cities including Addis Ababa. Forced eviction of families during #COVID19 poses great risk for vulnerable people including women and children. While there is a legitimate need to prevent new informal settlements, Ethiopian Human Rights Commission calls for moratorium on forced eviction of existing settlements during the state of emergency period.”
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ በኮልፌ ወረዳ 05 እና ከዚያም ቀደም ብሎ በቦሌ አራብሳ ዜጎች ቀደም ብለው ለዓመታት ሰርተው የኖሩበት ቤት እየፈረሰ ችግር ላይ መውደቃቸውን ማጋለጡ እና የኮልፌው ቤታቸው የፈረሰባቸውን ቀርቦ በማነጋገሩ የፓርቲው መሪ እስክንድር ነጋ ለሰዓታት ታስፎ መፍታቱ ይታወሳል። ፖሊስ ከእስክንድር የወሰደውን የእጁ ስልኩን ሳይመልስ ከፍቶ እየተጠቀመበት መሆኑ መገለጹ ይታወሳል።
ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንታገላለን ሲሉ የኖሩ ግምት የተቃዋሚ መሪዎች የህዝቡ ቤት እየፈረሰ መፈናቀል ላይ ድምጻቸውን ማጥፋታቸው እና የአንዳንዶቹ ደጋፊዎች እስክንድር እና ባልደራሱን ለማጥላላት እንደ ትላንቱ የሀሰት ትግል ቆርጠው መነሳታቸው ዛሬም በማህበራዊ ሚዲያው መነጋገሪያ ሆኗል።
ዳንኤል በቀለ(ዶ/ር) ኮሚሽነር ሆነው ከመሾማቸው በፊት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽኑ የመንግስትን የመብት ጥሰት በማድበስበስ የቀድሞ መሪው   ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሔር ሲወገዙ እንደነበር ይታወሳል።
Filed in: Amharic