>

የሦስት ትውልዶች ዕብደት!!! (ሙሉአለም ገብረመድህን)

የሦስት ትውልዶች ዕብደት!!!

ሙሉአለም ገብረመድህን
1- ‹‹ኢትዮጵያዊነት የሚያስጠላኝ በአማራ ምክንያት ነው!››    መ/ር ገብረኪዳን ደስታ
2- “.. አማርኛ ለመማር ያጠፋሁት ጊዜ ይቆጨኛል!”
ሜ/ጀ ተ/ብርሃን
3r ” ጎጃም ከሚለማ ሲናይ በረሃ ቢለማ ምርጫዬ ነው”
ዶ/ር ጎይቶም ገብረ አናንያ
በአማርኛ ቋንቋ ጭቆና የደረሰበት ጀነራል ይመራው በነበረው ተቋም ውስጥ ዐቢይ አህመድን እና ተመስገን ጥሩነህን  በማባረር በታዜር ገብረእግዚአብሔር እና ብንያም  ተወልደ መተካቱ ይነሳል።
ይህ ሹም ሽረት የልጅነት የአማርኛ ቋንቋ ጭቆናን በስራ ቦታ ለመከላከል ከነበረ  ቢያንስ ዐቢይ አህመድ ትግርኛ ይናገራል።
በርግጥ ጀነራሉ ” በረሀ የገባነው ለኢትዮጵያ ብለን አይደለም” ስላለ ነገሩ ከቋንቋ በላይ ሆኖ እናገኘዋለን።
ተስፋ የማደርገው ዐቢይ ትግርኛ ለመልመድ ያደረገው ድካም እንደማይቆጨው ነው።
*     *     *
ይህ ጥላቻን እንደ ዱላ ቅብብል ከትውልድ ወደ ትውልድ የማስተላለፍ ሚናን የሚገልጽ ምሳሌያዊ አገላለጽ ነገሮችን ወደ ኋላ ለመፈተሸ አስገድዶኛል፡፡ እናም፣ በኔ ግምገማ የጥላቻው መሠረት በሁለቱ ትውልድ (በተክለብርሃንና በዶ/ር ጎይቶም ገብረ አናንያ – ዘጸዓት) ብቻ የሚገደብ ሆኖ አላገኘሁትም፡፡
ሦስተኛ ትውልድም አለበት፡፡ የመምህር ገብረ ኪዳን ትውልድ የጥላቻ ንግግርም ሆነ ጽሁፍ መሠረት እንደሆነ አምናለሁ፡፡ በታሪክ ባለሙያዎች ብያኔ መሠረት  ‹‹ትውልድ ማለት ሃያ ዓመቱን የቆጠረ የህዝብ ስብስብ ማለት ነው››፡፡ በዚህ ብያኔ ልኬት ስንቆጥር ገብረኪዳን ደስታ፣ ተክለብርሃን እና ዘጸዓት የሦስት ትውልድ ውክልና ይይዛሉ፡፡ ምንም እንኳ ገብረኪዳን እና ተክለ ብርሃን የትጥቅ ትግሉ ተሳታፊዎች ቢሆኑም፣ ገብረ ኪዳን ዕድሜው ከፍ ያለ ነበር፡፡ ዋነኛ ሚናውም በቤተክርሲያናት ውስጥ የስለላ መዋቅሮችን መዘርጋትና ሰላዩችን ማሰማራት ነበር፡፡
ዶ/ር አረጋዊ በርኸ ‹‹A Political History of the Tigray People’s Liberation Front (1975-1991): Revolt, Ideology and Mobilisation in Ethiopia›› በሚል ለሦስተኛ ዲግሪ ማሟያ በሰራው ጥናት፤ ትሕነግ  ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ማዳከም የኢትዮጵያን የማዳከሚያ የትግል ስልት አድርጎ እንደተጠቀመበት ይነግረናል፡፡ እ.አ.አ 1979 ኢትዮጵያዊነትን ነቅሎ የትግራይ ብሔርተኝነትን የሚተክል ሥልጠና ለተመረጡ ከየአጥቢያው ለመጡ ካህናት በገብረኪዳን ደስታ አማካኝነት እንደተሰጠ ይተርክልናል::
“TPLF launched a series of conferences or ‘seminars’ for selected parish priests in 1979 to win them over. The underlying motive of the seminars was to isolate the church in Tigrai from the wider Ethiopian church in order to foster Tigraian nationalism along the lines of the TPLF’s strategic objective. Suppressed Tigraian nationalism was invoked to challenge the dominant Ethiopian Orthodox Church. The initial woreda seminars for priests were conducted by an eloquent TPLF fighter, Gebre-Kidan Desta, a graduate of the Theological College at Addis Ababa University.” (page  301)
ጉደኛው የጥላቻ ሰባኪ መምህር ገብረ ኪዳን 1998 ላይ ‹‹የትግራይ ሕዝብና የትምክህተኞች ሴራ ከትላንት እስከ ዛሬ› በሚል ርዕስ ባሳተመው መጽሐፉ ላይ ዳግማዊ አጼ ምኒልክን የሚከስበት መንገድ የጥላቻውን ጥግ ያሳያል፡፡ ‹‹ንጉሥ ምኒልክ ከደርቡሾች ጋርም አፄ ዮሐንስን በጋራ ለመመከት ምስጢራዊ ግንኙነት ፈጥረዋል… አፄ ዮሐንስ በንጉሥ ምኒልክ ሰላዮች እንጅ በደርቡሽ ወታደሮች አልተገደሉም” ( የመጽሐፉን ገጽ 63፣ 66 ይመለከቷል)
 –
ይህ የታሪክን ዕውነታ መካድ ብቻ ሳይሆን ጥላቻ የወለደው ዕብደት ጭምር  ነው። የሥነ ልቦና ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ አራት አይነት የዕብደት ዓይነቶች አሉ። Badmad, Mad-mad, Sad-mad, and Glad- mad ይሰኛሉ።ከእነዚህ ሁሉ የዕብደት ዓይነቶች ውስጥ ትሕነግ የተያዘበት የዕብደት አይነት ለህክምናም አስቸጋሪ የሆነው የመጀመሪያው የዕብደት ዓይነት ነው –”ክፉ ዕብድ” ወይም “መጥፎ ዕብድ” (Badmad) የሚለው ይመስለኛል።
ይህ ዓይነቱ የዕብደት አይነት ከግድያና (ንፁሃን) ሰዎችን ከማሰቃየት (እረፍት ከመንሳትና ከማበሳጨት) ጋር ይያያዛል። በመሆኑም የዚህ ዕብደት ተጠቂዎች ኀይል ሲያገኙ በመግደል፣ ዐቅም ሳይኖራቸው ሲቀር ደግሞ ማበሳጨት መገለጫቸው ነው። የሚያስደስታቸው የንፁሃን ነገር ግድያና ስቃይ ነው፡፡
በሦስት ትውልድ ከፍለን የተመለከትናቸው የትሕነግ ትውልዶች (በባህሪ ደረጃ) በፌዴራል ደረጃ ሥልጣን ላይ እያሉ ንፁሃንን በመግደልና በማሰቃየት ይታወቃሉ። በህዝብ ትግል ተሸንፈው መቀሌ ከተደበቁ በኋላ ደግሞ ክፋት በተሞላበት ንግግራቸው ብዙሃኑን ኢትዮጵያዊ በማበሳጨት ላይ ናቸው። ይህ ከተለከፉበት የዕብደት ዓይነት ጋር በተያያዘ እያደረሱት ላለው አገራዊ ውዥንብር፣ “ዕብድና ዘበናይ የልቡን ይናገራል” ተብሎ ሊታለፍ አይገባውም። ሕዝብ ሊያወግዛቸውና አንቅሮ ሊተፋቸው ይገባል። እነዚህ ዕብዶች ወደ ሥልጣን የመመለስ ዕድል ቢያገኙ ኢትዮጵያን ቄራ እንደሚያስመስሏት አትጠራጠሩ።
ይህ በትውልዶች ቅብብል የተገነባ ስር የሰደደ ጥላቻ፣ ወደ ዕብደት ካደገ ቆይቷል። ገና በ197ዐዎቹ መግቢያ ጀምሮ በትሕነግ የባህል ክፍል ተዘጋጅተው በትግራይ ገጠሮች ሲዘፈኑ የነበሩ ዘፈኖች በሙሉ ይዘታቸው  በትግራይ እና በተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለየ ሁኔታ ደግሞ በትግራይ እና በአማራ መካከል ለሺህ ዘመናት የዘለቀውን የታሪክ   ድልድይ ማፈራረስን ያለመ ነበር።
ለዚህ ነውኮ የሰማንያ ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ መምህር ገብረኪዳን ደስታ “ኢትዮጵያዊነት የሚያስጠላኝ በአማራ ምክንያት ነው” ሲል የተደመጠው። ይህ ንግግሩ “መጥፎ ዕብድ” (Badmad) በሚለው የዕብደት ዓይነት ያሰልፈዋል። የተከታዩች Teklebrhan Woldearegay Ztseat Saveadna Ananya ዕብደትም የዚህ ውርስ ቅጥያ ነው።
Filed in: Amharic