>
5:13 pm - Wednesday April 19, 8643

" አሁን እስክንድርን ፍቱት! እሱን ስታስሩ ብዙ ነገር ትነግሩናላችሁ!!!"  (መስከረም አበራ)

” አሁን እስክንድርን ፍቱት! እሱን ስታስሩ ብዙ ነገር ትነግሩናላችሁ!!!” 

 

 

መስከረም አበራ
* ግለሰብ አከራዮች ተከራይ ከቤት እንዳያስወጡ ጥሩምባ ነፍቶ አዋጅ የሚነግር መንግስት ራሱ ግሬደር ይዞ አንድ መንደር ዶግ አመድ የሚያደርግ፣”ቤት ተቀመጡ” እያለ ቤት የሚያፈርስ ከሆነ ከዚህ በላይ ግብዝነት ከየት ይመጣል? ይህን ሳደርግ ለምን ታየሁ ብሎ ሰውን ማሰርስ ምን የሚሉት ማናለብኝነት ነው?
ለሃገራችን ፖለቲካ መረጋጋት ትልቅ ፋይዳ ካላቸው ወሳኝ ጉዳዮች አንዱ የአዲስ አበባ ጉዳይ ነው። የአዲስ አበባ ጉዳይ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ቀልብ የሚስብ አንገብጋቢ ጉዳይ ቢሆንም በተግባር ትግል እያደረገ ያለው እስክንድር የሚመራው ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ የተባለው ፓርቲ ነው።ይህ ፓርቲ ይዞት የተነሳው “Cause” እጅግ አሳማኝ እንደሆነ አጥብቄ አምናለሁ።በግሌ እንደ አንድ ዜጋ አሁን ስልጣን ላይ ያለውን መንግስት በአንክሮ የማይበት አንዱ ነጥብም በአዲስ አበባ ላይ ያለው ወልካፋ አቋም ነው!
 በባልደራስ ተግባራዊ የትግል ስልቶች ላይ መጠነኛ ልዩነቶች፣አለመርካቶች ቢኖሩኝም የአዲስ አበባን ጉዳይ ነገሬ የሚለው በጠፋ ጊዜ እስክንድር ነጋ እና የትግል አጋሮቹ ከፊት ወጥተው መታገላቸው ብዙ ነገር እንደቀየረ አምናለሁ፤ ለዚህም እንደ አንድ ዜጋ ትልቅ አክብሮት አለኝ።
 በአንፃሩ በሃገራችን የሚንቀሳቀሱ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ ነን የሚሉ ፓርቲዎች በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የያዙት አቋም እጅግ አደናጋሪ ብቻ ሳይሆን ተስፋ  አስቆራጭ  ጭምር  ነው። እነዚህ ፓርቲዎች በአዲስ አበባ ላይ የያዙት ከሞት በበረታ ዝምታ የታጀበው አደናጋሪ አቋም ብቻውን በሚባትለው እስክንድርና ፓርቲው ላይ የመንግስት ጥርስ ንክሻ እንዲጠነክር አድርጓል። ይህ የፖለቲካችን አስከፊ ገፅ ነው!
 የዛሬው የእስክንድር እስር የሃገራችን ፖለቲካ እርምጃ ሁለት ወደፊት ሲባል በድንገት ሶስት ወደ ኋላ መሆኑ የማይለቅ ልክፍቱ እንደሆነ አንድ ማሳያ ነው።
ግለሰብ አከራዮች ተከራይ ከቤት እንዳያስወጡ ጥሩምባ ነፍቶ አዋጅ የሚነግር መንግስት ራሱ ግሬደር ይዞ አንድ መንደር ዶግ አመድ የሚያደርግ፣”ቤት ተቀመጡ” እያለ ቤት የሚያፈርስ ከሆነ ከዚህ በላይ ግብዝነት ከየት ይመጣል? ይህን ሳደርግ ለምን ታየሁ ብሎ ሰውን ማሰርስ ምን የሚሉት ማናለብኝነት ነው?
 ከዛሬው እንዲህ ያለ ሰው ጤፉነት ከተጀመረ ሲውል ሲያድር ምን ሊደረግ ነው?ኢትዮጵያን ብለን ዝም አልን እንጅ ሁሉ ነገር ተስማምቶን መች ሆነና?
አሁን እስክንድርን ፍቱት፣እሱን ስታስሩ ብዙ ነገር ትነግሩናላችሁ -በተለይ የኬኛ ፖለቲካችሁን ከሚስጥር ኪሳችሁ አውጥታችሁ እንዳልጣላችሁ።
Filed in: Amharic