>

በባለጊዜዎቹ  የተጣለውን  አንበሳ  ወደነበረበት ክብር ለመመለስ  አንበሳ ሆኖ መገኘት ነው...!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

በባለጊዜዎቹ  የተጣለውን  አንበሳ  ወደነበረበት ክብር ለመመለስ  አንበሳ ሆኖ መገኘት ነው…!!!

 

አቻምየለህ ታምሩ
ፒኮክ  የፋሽስት ወያኔንና የናዚ ኦነግን የአፓርታድ አገዛዝ  እውነተኛ ባሕሪን  በሚገባ የምትገልጥ የወፍ ዘር ናት። ፒኮክ ከሌሎች የወፍ ዘሮች የምትለየው ውኃ ቀጠነ እያለች የምታለቃቅስ፣ ሰማዩንም ምድሩንም የኔ ብቻ ነው የምትል እጅጉን ስግብግብ ፍጡር፣  ከሌሎች ወፎች ጋር አብራ መኖር የማትችል ዘውገኛ በመሆኗና ወደ ክልሏ ሌሎችን የወፍ ዘሮች  ድርሽ እንዲሉ ባለማድረጓና ወደ ግዛቷ ባለማስገባቷ ነው። ፒኮክ ምናልባትም ሌሎቹን የማታስገባበት የራሷ ብቻ  የሆነ ክልል የፈጠረች ስግብግብ የወፍ ዘር ሳትሆን አትቀርም። ፋሽስት ወያኔዎችና  ናዚ ኦነጋውያን ባለፉት 28 ዓመታት ያሳዩን ይህንን የፒኮክ ጠባይ  ነው። የፒኮክ ጠባይ የተጠናዎታቸው ፋሽስት ወያኔዎችና ናዚ ኦነጋውያን ሲወጡ ሲገቡ ራሳቸውን ለማየት ሲሉ  በአንበሳው  ቦታ የፒኮክ ሐውልት ማቆማቸው የማይጠበቅ ነገር  አይደለም።  በመሆኑም በሰው አምሳል የተፈጠሩ ፒኮኮች የባሕሪያቸው መገለጫ የሆነውን  የፒኮክ ሐውልት አቁመው  ለምን የራሳቸውን ማንነት ሲወጡ ሲገቡ አዩ ማለቱ  ቁም ነገር አይደለም።
ቁምነገር የሚሆነው ፋሽስት  ጥሊያን አገራችንን በወረረበት ወቅት የኢትዮጵያውያን የጀግንነት ምልክት የሆነውን  የአንበሳውን ሐውልት አፍርሶ  በምትኩ የፋሽስቶችን ምልክት አቁሞ ሲሸልል ያዩት ጀግኖች አባቶቻችን  አንበሳ ያውም «ጥቁር አንበሳ» የሚል ድርጅት መስርተው አንበሳ በመሆን  የአንበሳውን ሐውልት ያፈረሰውን ፋሽስትን በዱር በገደሉ አንደባለው በመጣል አንበሳውን ወደ ቦታው እንደመለሱት ሁሉ በባለጊዜዎቹ ፒኮክ እንዲተካው የተደረገውን  አንበሳም  ወደነበረበት ቦታ ለመመለስ  አንበሳ ሆኖ መገኘቱ  ነው።
Filed in: Amharic