>

‹ኮሮና ወደ ኢትዮጵያ አይገባም›፤ ይልቁንስ የኢትዮጵያን ኮሮናዎች ላስተዋውቅህ! (ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)

‹ኮሮና ወደ ኢትዮጵያ አይገባም›፤ ይልቁንስ የኢትዮጵያን ኮሮናዎች ላስተዋውቅህ!

 

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ 

 

ዳ. ጉ. ካሣ የሚባል ወፈፌ ተናግሯል ብለህ ሀኪም የሚነግርህን ጥንቃቄ የምትንቅ ዜጋ ካለህ ኃላፊነቱ የራስህ ነው – ወዳጄ ለማንኛውም ፌጦ መድኃኒት ነውና ለክፉም ለደጉም ጠንቀቅ በል፡፡ እኔ የሰማሁትንና የሚሰማኝን ከመናገር በዘለለ እንደነ “እኅተ ማርያም”ም ሆነ እሥራኤል ዳንሣና በላቸው ግርማ “ቅድስት ማርያም በጆሮየ ሹክ አለችኝ” ወይም “ኢየሱስ ኮሮናን እጄ ላይ ዱቄት ሲያደርገው አየሁ፤ ኮሮና በ30 ቀናት እንደሚጠፋ ኢየሱሴ ነገረኝ” የምል የእንጀራ ሰለባ ዚቀኛ(ቀልደኛ) አይደለሁም፡፡ 

ይህች ማስታወሻ ከነፍሴ ቋጠሮ የወጣች ናት፡፡ እጅግ ብዙ ሰው እንደምታስቀይምብኝም ከአሁኑ እረዳለሁ፡፡ ግን ምንም ማድረግ አልችልም፡፡ መጥፎ ምልኪን የማትወዱና በግለሰብና በድርጅት የምታመልኩ ወንድም እህቶቼ አታንበቡኝ፤ ትታመሙብኛላችሁ፡፡ ሸፋፋ መቆሚያ መጥፎ ነው፡፡

ወደገደለው፡፡ ኮሮና በጥቂት ምሥጢረኛ የአዲሱ ዓለም ሥርዓት አራማጅ ሰዎች በቤተ ሙከራ ተሠራ፡፡ ይህን ምሥጢር ከተመረጡት በስተቀር ቫይረሱን የሠሩት ሣይንቲስቶች ራሳቸው ለምን እንደተሠራ ዋና ዓላማውን ላያውቁ ይችላሉ፡፡ … ካነበብኩት የኮሮናን ስያሜ ከዐውሬው ቁጥር ከ666 እንዴት እንደሚያያዝ ላስታውስ፡፡ ይበልጥ እንዲመቸኝ ለተወሰነ ጊዜ የቋንቋ ማርሽ ልቀይር ነው፡፡

The name COVID19 is the official `baptismal` name of CORONA, a Latin word to mean “crown” in English but used on purpose to connote the symbol of the Beast as clearly stated by John the Apostle in his Revelation (13:18).

Though the naming is said to have some connection with regard to the shape of the virus, the main objective of picking up CORONA to name these series of biological weapons (SARS, MERS…) is related to the following alphanumeric gematria.

Give numbers 1 to 26 to the alphabets A to Z. Then, the calculation comes next.

C  –   3

O  – 15

R  – 18

O  – 15

N  – 14

A  –   1

___________

6     66 = 666

_____________

 

The masterminds of the `Invisible Government` are very smart. They perfectly know how to go with such treacherous things since the time their lord fell down to this poor planet Earth.

አያ ዲያቢሎስ በልጆቹ የሠራው ቫይረስ በመሠረቱ ዕንቁዎቹ የአብራኩ ክፋዮች የምድርን ሠፋሪዎች በ80 መቶኛ አጥፍቶ ፀሐያቸው እየደበዘዘችባቸው በመምጣቷ ምክንያት ሌላ ፕላኔት እየፈለጉ ከሚገኙት ኅዋውያን ማርካባውያን (The so called Marcabans … from among the ET beings) ጋር በሽርክና ይህችን ዓለም ለመቆጣጠር እንዲመቻቸው ነው – (ይባላል)፡፡ ይሁንና ይህ ክስተት የጨለማው ንጉሥ አበጋዞች በፈለጉት መንገድ የሄደ አይመስልም፡፡ የአወንታዊው ኃይል ቸሩ እግዚአብሔር (Dio, God, Allah,… I care less in the nomenclature…) ዕቅዳቸውን ወደ አንድ ወገን አንሻፈፈና እየሆኑ ያሉትን ሲሆኑና እርስ በርስ ሲካሰሱ እያየን ነው (ዛሬ እንኳን ለአብነት አሜሪካ “ቫይረሱን ፈጥራ ወደ ዓለም ልካለች” ብላ ቻይናን ከሳታለች)፡፡ ጥሩ ነው፡፡ እዚያው ይዋጣላቸው፡፡

“ከላይ የምለው ከታች ከምለው በምን ይገናኛል?” ብዬ ራሴን ልጠይቅ፡፡

ይህ ቫይረስ በአፍሪካ ለምን እነሱ የፈለጉትን ያህል ሊዛመትና የነሱን የሬሣ ቁልል ግልባጭ በአህጉራችን ሊያዩ እንዳልቻሉ እኛንም እነሱንም እንደገረመን አለን፡፡ የኛሁኔታ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ሰው “ከአሁን አሁን ተጠርቼ በጥይት ተበሳሳሁ ወይም በገመድ ተንጠለጠልኩ” እያለ የሚጨነቅበትን ጥቁር ድባብ ይመስላል፡፡ እንደውነቱ በብዙ ነገሮች ከተጎጂዎቹ ጋር የሚመሳሰሉትን እንደ ደ. አፍሪካና ግብጽን በተወሰነ ደረጃ ትተን የአፍሪካ በዚህ ደረጃ መገኘት ሊጠና ይገባዋል፡፡ 

ኢትዮጵያ ግን በጠቆምኩት ጥናት ሊጠቀሱ የሚችሉ መልካም የበሽታው ማምለጫ መንገዶች እንደተጠበቁ ሆነው የሚከተሉት የራሷ ቫይረሶች ስላሏት ፈጣሪ ይህን ግምኛ ቫይረስ ቢሰጠን ምን ዓይነት ሰቆቃና መከራ ሊደርስብን እንደሚችል ከማጤን የተነሣ ይመስላል እስካሁን ታግሶናል፡፡ በኛ ጥንቃቄ ነው ያልተጠቃነው የሚል ካለ ሞኝ ነው፡፡ በኛ ስትር ያለ የኑሮ ዘይቤና በተመጣጠነ አመጋገባችን ነው ቫይረሱን የከላነው የሚል ዕብድ መቼም አይኖርም፡፡ ዛሬ ዕለተ መስቀል ነው፡፡ ሚያዝያ 9 ቀን 2012 ዓ.ም፡፡ ሁለት ወሸባዎችን (የኳራንታይን ጊዜ) ጨርሰን ሦስተኛውን አጋምሰናል፡፡ በዚህች ቀን እንኳን የተያዘው ሰው አንድ ብቻ ነው – በአሜሪካ ግን በዚህች ቀን ከሁለት ሽህ በላይ ሰው ሞቷል፡፡ በሀገራችን ዛሬን ጨምሮ ባለፉት አራትና አምስት ሣምንታት ውስጥ በቫይረሱ የተያዘብን የሰው ቁጥር ግፋ ቢል 12 ቢሆን ነው፡፡ ሌላውና በዛሬው መረጃችን መሠረት 84 የሚሆነው የቫይረሱ ተጠቂ ከውጭ ያመጣው ነው፡፡ ከውጭ ያመጣውን በሀገር ውስጥ እንደተያዘ መቁጠር ደግሞ ስህተት ነው፡፡ ለዚህም ነው ከመነሻየ የሰውና የድርጅት ኮሮና እንጂ እውነተኛው ኮሮና ወደ ሀገራችን እንዳልገባ በሾርኒ የጠቆምኩት፡፡ የተንበጨበጭነው የሌላውን ዓለም በመስማት በፍርሀት ቆፈን ተይዘን እንጂ በገቢር ቫይረሱ ተዋግቶን አይደለም፡፡ ያሉን ህመምተኞችም ከሦስቱ በስተቀር ቀሪዎቹ እያገገሙ ይመስላል፡፡ የሞቱብንን በቫይረሱ እንደሞቱብን እንቁጠርና በመቶኛ ቢሰላ ሦስት ከመቶ መሆኑ ነው፡፡ ጥንቃቄችን ግን ተጠናክሮ ይቀጥል፡፡ ይሁንና በፍርሀት አስቀድመን አንሸነፍ፤ እጅም አንስጥ፡፡ በአንድዬ እንመን፡፡ የዛሬው የቀስተ ደመና ምልክትም አንድም ለተግሳጻዊ መከራ አንድም ለሰላማዊ ዝዬራ ሊሆን ይችላልና በጎው እንዲያመዝንልን በርትተን እንጸልይ፡፡ ከሰው እንደሆነ የሚጠበቅ ነገር የለም፡፡

ጥንቃቄው ጎልቶ የሚታየው የአምልኮት ቦታዎች ላይ ነው – እሱም ሌላ ዓላማ ከሌለው ነው፡፡ ገበያውና መዝናኛው ከሞላ ጎደል እንደደራ ነው፡፡ ጃዝ ብሎ የለቀቃቸውን እንጃ ወቴዎች የበረቱት በሙሰኞች፣ በዘማውያንና በሦዶማውያን ምክንያት ቀድሞውን በተዘጋች ቤተ ክርስቲያን ላይ ነው፡፡ ዝርዝር ኪስ ይቀዳልና ለምን ቀድማ እንደተዘጋች መናገር የሚጠበቅብኝ አይመስለኝም፡፡

በቀጥታ ወደ ኮሮናዎቻችን ልግባ መሰለኝ፡-

  1. ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ – ቁጥር አንድ ኮሮና! ኮሮና ቫይረስ – ኮቪድ 19 – የገዳይነት መቶኛ ሥሌት በአማካይ ከ4 እስከ 10 ነው፡፡ የአቢይ ግን በኔ ግምት ከ50 በመቶ ይበልጣል፡፡ የዚህን የጭቃ እሾህ ሰውዬ ገመና ዘርዝሮ መጨረስ አይቻልም፡፡ ብዙ ጊዜ ስለተናገርኩ ያን ማጣቀስ ነው፡፡ (በምትወዱት ሰዎች ላይ በማደርሰው የስሜት መጎፍነን አዝናለሁ፡፡) አወዳደቁ ከሮምም ይከፋል፡፡ ምክንያቱም ይሁዳ ለማትረባ 30 አላድ ብሎ ኢየሱስን በመሳም ለስቅላት አሳልፎ እንደሰጠው ሁሉ አቢይም ለመናኛ ሥልጣንና ዝና ብሎ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ለአጋንንቱ ዓለም አሳልፎ ሰጥቷቸዋል፡፡ ስለዚህም ሊሆን ይችላል ኮሮና በምርኮኞቹ ላይ እምብዝም ሊጨክን ያልወደደው!
  2. ሕወሓት፣ ብአዲን/ሕወሓት፣ ኦህዲድ/ኦነግና ብአዲን/ኦህዲድ – እነዚህ ኮሮናዎች የመግደል አቅማቸው ገና አልተነካም፡፡ ማይምነትንና የትምህርት ጥራትን ውድቀት በዋናነት ጨምሮ ዘረኝነትንና ጎጠኝነትን እንዲሁም ሥር የሰደደ ሙስናን ከማስፋፋት እስከትልቁ የሰውን ልጅ ዘቅዝቆ መስቀል ድረስ ያላስተማሩንና ያላለማመዱን የወንጀልና የኃጢኣት ዘር የለም፡፡ የሁለት ጌቶች ባርያ የሆነው ብአዴን በተለይ አንድን የኅብረተሰብ ክፍል ለማጥፋት ቀን ከሌት እየደከመ ነው፡፡ የዘመናት የእሽክርና ልፋቱም መስመር ይዞለታል፡፡ እወክለዋለሁ የሚለውን ሕዝብ በሰላይነትና በእጅ አዙር አስተዳዳሪነት እያኮሰመነ ሌሎቹ ጠንክረው እንዲወጡ ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረላቸው ነው፡፡ የነሱን ጦርነት ተረክቦ ያንን የዋህ ሕዝብ ጉያው ውስጥ በመግባት የኅልውና አደጋ ደቅኖበታል፡፡ ሕወሓት ከአንድ የአውሮፓ ሀገር ባልተናነሰ እንዲያውም ከበርካታዎቹ በበለጠ በወታደርና በስንቅ ትጥቅ ተዘጋጅቷል፡፡ ትናንትና መጋቢት 17 ቀን 1981 ዓ.ም ደራ ሰሜን ሸዋ ላይ በወያኔ ተጠፍጥፎ በኦሮምኛ ተናጋሪ ምርኮኞች የተበጃው ኦህዲድ/ኦነግም እንደዚሁ በመቶ ሽዎች የሚቆጠር ጦርና ሙሉ ዝግጅት ማድረጉ ይታወቃል፡፡ ይህ ሁሉ የፈሪ ዱላ የሚዘጋጀው ለማን እንደሆነ ሰው ብቻ ሣይሆን እግዚአብሔሩም ሰይጣንም በሚገባ ያውቃሉ፤ “ለኔም እግዜር በግልጽ ነግሮኛል፤ ‹ሦስት ብትርም አንሳ› ብሎኛል” (እኔስ ከእኅተ ማርያም በምን አንሳለሁ?- ስቀልድ ነው አንተ)፡፡ እነዚህ በተለይ ሁለቱ ኮሮናዎች ከዚህ ከቫይረሱ ኮሮና መብረድ በኋላ በሚያስነሱት አቧራ ብዙ … ሕዝብ የሚያልቅ ይመስለኛል (እንደዚያ እንደያዬሰው የሚባል ጋዜጠኛ እንዳልሆን ነው ቁጥር ያልገለጽኩት፡፡) ትልቁ ዕልቂት የሚከሰተው አጥፊና ጠፊ፣ ጥጋበኛና አልሞት ባይ ተጋዳይ የሚቧቀሱበት የጦር ዐውድማ ሲለቀለቅና የማይቀረው የሞት የሽረት ፍልሚያ በሰሜንና በሰሜን ምዕራብ በኩል ሲጀመር ነው፡፡ የሚተርፈው ጥቂት እንደሆነ ይነገራል፡፡ ሱቅ እንደገባ ሕጻን “ሁሉንም እኔ ካልጠቀለልኩ ሞቼ እገኛለሁ” ብሎ ጅልነቱን በአደባባይ እያሰጣ የሚገኘው የኦህዲድ ጠንጋራ አካሄድ በግልጽ የሚናገረውም ይህንኑ የማይቀር አርማጌዴዖን ነው – ቁርጥህን ዕወቅ አዳሜ! ወያኔ ብልጥ ነበር – ይሄኛው ደግሞ ንክር ያለ ንክር፡፡ ሰው አበላልን እንኳን መማር አይችልም? አወዳደቅን ስለማሳመር ከቀደመ ውዳቂ ማለቴ ወዳቂ መማርስ ማንን ገደለ!
  3. ርሀብ – ከጦርነት በፊትም ሆነ በኋላ ርሀብ ትልቅ የእርስ በርስ ፍጂት መንስኤ ነው፡፡ ከጦርነት የበለጠ ኃይልና ብርታት አለው፡፡ የሚጎርሱና የሚጮሁ አፎች እንጂ የሚያመርቱ እጆች በበቂ ሁኔታ በሌሉበት የሀገራችን አስጨናቂ ድባብ ጦርነት ታክሎበት ቡሃ ላይ ቆረቆር ነው፡፡ ወዮልሽ!
  4. ሙስና – የሀገራችንን የመቃብር ጉድጓድ በፍጥነት እየቆፈሩ ከሚገኙ ወያኔ/ኦህዲድ ሠራሽ መቅሰፍቶች አንዱ ሙስና ነው፡፡ ወያኔ እንኳን ነፍስ አውቃ ከማዕከላዊ መንግሥት በሰባት ሚሊዮን ብር ተገዝቶ የተላከላትን የኮሮና መከላከያ ቅራቅንቦ በራሷ መንገድ አጥንታ እንኳንስ ሰባት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሽህ ብርም እንደማያወጣ በግልጽ ተናግራለች፡፡ ይህም አይገርምም፡፡ በነአፍላጦን ፍልስፍና እኮ ተማሪ መምህርን ካልበለጠ መምህር በከንቱ ደከመ እንጂ እንዳስተማረ አይቆጠርም፡፡ ስለዚህ ሙስናው ከወያኔም ብሷል ማለት ነው፡፡ ቁጥር የማያውቁ ስግብግብና ራስ ወዳድ ባለሥልጣናት ገጥመውን በሁለት ሚሊዮን ብር እንደነገሩ የተገነባን ክሊኒክ በመቶ ሚሊዮኖች፣ በመቶ ሚሊዮን የተሠራን ሽሮ ፈሰስ የሚባል የአስፋልት መንገድ በቢሊዮኖች፣ በአምስት ሚሊዮን ብር የተሠራን ፍርግርግ ትምህርት ቤት በመቶ ሃምሳ ሚሊዮን … ማወራረድ እጅግ የተለመደ መደበኛ ሥራ ነው፡፡ አዲዮስ ሀገር! አዲዮስ ፖለቲካ! አዲዮስ ኅሊና! አዲዮስ ሞራልና ሃይማኖት! እዚህ ደረጃ የደረሰው የሙስና ተግባር ሀገሪቷን ሊቀብራት ቋፍ ላይ ነው፡፡ ካለጉቦ የሚገኝ ነገር ምናልባት ሞት ብቻ ነው፡፡ ሰዎች እንደሚያሟርቱብን ኮሮና በሙሉ ግርማ ሞገሱ ከተገለጠ ግን ሞትም ከርሱ ብሶ ቢለምኑት የማይገኝ ይሆናል፡፡ ያን በሩቅ!
  5. ባዕድ አምልኮና ሃሣይ መሲሖች – በሃይማኖቶችና ዛርና አውሊያን በመሳሰሉ ባዕድ አምልኮቶች መሠማራትና ሕዝብን በአእምሮ ማቀንጨር፣ በገንዘብም ማደኽየት ህግና ሃይ ባይ የሌለው የሥራ አጦች ዋና መናኸሪያ ሆኗል፡፡ ከፍ ሲል በአግቦ መልክ እንደጠቃቀስኳቸው ያሉ አሰለጥ ቦዘኔዎች በሃይማኖት ሰበብ እያደረሱት ያለውን ማኅበራዊ ቀውስ መታዘብ ለቻለ ሀገራችን ምን ያህል ዕድለቢስ እንደሆነች መገንዘብ አያቅተውም፡፡ አተርፍ ባይ አጉዳይ እንዲሉ የበለጠ አገኛለሁ ብሎ ብር 450 ሽህና ሚስቱን ለታምራት ገለታ ገብሮ አጨብጭቦ ስለቀረ አንድ ገልቱ ዜጋ በሰማሁ’ለት የተገረምኩትን አግራሞት መቼም አልረሳውም፤ አንዲት ቀበጥ ዘፋኝም ለሞት ተዳርጋለች፡፡ ሕዝባችን በአባይ ጠንቋዮችና በ“ጽድቅ ሥራቸው” ኢየሱስ ክርስቶስን እናስከነዳለን በሚሉ ሀሰተኛ ነቢያት ምን ያህል እየተጎዳ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ መጽሐፉ በምንገኝበት የመጨረሻ ዘመን እሳት ከሰማይ ማዝነብ የሚችሉና ታላላቆችን ሳይቀር የሚያስቱ ሣተና የአጋንንት ውላጆች እንደሚመጡ መተንበዩን ዘንግተናል – ይሄውና የአንድን ታላቅ ፍልፍል ቤተ ክርስቲያን መሥራች አባት ያሳሳተች መበለትስ ተፈጥራ የለምን? ከተባለው ምን ያልሆነ ነገር አለ? የዚህ ሁሉ ውርጅብኝ መሠረቱ በፈጣሪ ምትክ ገንዘብ መመለኩ ነው፡፡ የልቡ እስኪደርስ ባህታዊና አጥማቂ ሲለውም የዐውደ ምሕረት ሰባኪ ሆኖ ሲያበቃ ሕዝብን አውላላ ሜዳ ላይ ጥሎ ከወደዳት ጋር ሼሼ ገዳሜ የሚለውን መነኩሴና ባህታዊ ቤቱ ይቁጠረው፡፡ ክርስቶስን ስለመምሰልና ስለዘመናችን ተዓምር ሠሪ የዲያቢሎስ ሊቀ ሊቃውንት ብዙ ባልኩ ደስ ባለኝ፡፡ ችግሩ ሰሚ የለም፡፡ እንዳንደማመጥ በመካከላችን የሰናዖር ግምብ ቆሟል፡፡
  6. ያለመለወጥና ለውጥን የመፍራት አባዜ – ብዙዎቻችን ለውጥን አጥብቀን እንፈራለን፡፡ የሽዎች ዓመታት ዕድሜ ጠገብ አሠራርንና እምነትን ጭምር ሙጭጭ ብለን ስንጓዝና በዚያም ስንኮራ ሌላው ዓለም ጥሎን ኮበለለ፡፡ የኮበለለው ዓለም የራሱ ችግሮች ቢኖሩበትም ጠንካራ ጎኖቹን በመውሰድ ከኛ ጠንካራ ጎኖችም ጋር በማዛነቅ ትልቅ እመርታ ልናሳይ በቻልን ነበር፡፡ ለምሣሌ በዚህ ዘመን በዶማ ባንጎደፍርና በበሬ ባናርስ ኖሮ ለሌላ መትረፉ ቀርቶብን ለራሳችን ባላነስን ነበር፡፡ ባለን ድህነትም ላይ እንደባህል ሰቅዞ የያዘን የምቀኝነትና የተንኮለኝነት ልክፍትም ስንዝር ሊያነቃንቀን ያልቻለ ትልቅ ኮሮና ነው፡፡ በነዚህ ሁሉ ኮሮናዎች ላይ ታዲያ ኮቪድ19 የሚሉት ቢታከልብን ምን ይውጠናል? እግዚዖ ነው! አያድርስ፡፡

ነጋዴው – የነጋዴዎች ነገር ባይነሳ ይሻላል፡፡ ግን እንዳይቀየሙኝ በትንሹ መጥቀስ አለብኝ፡፡ ነጋዴው ከመንግሥት ሹሞች ጋር በመመሳጠር የለዬለት የቀን ጅብ ሆኗል፡፡ በዚህ በኮሮና ጊዜ ሳይቀር እርሱም መሞቱን ረስቶት አቅሉን ስቶ በስንጥቅ ትርፍ ገንዘብ እያከማቸ ነው፡፡ ለዚህም ማይምነቱና በዚያም ሰበብ የተጣባው ዘረኝነቱ ሳያበረታታው አልቀረም፡፡ የዕቃ ውድነቱ በሴከንዶችና በደቂቃዎች ነው – እንደዱሮው በመተሳሰብ ላይ ተመርኩዞ በአሥራዎች ዓመታት ግፋ ቢል አንዴና በሣንቲም ደረጃ አይደለም፡፡ ጭንቅላት ወደ ሆድ ወርዶ የተወተፈበት ሁኔታ ነው የሚታይ ያለ – ለዚህም ክስተት መፈጠርና እንደሰደድ እሳት መስፋፋት ከላይ ከፌዴራል መንግሥት አቅጣጫ ወርዶ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፤ ሆ! ኢሕአዲግ ማነው ኦህዲድ ብሆንም እንደሚሳካልኝ የሚጠቁም ሁኔታ ላይ እኮ ነው ያለሁት በዚህ የአነጋገር ሥልቴ፡፡ መልካም የፋሲካ በዓል፡፡

EMAIL

ma74085@gmail.com

Filed in: Amharic