>

ዘውዳዊዉም ሆነ ወታደራዊዉ፣ ወያኔውም ሆነ ብልጽግናው ህዝብ ከማስለቀስ ያለፈ ፋይዳ የላቸውም?  (ኣስገደ ገብረስላሴ)

ዘውዳዊዉም ሆነ ወታደራዊዉ፣ ወያኔውም ሆነ ብልጽግናው ህዝብ ከማስለቀስ ያለፈ ፋይዳ የላቸውም? 

ኣስገደ ገብረስላሴ
መጀመሪያ  ባለዘውዱ ወርቃማ ካባ ለለበሰው ስርአት ፤ እንዲሁም  ባለኮኮቡ  ወታደራዊ ስርአት በመቃወም  የታገሉት እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች  መስዋእት ከፍለው  እጅግ ቡዙ በአስር ቢሌን ብር ብሎ  ቁሳቁስ የወደመበት  በገንዘብ  ሲታሰብ   ።በመሆኑም ሁሉም  ኢትዮጱያዊ የስደት የረሀብ ሱስ እንዳለው ከሱ በማይ በልጡ ኣረብ ኣገሮች ፣በሌሎች ኣገሮች ተዋርዶ ኖሮዋል ኣሁንም እየተዋረደ ነው ኣለቆመም  ።
ከላይ የተጠቀሱ ገዥዎች ስርኣታቸው (ኣጋዛዛቸው) ህዝብ መብቱ  ኣግኝቶ ራሱ  በመረጣቸው መሪዎች ሳይሆን ይመራ የነበረ፤  ዘውዳዊ ስርኣት  አዲስ ኣባባ ቤተመንግስት ቁጭብሎ  ህዝብ በማያውቃቸው ያልመረጣቸው ፣ጠቅላይ ግዛት ፣ኣውራጃ ፣ወረዳ ፣ገዥዎች ተብለው መሳፍንቶች ወይ ነፍጠኞች  ይሾሙለት  ነበር። ወረድ ብለውም ምስሌነ ፣ጨቃሹም ተመድበው ለህዝብ ኣፍነው በመያዛቸው  ህዝብ መሮት  ከባድ መስዋእት  ከፍሎ ታግሎ ጣላቸው።
ቀጥሎ የመጣ  የዘውዳዊው ስርዓት ዘብ የነበረ ባለኮኾቡ ፋሽሽታዊ ደርግ የህዝቦች የትግል  ስትራተጂ ጠልፎ በሀገራችን ከዘውዳዊ ስርኣት የባሰ ስርኣትይዞ ብቅ ኣለ።ይህም ከዘውዳዊው ኣሀዳዊ ሰርአት በተጠናከረ መንገድ  ስሙ ቀይሮ የኢሰፓ መዋቅር  የኣማራር ቡዱን  ኣሁንም ከክልል እስከ ቀበሌ የኢሰፓ ተጠሪዎች ፈላጭ ቆራጭ  ገዳዮች ፋሽሽቶች መድቦ ቀጠቀጠን ።  የኢትዮጱያ  ህዝቦች  ኣሁንም የደርግ ስረኣት ከዘውዳዊው ስርአት የበለጠ ኣፋኝ  ኣሀዳዊ ስርአት መሆኑ በፍጥነት ተገንዝቦው   የማያዋጣቸው መሆኑ ስለገባቸው ፤ በሁሉም ኣቅጣጫ የኢትዮጱያ ክልሎች ጸረ ደርግ ትግል  በተደራጀም ባልተዳራጀም  መንገድ ትግላቸውን በመቀጣጠል ለ17 ኣመታት ያህል ከባድ ጦርነት በማድረግ በሀገር ደረጃ  በሰራዊት ፣በኣየር ፣በመጨፍጨፉ  የህዝብ ሀፍት በመውደሙ  ህዝብ ወደ የኣህጉሮች ተሰደደ በተለይ በኣረቦች በሌሎች ኣገራት ተሳቃዬ ፣እንዳው  በዘመነ ዘውዳዊ ስርኣት ኣጋዛዝ የባሰ ተሰደደ ። ግን ጮቋኞች ለህዝብ ፍትህ ከነፈጉ ሊኖሩ ኣይችሉምና ደርግሞ  በ17  ኣመት ህዝባዊ ትግል ጥጉን ያዘ ።
ቀጥሎ የመጣ በረኸኛዎ  ህዋሓት ኢህኣደግ ሀቀኛው ጥቁር  የዘውዳዊው ስርኣት  ካባው ደበቆ  ሰላማዊ ይመስል ነጭ ካባ ለብሶ በእኔ ዘመን ፍትህ ፣ዲሞክራሲ፣ የህግ የበላይነት በሽ ነው ኣለን ። ህዋሓት ኢህኢደግ ለይምሰል ከሰወስ ኣመት ያልበለጠ  ጊዜ ኣስመሳይ ዲሞክራሲያዊ ስራዎች ሰርቶዋል ። ከዚህ ጎን ለጎንግን ወስጣዊ ኢዲሞክራሲያዊ ስራዎች ሰርቶዋል ።የህዋሓት ኢህኣደግ አንድ ጠንካራ ጎን የምንሰጠው ባለፉት ኣሀዳዊ ገዥዎች ያልነበረ  ምንም እንኳን የህዋሓት ኢህኣደግ ተጽእኖ ይንሮው  ኣብዛኛው የተሸራረፈ  ዲሞክራሲያዊ ይዘት ያለው ህገመንግስት ነበረው ።
ህዋሓት ኢህኣደግም ልክ እንደደርጊ ረጅም ሳይጋዝ  በህገመንግስት የሰፈሩ ዲመክራሲ ቀይ መስመሮች፣ ኣሳራሮች ራሱ  በመናድ ከደርግ የማይተናነስ ጸረዲሞክራሲ፣ኣፋኝ ፣ኣሳሪ ፣ገዳይ ፣ በእሱር ቤት ዜጎች መሰቃየትም  ልክ እንደደርግ ሆነ ።  ኢህኣደግ  ጦሮኛ ሆነ ፣ህዋሓት ኢህኣደግ  27 ኣመት ዚገዛን  ሀገራችን የጥይት ድምጽ ጦርነት የማይሰማባት  ቀን ሳምንት ኣልነበረቾም ።ፍትህ የህግ  የበላዮነት፣ ነጻ ምርጫሞ ኣይታሰብም  ነበር ። በዘመነ ህዋሓት ኢህኣደግ ሰደት ፣በበረሀ መታረድ ፣በባህር መገልበጥ ከሌሎች ስርኣቶች የባስ ነበር ።
የህዋሓት ኢህኣደግ ኣጋዛዝ ለዩስሙላ ዲሞክራሲያዊ ስርአት መሰረትኩ ኣለን እንጅ የመሰረተው መንግስታዊ መዋቅር ከዘውዳዊውና ከፋሽሽቱ ስርዐት  የባሰና የተራቀቀ  ፈላጭ ቆራጭ  ኣሀዳዊ  ስርኣት ነው ያመጣልን ። ለዚሁ ሀቅ መረጋገጫ ፣ለይስሙላ ምርጫ በሚል ሽፋን ራሱ መልምሎ ህዝብ የማያውቃቸው ያስቀመጣቸው  ሰዎች  በግድ እንዲመረጡ ፣ተፎካካሪ ፓርቲዎች ወደ እሱር ቤት ወይ የምርጫ ኮሮጆ  ይሰርቅ ነበር ።  ይህ ኣሳራር ለወደፊት የሚተዎው ኣዮደለም ።
  የኣሁኑ  በዶ/ ኣብይ አህመድ የሚመራ ራሱ የለውጥ ሀይል ነኝ እያለ  የሚጠራ ገና ሁለት ኣመት እየመላው ያለ የብልጽግና ፓርቲ  ማን ንበለው፣ባህሪውስ  የማነው ?
 ወዴትስ  እያመራ ነው ?  በመሰረቱ ኣብይ ኣህመድ ከነጓዶቹ  ኣብዛኞቹ በኢህኣደግ ውስጥ ከ28 —30 ኣመት የኖሩና በኢህአደግ ካድሬ ሆነው  በኢህኣደግ የተራቀቀ ኣሀዳዊ ስርኣ በጥልቀት የሰለጠኑ  ፣በኣፈና ኣሳራራቸው በየሙሱና ጥበብ  በሙያው የተካኑ ፣ህዋሓት ኢህኣደግ በፈጸመው በጎም መጥፎ ስራ ወሳኝ ሚና  የነበራቸው  ሲሆኑ ።ኣሁን ደግሞ መላው የኢትዮጱያ ህዝቦች በፈጠሩት ህዋሓት ኢህኣደግ ያንቀቀጠ ህዝባዊ ማእበል   በመገንዘብ  በፍጥነት ወደማእበሉ በመቀላቀል የግግል ማእበሉ   ጠልፈው ወደ ጥቅማቸው በማዋል ለጊዜው ከወንጀለኝነት ድነዋል  ።
እነዚህ ሰዎችም  ምንም እንኳን እንደ ህ ዋሓት  ኢህአደግ ኣሀዳዊ ስትራተጂ ፣ፖሊሲ ፕሮግራም  ባይኖራቸውም  ኢትዮጱያ ህዝቦች  እንወክላለን የሚሉ ቡዙ ሀገራዊ፤ ክልላዊ (ብሄራዊ )  ፓርቲዎች ትግል ኣንስተው ህዋሓት ኢህኣደግ ለማስወገድ በማሰብ 27 ኣመት በመታገል ምንም እንኳን በነበረው ኣፈና ቡዙ ሽግር  ማሰር መግደል ወዘተ ቢያጋጥማቸውም  እየወደቁ እየተነሱ በሀገር ውስጥም በውጭም የነበሩ ታጋዮች የፈጠሩት ህዝባዊ  የፓለቲካ ማዕበል  የትግል ውጤት  ተደማምሮ  ለህዋሓት ኢህኣደግም በውስጡም  በውጭም በስብሶ  ህዝባዊ ተቀባይነቱ ወደ ዜሮ ድሪ ወርዶ ስለተፍረከረከ ፣የመፍረክረኩ ውጤት ደግሞ  የተፎካካሪ ፓርቲዎች  ውጤት  እያለ ፤ እነዚህ የለውጥ ሀይልነን የሚሉ ለኣዳዊ ስርኣት ከመቃብሩ ጉድጓድ አውጥተው  ለማደስ  የተሰሩ ይመስል  በእንደመር ቃላት መዝሙር እስትራተጅ ፣ ፖሊሲ  ነድፈው የመጡ መሆናየው ኣውን ዘጊተን ተገንዝበናል ።
ቢያንስ የደርግ ወታደራዊ ኣሀዳዊ መንግስት እና  የኢህኣደግ ዘመናዊ ኣሀዳዊ መንግስታት  መጀመሪያ ወደ ስልጣን ሲመጡ ለስሙላ ጥቂት ዲሞክራሲ የሚመስሉ ነጥቦች እያነሱ  ኣንድኣንድ ለህዝብ ኣሳማኝ የሚመስሉ ስራዎች  እንደፈጸሙት ሁሉ ፤እነዚህ የህዝብ ስሜት ለማብረድ ጽንሰ ሀሳብ የሌለው የእንደመር ሰበካ ህዝብ ለመደናገር  ኣስመሳይ ዲሞክራሲያዊ መፍትሂዎች ሰጥተዋል
እኒህ  የለውጥ ሀይሎች ግን ከአንድ ኣመት በኃላ  ራሳቸው ብልጽግና ፓርቲ ሆነው መንግስት  የሆኑ ረጅም ሳይጓዙ የኢትዮጱያ ህዝቦች ከ150 ኣመታት በላይ ዜጎች እንቢ ለኣሀዳዊ ስርኣት ኣንገዛም ብለው  ራሰቸው በመረጡት ራሳቸው  በራሳቸው ለማስዳተደር መብት ጥያቄ አንስተው ኣእላፍ መስዋእት የከፈሉበት ጥያቄ  እነብልጽግና ፓርት  ይህ የሚሌኖች ለመደብ ጠላቶቻቸው ለመጣል  የታገሉለት  በመጥለፍ  ኣሀዳዊ ስርዓት  በማያራመዱ  ወደ ክልሎች ጣልቃ በመግባት የነበሩዋቸው መሪዎች በማግለል ለህዝብ በተለያዩ ድለላ ብሎም መሪዎቻቸው  በማሰር በማስፈራራት ህዝብ ያልመረጣቸው  ግለሰዎችን በመመልመል የከልል ፣የዞን  ፣የወረዳ  የምስሌነ ሽሞኞች በመመደብ ፣ልክ እንደዘውዳዊም  እንደደርግ ስርኣት የሽመት ኣሰጣት በመሾም በሁሉም ክልሎች ትርምስ ፣ጦርነት በመፍጠር ኣገራችን ታውካለች ትንሽ እንኳ እንደ ኢህኣደግ ሽፋን ባለበት  በድራም በመቀናበር  (ማጭበርበር) በሌለበት የተራቀቀ ሌባ ኣሀዳዊ ስርኣት  ቢያራምዱ መጋለጣቸው እንኳ ኣይቀሬ ቢሆን ለጊዜው ለመደናገር ይችሉ ነበር ።ኣሁን ግን ኣይናቸው አፍጥጠው የኣሀዳዊ ስርአት የኣሟራር መዋቅር እስከ ቀበሌ ለመሾም እንደሚያስቡ እየነገሩን ነው ።
እነዚህ ሰዎች  ኦሮሞ ቢሄዱ ፣ደቡብ ፣ጋንቤላ ፣ሱማል ፣ኣፋር ፣ትግራይ ኣማራ ፣ቤልሻንጎል ጉሙዝ ፣ሌሎች ኣሳናዎችስ ቢሄዱ  ከእንግዲህ ወዲህ ወደ ኣሀዳዊ ሰርኣት መዋቅር እጅ ገብተው ሊሸጡ ሊለወጡ ፣መሬታቸው ሊዘረፉ ይችላሉ ብላችሁ ተስፋ ታደርጋላቹሁ ? ሞኞች ናችሁ ። እንደምመለከታችሁ  ሁለም ነገር ኣጢናቹ ወደ ከባድ ኣለመግባባት ገብታችሁ ኣዋዳድቃችሁ ባታባላሹ ይሻላችዋል ።
እኔ እናንተ የለውጢ ሀይሎች  በኣሀዳዊው ስርኣት ህዋሓት ኢህአደግ  እያላችሁ   ድሮ እናንተ  በነበራችሁ እና እጃችሁ ያለበት   ኢህኣደግ ከነበረው ትእቢት ብልሽው ኣሳራር ሙሱና  ፣ምንም  እንኳ እናንተም በዛው ብትኖሩም ለዚሁ ኣፋኝ ስርኣት በህዝብ ተግል ተገፍታችሁ  ማንበርከካችሁ ለጊዜው ቢሆንም  ባለ ውለታችን ብትሆኑም ፤ኣሁን ግን ሁለት አመት ሳትሞሉ የእንደመር ጽንሰ ሀሳባችሁ  ለካስ ኣሀዳዊ ስርአት እንመስርት ነበር  ፕሮግራማችሁ። ትልቁ ነገር  ደግሞ ያለፉት  ስርኣቶች ወሸታሞች ኣጭበርባሪዎች ፣ለህዝብ የማያስቡ ፣ለሆዳቸው ፣ለቤተሰቦቻቸው የሌብነት ግብኣበሮቻቸው ብቻ የሚያስቡ ነበሩ።
 የኣሁኑ ብልጽግና  ኣሀዳዊ  ፓርቲ ግን እጅግ እጅግ ውሼታም ከመሆኑም በላይ ፤ለሁሉም ነገር በጥናት በምርምር የማይሄድ፤ ኣቅም ካጣም ከቂም በቀል የጸዱ ለሀገር የሚያስቡ ሙሁራኖች ኣማካሪዎች እንደመጠቀም ፈንታ  ብልጽግና ፓርቲ ለነገሮች በግብታውነት እየተመራ  ሀገራችን ወደ ኣልሆነ ጎዳና እየመራት ነው ።  በመሆኑሞ በኣሁኑ ጊዜ ኣሀዳዊ ስርአት ለመጣል ሚሊዮኖች መስዋእት የከፈለበት  መልሰን ኣሀዳዊ ስርኣት ከመቃብሩ ቆፍረን እናወጣለን በማለት  በሀገራችን በሁሉም ክልሎች ፣ዞኖች  ነፍጦኞች፣መሳፍንቶች የሚተኩ የኣሀዳዊ ፓርቲ  የምስሌነ መዋቅር ለሞሾም ሌት ተቀን እንቅልፍ እንዳጣቹሁ እንመለከታለን ።ይሀ ደግሞ ቆም ብላችሁ ኣስባቹሁ  መስመራችሁ ካላስተካከላችሁ  በራሳቹሁ  በኣንገታችሁ ገመድ ኣጥልቃችሁ  ሞት መፍረድ  ማለት ነው ።
                ይቀጥላል ፣
                      መቐለ  ፣
             07 / 08 / 20 12
ሁሉም ተንኮል በመጣል ለገዳዩ ኮሮና ቫይረስ እንከላከል ብሎም ለማጥፋት በህብረት ንነሳ!!
Filed in: Amharic