>

የአይን ብርሃን ማጣትና አደገኛ የሆነው የእጅ ስልክ አጠቃቀማችን!!! (ዶክተር ገበየሁ ተፈሪ)

የአይን ብርሃን ማጣትና አደገኛ የሆነው የእጅ ስልክ አጠቃቀማችን!!!

ዶክተር ገበየሁ ተፈሪ


* የእጅ ስልክ (Cell phone) ተጠቃሚ ከሆኑ የግድ ሊያነቡት የሚገባዎ መረጃ!

* የአይን ሀኪሙ አንዱን ወጣት ስለ Cell phone አጠቃቀም በተለይም በጨለማ የሚጠቀም ከሆነ ማኩላር ዲጀነሬሽን macular degeneration የተባለ የአይን በሽታ ያስከትላል ብለው ሲመክሩ ተመልክቼ ደስ አለኝ፡፡ 

* በሄፓታይትስ በሽታና በእርግዝና ጊዜ አልኮል አጠቃቀም ላይ ማስተማር ሲችሉ ሳይጠቀሙበት የቀሩበትን ሁኔታ አንስቼ ከአንዴም ሁለት ጊዜ ወቅሼ ነበር፡፡ አሁን ግን አመሰግንሁ፡፡ ታዲያ ሰለዚህ macular degeneration ሰለተባለ በሽታ በመጠኑም ሰፋ አድርጌ ትምህርት ለመስጠት ፈለግሁ፡፡ የአጅ ስልክ ተጠቃሚውን ብዛት ስመለከት ደግሞ ነገሩ አሳሳቢ መሆኑን ተረድቻለሁ፡፡ 
***
macular degeneration በአሜሪካና በቀረው አለም የአይን መታወር ምክንያት በመሆን አንደኛ ደረጃ የያዘ ህመም ነው፡፡ ይህ ህመም ግን በዕድሜ የበለፀጉ ሰዎች ላይ ነው የሚከሰተው፡፡ ዕድሜያቸው በ50 -60 አመታት በሆኑ ሰዎች ነው የሚታየው፡፡ ዋናው ባህሪው በአይን ውስጥ የሚገኘው ዕይታዎችን በደንብ ማየት የሚያስችለው ሬቲና የተባለ የአይን ክፍልን ስለሚጎዳ፣ ሰዎች ብዥ ያለ ዕይታ ይፈጠረባቸዋል፡፡ ይህም በተለይ የሚመለከቱት ነገር መሀሉ ላይ ብዥት ስለሚፈጥር በትከክል የተጣራ ዕይታ እንዳይኖራቸው ያደርጋል፡፡ ጋዜጣ ማንበብ፣ መኪና መንዳት የመሳሰሉ ተግባራትን ማከናወን ይሳናቸዋል፡፡ በዚህ ዕድሜ ክልል ለሚገኙ ሰዎች macular degeneration በሁለት መንገድ ይከሰታል፡፡ አንደኛው እርጥብ የሚሉት ሲሆን፣ ይህም በሬቲናው ጀርባ የሚገኙ የደም ሥሮች ከመጠን በላይ ያድጉና ደም መፍሰስ ወይም ፈሳሽ ወደ ሬቲናው በመዝለቅ ጉዳት በሚያደርስበት ጊዜ ነው፡፡ በዚህ ጉዳት ምክንያት የዕይታ አቅም በፍጥነት ይቀነሳል፡፡ በዚህ ሁኔታ የሚከሰተው የዕይታ መጋረድ የመጀመሪያ ምልክቱ፣ ቀጥ ያሉ መስመሮች በሚመለከቱበት ጊዜ፣ መስመሮቹ የተወላገዱ ሆነው መታየት ነው፡፡

ሁለተኛው አይነት macular degeneration ደረቅ የሚባለው ነው፡፡ የህ ደግሞ በዕደሜ መግፋት ምክንያት ሬቲናው እየሳሳ በመሄድ የሚፈጠር ሁኔታ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ከላይ እንደተጠቀሰው central vision መታወክ ነው የሚያስከትለው፡፡ ይሄኛው አዝጋሚ ሆኖ ነገር ግን በነዚህ ዕድሜያቸው በገፉ ሰዎች ከሰባ እሰከ ዘጠና በመቶ በሚሆኑት ላይ በመከሰት በmacular degeneration የዕይታ መጋረድ ዋናው ሰበብ ነው፡፡

ይህ የተለመደና የታወቀ ሁኔታ ሲሆን፤ አሁን ግን ይህ ቸግር በወጣቶች ላይ መከሰት በመጀመሩ የጉዳዩን አሳሳቢነት ጨምሮታል፡፡ ከኮምፒተሮችና ከእጅ ስልኮች የሚመነጨው ሰማያዊ ብርሃን አይን እንደሚጎዳ ይገመት ነበር፡፡ ይህን ሁኔታ በቅርቡ ባለሙያተኞች ባደረጉትና ይፋ ባደረጉት ጥናት ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በ journal Scientific Reports በቀረበው ጥናት መሠረት ይህ ሰማያዊ ብርሃን ወደ አይን በሚዘልቅበት ጊዜ፣ ሌሎች የአይን ክፍሎች ብርሃኑን የመቀነስ ወይም መልሶ የማንፀባረቅ ችሎታ ሰሌላቸው በቀጥታ ሬቲናው ላይ ያርፋል፡፡ ይህ ሰማያዊ ብርሃን በሬቲናው ላይ በሚያርፍበት ጊዜ ሬቲናው እንደምላሽ ኬሚካሎችን ያመነጫል፡፡ እነዚህ ኬሚካሎች ግን photoreceptor cells የሚባሉ ዕይታን ተቀብለው ምን መሆኑን እንድናውቅ የሚያደርጉትን ሴሎች ይጎዳል፡፡ ጉዳቱም ዘለቄታ ያለው በመሆን ከላይ የተጠቀሰው የምናየው ነገር መሀከሉ ላይ ብዥታ ይፈጥራል፡፡ የዚሁ ጥናት ሳይንቲስት የሆኑት ሰው እንደሚሉት ከሆነ፣ “ይሀ ሰማያዊ ብርሃን መርዝ ነው”

ከላይ የተጠቀሰው ስለጉዳቱ የተረጋገጠ ሳይንሳዊ ምክንያት ነው፡፡ እንግዲህ ይህን ሰማያዊ ብርሃን የሚያመነጩ ዕለት ከለት የምንጠቀምባቸው ዕቃዎች ዋናው የእጅ ስልክ ሲሆን፣ ቴሌቢዥኖችና፣ ኮምፒተሮችን ይጨምራል፡፡ አንዳንድ Cell phone ካምፓኒዎች የሰማያዊ ብርሃን ማጣሪያ ነገር ስልኩ ላይ ይጨምራሉ፡፡ በተፈጥሮ፣ የቫይታሚን E ውጤት የሆነ alpha tocopherol የተባለ ሞሎኪል ይህንን ለመከላከል ይረዳል፡፡ ዕድሜያቸው በገፉ ሰዎች ግን ይህ የመከላከል አቅም እያነሰ ሰለሚሄድ በ macular degeneration ሲጎዱ ይታያል፡፡

በወጣቶች ላይ ከላይ የተጠቀሱትን ዕቃዎች በተለይም የእጅ ስልክን በጨለማ አዘውትሮ መጠቀም ለዚህ ጉዳት እንደሚያጋልጥና ለአይነ ስውርነት እንደሚዳርግ ነው፡፡ ሁኔታው አዝግሞ ሰለሚከሰት አስቀድሞ መጠንቀቅ ጥሩ ነው፡፡

በዚህ በሰማያዊ ብርሃን ምክንያት የሚጎዱት photoreceptor cells ሲጎዱ ወይም ሲሞቱ ለዘለቄታው ነው፡፡ ማለትም ተመልሶ የማገገም ሁኔታ የለም፡፡ የአይን ዕይታዎ ምልክት እስኪሰጥዎ መጠበቅ ተገቢ አይደለም፡፡

ሰለዚህ በጨለማ የእጅ ሰልክ ሆነ፣ ታብሌት የሚባሉ አነስ ያሉ ኮምፕዩተሮችን መጠቀም ማቆም

መጠቀም የግድ ከሆነ ደግሞ የፀሐይ ብርሃን መከላከያ መነፀር መጠቀም የግድ ነው፡፡ በጨለማ የፀሐይ መነፅር ማድረግ መቼም ሰውን ሳይስገርም አይቀርም፡፡

ለወደፊት የሚገዙት ሰልክ፣ blue light filter ያለው ቢሆን ይመረጣል፡፡

Filed in: Amharic