>

ኮረና ቫይረስን ሳይጨምር በሰው ልጅ ታሪክ የተከሰቱ አደገኛ ወረርሽኞች ፤  (ታጠቅ መ. ዙርጋ)

Aኮረናቫይረስን  ሳይጨምር በሰው ልጅ ታሪክ የተከሰቱ  አደገኛ ወረርሽኞች ፤ 

 

ታጠቅ መ. ዙርጋ

 

 

በሽታ፣ ሞት፣ ድህነት ፣ ጦርነት ፣ ጭቆናና ብዝበዛ የሰው ልጅ ዋንኛ ጠላቶች ስለመሆናቸው ለሁሉም ግልጽ ነው። ጦርነት፣ ጭቆናና ብዝበዛ  የተከሰቱት ማኅበረሰብ በመደብ ከተከፋፈለ በኋላ ስለመሆኑ ከማኅበረስብ የዕድገት ጉዞ ከ(historical materialism) መማር ይቻላል ። 

የሰው ልጅ ኅልው ከሆነበት ታሪካዊ ወቅት አንስቶ ስዎች ከተለያዩ ቀላል ፣ከበድ ካሉና እጅግ በጣም ከበድ ካሉ በሽታዎች ጋር አብሮ ኖሯል ፤እየኖረ ነው፤ ወደፊትም አብሮ ይኖራል።ስለሆነም በሽታ የሰዎች ሁለተኛ ተፈጥሮ ነው ማለት ይቻላል።

በየዘመኑና በየወቅቱ የተከሰቱ በሽታዎች በብዙ ምሊዮን የሚቆጠር የሰው ሕይወት ቢቀጥፉም፤ የሰው ልጅ ከምድር ገጽ ማጥፋት አልቻሉም። “ችግር ብልሃት ይፈጥራል -necesisty is the mother of invention”  እንደሚባለው የስዎች የማሰብ፣ የፈጠራና የምርምር ችሎታ ሁሉንም በሽታዎች ማጥፋት ባይችልም ፤በየዘመኑና በየግዜው ብቅ ላሉት በሽታዎች መፈወሻ ወይም መከላኬያ መድሃኒት እያገኘ ተጉዟል። በተለይም የህክምና ሳይንስ (medical science) ዕውቀት ማደግ ፤ የስው ልጅ በአብዛኞች  አስከፊ በሽታዎች ላይ ድል ተቀዳቷል።

ለምሳሌ ከ3000 B.C /ዓ.ዓ ጅምሮ የአሁኑ ኮረናቫይረስን  ሳይጨምር፣ በእኛው ዕድሜ እውን የሆኑትን (HIV and AIDS,Ebola, SARS, MERS  viruses etc) ጨምሮ እጅግ ከከፉ 20 ኢዓለም-አቀፋዊና ዓለም አቀፋዊ  ወረርሽኝ በሽታዎች ተጋድሎ ተወጥቷል ። 

ገዳያቸውን/ተጻራሪያቸ ውን ወይም የመግደል አቅማቸውን የሚያዳክም  መድሃኒቶች በመቀመም ፣ ማኅበራዊ የአካል ግንኙነት በመገደብ ፣የመጸዳች ትምህርት በመስጠት  ወዘተርፈ በሽታ/ዎች (ለሰው ተገዢ እንዲሆኑ  እንጂ ሰው ለበሽታዎች እንዳይገዛ  – disease/s to surrender to humans/subjects   not vise versa) ለማድረግ እየተጋደለ አሁን ላለንበት 21ኛው ክ/ዘመን  ደርሰናል።

እ.ኤ አ (1820 -1895) ዓ.ም የኖረው እንግሊዛዊው  ፍሬዴሪክ ኤንግልስ የተባለ ሰው (Dialectics of Nature) የተፈጥሮ ኩነት በተሰኘው መጻፉ  በዚህ ዓለም ያለ ‘ተቃራኒው የሚኖር ምንም ነገር የለም ብሎዋል’ ። ከፍልስፍናው ፥ በሽታና ፀረ-በሽታ፣ ፍቅርና ጥላቻ፣ ሃዘንና ደስታ፣መኖርና መሞት፣በጋና ክረምት፣ጥቢና በልግ፣ ቀንና ለሊት፣ማታና ጠዋት፣ ከተጠጣ ይሸናል፣ከተበላ ዓይነ-ምድር ይደረጋል  ወዘተርፈ መጥቀስ ይቻላል ። ከኤንግልስ ፍልስፍናና ከዚህ ቀደም ለተከስቱ ቫይረሶች ማምከኛ ከማ ግኘት አንጻር ፤ ለኮረና ቫይርስ መድሃኒት የማይገኝበት ምክንያት አይኖርም፤ በቅርብ ግዜ ፀረ-ኮረናቫይረስ ንጥረ ነገር ይገኛል ባይነኝ ። 

ምክንያቱም ፦የተለያዩ በሽታዎች፣ተውሳኮችና ቫይረሶች – አጥፊዮቻቸውን  ወይም ተከላካያቸውን የማግነት ታሪክ የሚያስረዳው ፤ የአንድን በሽታ ጸረ ወይም  መድሃኒት የሚቀመመው ወይም የሚፈለገው በሽታው ገሃድ ከሆነ በኋላ እንጂ ከዚያ በፊት አይደለም ፤ በወደፊት ሳይንሳዊና ቴክኖሎጂያዊ ምርምር የነገን በሽታ ማውቅና  የበሽታውን መድሃኒት መቀመም ይቻል እንደሆን እንጂ ፤ እስካሁን ስለነገን በሽታና መድሃኒቱ የማወቅ እውቀት አልነበረም።

ኮረናቫይረስ ከዚህ ቀደም ከተከሰቱ የወረርሽኝ በሽታዎች ሁሉ የከፋ ያደረገው ፤ እጅግ በጣም ከሚፈሩት የኒዩክለር እና የጠፈር ጦርነት (nuclear and star war) የበለጠ የዓልምን ማኅበረሰብ  ያርበተበተው ለምንድነው? ከጉግልና ከማህበራዊ ገጽ ካገኘኋዋቸው ምክንያቶች ጥቀቶቹ ፦( 1) በመዛመትና በመግደል ፍጥነቱ፣ ለምሳሌ ስለበሽታው  በኢይፋ የተገለጸው እ.ኤ.አ ዴሰምበር መጨረሻ ገደማ ሲሆን ፤ ከመነገሩ በፊት 88 000 በበሽታው እንደተለከፉና 3000 ሰዎች እንደሞቱ ተዘግቦዋል (2) አስቃቂ ህመም ያለው በመሆኑ (3) በሽታን የሚካላከሉ ህዋሳት ክፉኛ የሚያጠቃ በመሆኑ (4) ከሰው አልፎ ሌሎች እንስሳትንም  የሚመርዝ በመሆኑ (5) ሌላ በሽታ ያለበት ሰው በኮሮናቫይረስ ከተጠቃ ያንን በሽታ የማባባስ ባህሪ በመኖሩ (6) ድብቅ፤ተሽሎክላኪና መሰሪ ባህሪያት ያሉት በመሆኑ (7) ከሃቻማና አምና፣ከአምና ዘንድሮ፣ከትላንት ዛሬ ፤ የዓለምን ማህበረስብ በጣም በአጭር ግዜ የሚያገናኙ የትራንስፖርት አውታሮች በመፈጠራቸው  ቫይረሱ ከመቅስፈት ወደ ሁሉንም ፦ አካባቢ፣አገራት፣ ንፍቀ አሁጉራትና አሁጉራት በመዳረሱ (8) በሽታው ለሁሉም የመጣ ፣ መደብ፣ዘረመር፣ጾታ፣ቀለም ወዘተርፈ አልባ በመሆኑ (9) በሃብት ክምችትና በሥልጣን መከታ ከሰፈው ሕዝብ ተለይተው በሽታው ያልደረሰበት አገር ሄጄ እቀማጣለሁ ፣ ምርጥ ሃኪሞች ያሉበት አገር  ሄጄ እታከማለሁ የማይባልበት በመሆኑ ።     

ኢትዮጵያንም ጨምሮ የሶስተኛው ዓለም አቀፍ አገራት ባለሥልጣናት  የአገርና የሕዝብ ሃብት በመጠቀም ፤ ሃብታሞች (ሃብቱ ከህዝብ የተዘረፈም ይሁን በላብ የተገኘ)  ትንሽ ጠንከር ያለ በሽታ ሲዛቸው ፥ ወደ አሜሪካ፣ለንደን፣ ጀርመን፣ፍራንስ፣ ዴንማርክ፣እስዊድን ፣ቢያንስ ቢያንስ ደቡብ አፍሪካና ታይላንድ  መጭ ብለው በመታከም ከበሽታቸው ይፈወሱ ነበር፤ ዕድሜያቸውን ያራዘሙ ነበር ። ኮረናቫይረስ ግን ይህንን ቅንጦት ገድቧል። 

አሁንም ቢሆን  ባለሥልጣኖች፣ሃብታሞቻና ቅንጥዎች ኮረናቫይረስ እንዳይደርስባቸው ፣ከደረሰባቸውም  ለመከላከል ከሰፊው ሕዝብ የተሻለ አቅም (resource) እና እውቀት የሚጠይቅ ዜዴ/ መካኒዝም የላቸውም ማለቴ አይደለም። 

ምክንያቱም በጣም በጸዳና  ዘመናዊ ቪላ ቤት ይኖራሉ፣ በዘመናዊ (ባኞ፣ሻወርና የእጅ መታጠቢያ ይታጠባሉ፣ ሽንት ቤት ይጸዳዳሉ)። ኦርጋኒክ ውሃ መጠጣት፤ ኦርጋኒክ ምግብ መመገብ ይችላሉ። በሽታውን ለመከላከል  ሁ(WHO) ያወጣቸውን መስፈርቶች ለምሳሌ ፦ የአፍንጫና የአፍ መሸፈኛ ማስክ፣ ፀረ-ተውሳክ ፈሳሾች(ant-infect ant detergent) የማግኘትም ሆነ የመግዛት፣ ሰፋፊ ሳሎን፣ ሰፋፊ የቤትስብ መዝናኛ ክፍል፤ሰፋፊ  መመገቤያ ክፍል ፣ በርካታ መኝታ ክፍሎች ወዘተርፈ ስለሚኖርዋቸው ተራርቆ መቀመጥ ፣መቆም ፣ መመገብና መተኛት ስለሚችሉ ፤ያለመጠጋጋት (social distancing) ችግሮች የሉባቸውም። ላቅ ያለ ችሎታ አላቸው በሚባሉ አገር በቀለ የግል  ሃኪሞች መታከም ይችላሉ ፤መኪና ስለሚራቸው በአደባባይ ከሰፊዩ እግረኛ ሕዝብ ጋር  መጋፋት አይኖርባቸውም። ኮረናቫይረስ- የማህበረሰቡ ጎስቋሎችን (socially destituted) የሆኑትን  በቀላሉ ያጠቃል /ይገላል ወዘተርፈ።

በኮረናቫይረስ (Covid-19) ክስተት ላይ እይታዎች ወይም ምልከታዎች ፦ያለ ምክንያት የሚሆን ነገር የለም። ሁሉንም ኩነቶች ምክንያታዊ ናቸው ። ስለሆነም  (Covid-19) ኩነትን በተመለከተ (as why Covid-19 has happened) የተለያዩ ምክንያቶች ተሰንዝሯል። ከእነዚህም ጥቂቶቹ እነሆ

  1. የዓለም መጨረሻ -Armageddon ምልክት ነው
  2. (2) የሰዎች ሃጥያት ስለበዛ ለመቀጣጫ የመጣ ነው
  3. (3) ስዎች ወደ መለኮታዊ ሃይል እንዲያተኩር  ለማስጠንቀቄያ የመጣ ነው
  4. (4) እኛ ሰዎች በምድርና በጠፈር ላሉ ነገሮች ሁሉ ንጉስ እንዳልሆን ሊነግረን የመጣ ነው
  5. (5) ምድር የሰው ብዛት መሸከም ስላቃተው  ባለው ተፈጥሯዊ መንፈሱ/spirit ሃይል ተጠቅሞ ሊቀንሰን የመጣ ነው
  6. (6) ኮረናቫይረስ የቻና ላቦራቶር ውጤት ሊሆን ይችላል ፤ ለማስረጃ ቀጥሎ ያለውን ሊንክ ክሊክ VID-20200321-WA0014.mp4 አድርጉ ።

 ከላይ  እንደጠቀስኩት – በዚህ ባለንበት ምድርና ህዋ ያለተቃራኒዩ የሚኖር ምንም ነገር ስለሌለ ሳይንሳዊ አብዮትና  ሳይንሳዊ ቴክኖሎጂ አውንታዊ ጥቅም እንዳላቸው ሁሉ አሉታዊ ይሁንታዎች አሏቸው

(7) የተሃዲሶ ሊበራሎች ቾርኔቤል -chernobyl  ነው ፤ ካፒታሊስቶች ሃብት ለማካበት፤ የተፈጥሮ አካባቢ ከመደምሰስና የአየር መበከል(pollution) ጋር የተዛመደ ነው ፤ chernobyl – እ.ኤ.አ 26አፕሪል 1986 ፕርፕያት በተባለ  ከተማ አጠገብ የፈነዳው የረሺያ ኒዩክለር ክምችት ማለት ነው

(8) የግሎባላይዜሽን ሄደት ለማናጋት ወይም ተጽኖ ለማድረግ የመጣ ነው

(9) ግብረሶዶም ስለበዛ የመጣ ነው ወዘተርፈ ይላሉ ።

Filed in: Amharic