ቤት ለቤት የሚባል የኮሮና ምርመራ የለም!!
ቅዱስ ማህሉ
* ታኬ ሲቦተረፍ “ቤት ለቤት እየዞርን የኮሮና በሽታን የደም ምርመራ እናደርጋለን” ብሎልሀል። ስማ ! ሰዉዬ እነ አሜሪካም በቂ ባለሙያና በቂ መመርመሪያ ስለሌላቸው ቤት ለቤት እየሄዱ አልመረመሩም እስካሁን በአለም ላይ አንድም ሃገር (እደግመዋለሁ አንድም ሃገር) ቤት ለቤት እየዞረ የኮሮና በሽታ የደም ምርመራ ያደረገ የለም!! ሙቀት መለካት በየትኛውም መመዘኛ ምርመራ ሊባል አይችልም !!
***
የሳንባ ቆልፍ(ኮሮና ቫይረስ)ን ቤት ለቤት ለማዳረስ ካልሆነ በቀር ቤት ለቤት የሚባል ህክምና እስካሁን የትም ሃገር አልተጀመረም። ግምባር ላይ ሙቀት መለኪያ ደግኖ የሙቀት መጠን መለካት እና የሳንባ ቆልፍ(የኮሮና ቫይረስ) ምርመራ ምንም ግንኙነት የላቸውም። #በድሬዳዋ እና #በአዲስ አበባ የታሰበው የቤት ለቤት ምርመራ ሰዎችን በብዛት ለቫይረሱ ተጋላጭ ያደርግ እንደሆን እንጅ ከምርመራ ጋር ምንም አይቆራኝም። ግምባራቸው ላይ እኮ ሙቀት እየለኩ የለባችሁም ያሏቸው ተጓዦች ናቸው አሁን ከማህበረሰቡ ውስጥ ኮሮና ተያዙ እያሉ መልሰው የሚያወጧቸው። የሰውነት ሙቀቱ ከፍተኛ የሆነን ሰው ሁሉ ወደ ማግለያ ጣቢያ መውሰድም ቫይረሱን ያስፋፋል እንጅ አይቀንሰውም። የሰውነት ሙቀት የሚጨምረው በኮሮና ቫይረስ ብቻ አይደለም። ቤት ለቤት የሚባለው አሰራር የሳንባ ቆልፍን ቤት ለቤት የሚያሰራጭ አደገኛ አሰራር ነው። የቤት ለቤት የሚባል ህክምና እንሰጣለን የሚሉት ሰዎች ስራ ካጡ አርፈው በቤታቸው እንደሌላው ሰው ቢቀመጡ የተሻለ ነው። ለሳንባ ቆልፍ የቤት ለቤት የሚባል ህክምና የለም! በቤቱ አርፎ የተቀመጠን ሰው ለመበከል በየቤቱ አትሂዱ!!!