>
5:13 pm - Saturday April 19, 2414

የሳንባ ቆልፍ(ኮሮና ቫይረስ) እና የወባ መድሃኒት ሲደመር ፖለቲካዊ ውሳኔ!!!  (ቅዱስ ማህሉ)

የሳንባ ቆልፍ(ኮሮና ቫይረስ) እና የወባ መድሃኒት ሲደመር ፖለቲካዊ ውሳኔ!!!

 ቅዱስ ማህሉ
 
በሳንባ ቆልፍ ተይዘው ሞት አፋፍ ላይ የሚገኙት ግን ምንም ሌላ የሚሞከር መድሃኒት በሌለበት ወቅት የወባ መድሃኒትን እንደ አማራጭ ሊወስዱ ይችላሉ። ሳይውጡም ሊሞቱ ይችላሉ! ምናልባት መድሃኒቱን ውጠው ሊድኑ ይችላሉ! ሊሞቱም ይችላሉ!!!
 
አሜሪካ ውስጥ ወባ የለም። አሜሪካ ወባን ከሃገሯ ካጠፋች 71 ዓመታት ተቆጠሩ። እኛ ለወባ መድሃኒትነት የምንጠቀምበት መድሃኒት አሜሪካ ውስጥ ለሉፐስ በሽታ ህክምና ጥቅም ላይ ይውላል። በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የወባ መድሃኒት እያልኩ የምጠቅሰው በኢትዮጵያ መድሃኒቱ ጥቅም ላይ ከሚውልበት አንጻር ብቻ ነው። የአሜሪካ የመድሃኒት ቁጥጥር መስሪያ ቤት በሳንባ ቆልፍ የሚታመሙ ሰዎች አማራጭ መድሃኒት አጥተው ዝም ብለው ከሚሞቱ በፍቃደኝነት የወባ መድሃኒት ከፈለጉ ዶክተሮች እንዲሰጧቸው መድሃኒቱን ለሉፐስ በሽታ ቀደም ሲል ጥቅም ላይ እንዲውል ከጸደቀበት ሳይንሳዊ ምክንያት ውጭ ጥቅም ላይ እንዲያውሉት ያለበቂ ሳይንሳዊ የምርምር ድጋፍ በጥድፊያ የተላለፈ የፖለቲካ ውሳኔ ነው።
መስሪያ ቤቱ ይህን ፍቃድ ከመስጠቱ በፊት ታማሚዎቹ መድሃኒቱን መጠቀም ቢፈልጉ እንኳ ዶክተሮቹ ያለመስጠት መብት ነበራቸው። አሁን ግን ስለጸደቀ የዶክተሮቹ መብት መድሃኒቱን መከልከል ሳይሆን የሚያስገኘውን ጥቅም እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለታማሚው ነግሮ የታማሚውን ፍላጎት መፈጸም ብቻ ነው። ምክንያቱም ትግሉ መድሃኒት ከሌለው ወረርሽኝ ጋር ነው።
በሳንባ ቆልፍ የሚያዙት ሰዎች ምንም ሳይሞክሩ እንዳይሞቱ ለመርዳት እና ለታማሚዎቹ ተስፋ ለመስጠት ፖለቲከኞች ያዘዙት መድሃኒት ነው። በአንዳንዶች ላይ ጥቅም እንጅ ጉዳት እንደሌለው ያውቃሉ። የወባ መድሃኒት ተጓዳኝ ጉዳት የሳንባ ቆልፍ ከሚፈጥረው ኢንፌክሽን የሚብስበት አጋጣሚ ብዙ ነው።
በእድሜ የገፉ እና ሌላ ተጨማሪ ህመም ያለባቸውን ሰዎች( ለምሳሌ የስኳር ህመም፣የጉበት ህመም፣የልብ፣የደም ግፊት ወዘተ) ከማዳን ይልቅ 30 በመቶ ያህል ወደሞት የሚያቀርብ ትኬት የመቁረጥ ያህል መሆኑን ጥናቶች ይጠቁማሉ። የወባ መድሃኒት የተፈጥሮ የበሽታ መከላከል አቅማችንን ያዳክማል። የሳንባ ቆልፍ በሽታ ደግሞ ከ80በመቶ በላይ ባብዛኛው በቤታችን ውስጥ ያለምንም ተጨማሪ ህክምና የሚድን ህመም ነው። ያለህክምና መዳን የሚችሉ ሰዎች የወባ መድሃኒቱን ቢውጡት በኮሮናው ከሚደርስባቸው ኢንፌክሽን በላይ በተጓዳኝ መድሃኒቱ የሚያደርስባቸው ጉዳት ሊበልጥ ይችላል።
በሳንባ ቆልፍ ተይዘው ሞት አፋፍ ላይ የሚገኙት ግን ምንም ሌላ የሚሞከር መድሃኒት በሌለበት ወቅት የወባ መድሃኒትን እንደ አማራጭ ሊወስዱ ይችላሉ። ሳይውጡም ሊሞቱ ይችላሉ። ምናልባት መድሃኒቱን ውጠው ሊድኑ ይችላሉ። ሊሞቱም ይችላሉ። በአሁን ሰዓት የወባ መድሃኒትን ለኮሮና በመዋጥ እና ባለመዋጥ መካከል ያለው ልዩነት እዚህ ድረስ ነው። ከዚያ ይልቅ አዚትሮማይሲን የሚባለው መድሃኒት የታችኛው የመተንፈሻ አካላት ችግርን ሁሌም ለማቃለል የሚታዘዝ መድሃኒት ስለሆነ እና ኢንፌክሽንን ለመቀነስ ጥቅም ላይ ስለሚውል ለምሳሌ እንደ አስም ያለ ታያያዥ ህመም ያለባቸው ሰዎችም ሆነ ጤነኛ ሰዎች በሳንባ ቆልፍ ህክምና ወቅት ቢጠቀሙበት የሚያስከትለውን ኢንፌክሽን በከፍተኛ ሁኔታ ይከላከላል ተብሏል። መድሃኒቱ ግን በሃኪም የሚታዘዝ ነው። በተጨማሪም በሳንባ ቆልፍ የተያዙ ሰዎች በጀርባችን የሚገኘው አብዛኛው የሳንባ ክፍል ላይ ጫና ስለሚበዛበት እና የመተንፈስ ችግራችንን ስለሚያባብስብን ነው ተብሏል። በጎን መተኛት እፎይታን ቢፈጥርልንም የተሻለው ግን በሆድ መተኛት ነው ተብሏል። የወባ መድሃኒትም አንዳንዶች በሃኪም ምክር ጭምር ከወዲሁ ዋጡ ለሳንባ ቆልፍ መከላከያ ይረዳል ተብለው በኢትዮጵያ እየዋጡ ነው።ኮሜንት ላይ ያለው ያስቀመጥኩት ካንድ ሰው የደረሰኝ መልዕክት ነው። አንድ ሙሉ ቤተሰብ በዶክተር ትዛዝ ይሄን እያደረገ ነው።ከብዙዎች የሚነገረኝም ሆነ የሚጠይቁኝ ይሄንኑ ነው። እኔ ከታች ያያዝኳቸውን ጥናቶች አንብቤ ይሄን ጽሁፍ በአጭሩ ጽፊያለሁ። ባጭሩ ሳንባ ቆልፍን የሚከላከለው ባለን የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅም ልክ ነው። የወባ መድሃኒት ይሄን አቅማችንን የሚቀንስ እንጅ የሚጨምር አይደለም። የወባ መድሃኒት አሜሪካ ጥቅም ላይ የሚውለውም ሉፐስ የሚባለውን በራሳችን የሰውነት መከላከያ ሴሎቻችንን የሚያጠቃን ህመም የሰውነት መከላከያ አቅማችንን በማዳከም ስቃይ ለመቀነስ እንዲረዳ ነው። በሳንባ ቆልፍ(ኮሮና ቫይረስ) አንጻር ሲታይ ውጤቱ ተቃራኒ ነው። ብቸኛ መዳኛችን የሆነውን የሰውነታችን የበሽታ መከላከል አቅም በወባ መድሃኒት ባንሸረሽረው ጥሩ ነው። በዚያ ላይ ሳያመን መወሰዱ ደግሞ ሌላ ተጨማሪ ጉዳት ነው። ፈረንጆቹም እኮ ቢሆን የመጨረሻ አማራጭ ሲጠፋ ታማሚው ተስፋ እንዳይቆርጥ እንዲሞክር እድል ለመስጠት እንጅ ፍቱን መድሃኒት ነው አላሉም። እኔ ለሁላችንም የምመኘው መጀመሪያ እንዳይዘን ነው። ከተያዝንም በኋላ የመጨረሻ አማራጭ አጥተን “መሞቱ ካልቀረ ይሄን ሞክሮ ይሙት” የሚባልበት ደረጃ ላይ ሳንደርስ እንድንድን ነው። ለሁሉም እግዜር ይርዳን!!
[*ተጨማሪ*ሌላው ከብዙ ሰዎች በደረሰኝ አስተያየት መሰረት ብዙ ሰዎች ነጭ ሽንኩርት፣ፌጦ፣ ኑግ፣ ጥቁር አዝሙድ ወዘተ ነገሮችን ቀላቅለው እንደ ሻይ አፍልተው በፔርሙስ ሞልተው ቀኑን ሙሉ እየተጎነጩ ልባችንን ደከመን እያሉ ነው። ወዳጆቼ በኮሮና ፍራቻ ልባችሁን አታቃጥሉ እንጅ! ትኩስ ነገር ቶሎ ቶሎ ጠጡ የተባሉት የታመሙት ሰዎች ናቸው። ለእነሱም ቢሆን የሚጠጡት እና የሚጠቀሙት ነገር ላይ ምን ያህል መጠቀም እንዳለባቸው ከራሳቸው ልምድ አንጻር ተናገሩ እንጅ ነጭ ሽንኩርት ቀኑን ሙሉ እየጠጣችሁ ልብን እና ጨጓራችሁን አቃጥሉ አላሉም። እየተጠነቀቅን!]
የወባ ክኒን እና ኢንፌክሽኑን በተመለከተ የተካተቱት ምክሮች ከሚከተሉት ሁለት የሳይንስ የምርምር ጽሁፎች/ጆርናሎች የተገኙ ናቸው።
ምንጭ 1፡ Evidence of Rapid Antiviral Clearance or Clinical Benefit https://www.sciencedirect.com/…/arti…/pii/S0399077X20300858…
ምንጭ 2፡ Fatal toxicity of chloroquine or hydroxychloroquine with metformin in mice https://www.biorxiv.org/content/10.1101/2020.03.31.018556v1
Filed in: Amharic