>

ለየመን እና ሳውዲ ተጓዦች ጥብቅ ማሳሰቢያ ! (ነቢዩ ሲራክ)

ለየመን እና ሳውዲ ተጓዦች ጥብቅ ማሳሰቢያ 

ነቢዩ ሲራክ
* ወገኖቼየጥይት ራት እንዳትሆኑ  !
 ለየመን እና ሳውዲ መካከል በምትገኘውና
ራጎ የምትባል መሸጋገሪያ ቦታ በሽዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአደጋ ተከበዋል። በርካታዎች በጅቡቲና በሶማሌ አደደርገው የመን የገቡ ዜጎች በበርሃው ንዳት ከመሰቃየት ባለፈ ከሳምት በፊት ቁጥራቸውን መግለጽ የማልፈልገው ኢትዮጵያውያን በበርሃው ሞተዋል 🙁
    በግምት 3,500 አካባቢ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ዋዲ አህመድ በተባለ የየመን ሳውዲ ድንበር መተላለፊያ ክፍል ብቻ ይገኛሉ ። የሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች ኮሮና ከገባ ወዲህ ልዩ የተጠናከረ ጥበቃ እያደረጉ ነው። በሁቲና በኢራን በኩል በድንበር በኩል ሰርገው በሚገቡ ኮሮናን የማሰራጨት ተንኮልና ሴራ ስለሚጠረጠር ጥበቃው የከበደ ነው። ድንበር የሚያቋርጡትን በአልሞ ተኳሽ የድንበር ጠባቂዎች ጠመንጃ  እስከመግደል የደረሰ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይችላል። የማቀብለውን መረጃ ማመን ካቃታችሁ የአሲርና የጄዛን የጅዳ ቆንስል ተወካዮች በጥይት ተመትተው ነፍሳቸው ስለሚቀጠፍ በድንበር የሚገቡ ኢትዮጵያውያን ጠይቋቸው!
    እናም ወሬ አላብዛባችሁ ፣ በአሁኑ ሰዓት በየመን በኩል የሚሰደደው ኢትዮጵያዊ ወጣት ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ጭብጥ መረጃ ደርሶኛል ስላችሁ እመኑኝ …ይህን መረጃ የማስተላልፍበት ዋና ምክንያት ወላጆች በአሳር በመከራ በድህነት ያሳደጓቸው ልጆቻቸው ይጠብቁ ዘንድ ለመምከር በሚል ነው። በሞቱ የየመን ሳውዲ መንገድ ለመሄድ ለተዘጋጁት  ወንድም እህቶች በቦታው በተጨባጭ ያለውን መረጃ ተረድተው ከመጓዝ ይታቀቡ ዘንድ አበክሬ እመክራለሁ ።
  በተረፈ ዛሬም እንደ ቀደመው ከቦታው ባሉኝ ታማኝ ምንጮች ደርሶኝ የማቀብላችሁን መረጃ ትክክለኛነት ትረዱ ዘንድ እንደ አስፈላጊነቱ ሁኔታውን የሚያሳይ ቪዲዮ የማቀርብ ይሆናል ። የወንድም ምክሬን ስሙ ! ከቤታችሁ ፣ ከሀገራችሁ አትውጡ  !
እስኪ ቸር አሰማን
መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓም
Filed in: Amharic