>

ኮሮናን እየተዋጋን ፍትሕን እንጠይቃለን! የታገቱት ተማሪዎች የት ናቸው?

ኮሮናን እየተዋጋን ፍትሕን እንጠይቃለን! የታገቱት ተማሪዎች የት ናቸው?

ያሬድ ሀይለማርያም
ምንም እንኳን በኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ አይምሯችን ቢወጠርም እና ከቫይረsu ጋር በሚደረግ ጦርነት ሽብር ውስጥ ብንሆንም ታፍነው ከተወሰዱ አራት ወር ግድም የሞላቸውን አሥራ ሰባት ሴት ተማሪዎች ጉዳይ ልንዘነጋው አንችልም። ተዋሪዎቹ የት ናቸው? ጉዳዩን ለእኔ ተውሉኝ ያለውስ መንግስት ምነው ዝም አለ? ተማሪዎች በጠቅላላ ወደየቤታቸው ሲመለሱ እነዚህ ልጆች እንደወጡ መቅረታቸው ትልቅ አገራዊ ክሽፈት አይደለም ወይ? ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት የሚልኩት እኮ መንግስት ላይ እምነት ጥለው ነው።
መንግስት አለ በለው ነው። መንግስት በብዙ መልኩ ሕዝብ የጣለበትን እምነት እያንጠባጠበ እየጣለው ይመስላል። በቅርቡ የኦሮሚያ ክልል ም/ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ ልጆቹን በማፈን በሚጠረጠረው የኦነግ ሽኔ ጦር ላይ የበላይነታቸውን የተቀዳጁ መሆኑን በመግለጽ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረውን የኢንተርኔት መስመር እንዲለቀቅ ማድረጋቸውን ሲነግሩን ሰለ እነዚህ ልጆች ግን አንድም ቃል ሳይተነፍሱ ቀርተዋል። አሁንም ሰሚ ካለ፤ እደግመዋለው ሰሚ ካለ የፍትህ ያለ እንላለን። መንግስት የደረሰበትን የምርመራም ሆነ የክትትል ውጤት ምንም ይሁን ምን ለሕዝብ እና በተለይም ለቤተሰቦቻቸው ሊያሳውቅ ይገባል።
ኮሮናን እየተዋጋን ፍትሕን እንጠይቃለን
Filed in: Amharic