>

ዛሬም ወደ 400 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ ይመለሳሉ ! (ነቢዩ ሲራክ)

ዛሬም ወደ 400 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ ይመለሳሉ !

 

ነቢዩ ሲራክ 
ከዚህ ቀደም በሳውዲ አየር መንገድ መጥተው የማረፊያ ፍቃድና ዝግጅት ባለመደረጉ እንዲመለሱ የተደረጉትን 390 ኢትዮጵያውያን ጨምሮ ቁጥራቸው ከ1,000 በላይ ኢትዮጵያውያ አዲስ አበባ ገብተዋል!!!
   ዛሬ ቅዳሜ መጋቢት 26 ቀን 2012 ዓም 400 የሚጠጋ ቁጥር ያላቸው ከእስር የተለቀቁ ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ጅዳ ተነስተው አዲስ አበባ ወደ  ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። በትናንትናው እለት በሳውዲ አየር መንገድ ሁለት በረራዎች ከዚህ ቀደም በሳውዲ አየር መንገድ መጥተው የማረፊያ ፍቃድና ዝግጅት ባለመደረጉ እንዲመለሱ የተደረጉትን 390 ኢትዮጵያውያን ጨምሮ ቁጥራቸው ከ1,000 በላይ ኢትዮጵያውያ አዲስ አበባ ገብተዋል ።
    ትናንት የገቡትና ዛሬም ይገባሉ ተብለው የሚጠበቁት ኢትዮጵያውያን አብዛኛው በሳውዲና በየመን ድንበር ጥሰው ሲገቡ የተያዙና በድንበር ከተማዋ በጄዛን ወህኒ በእስር ላይ የነበሩ መሆናቸው አረጋግጫለሁ።
  ተመላሽ ዜጎችን በሚመለከት የጅዳ ቆንስል የበላይ አምባሳደር አብዱ ያሲን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከከፍተኛ የሳውዲ ፖስፖርት መ/ቤት   ባለስልጣን ጋር በምክክርና ቅንጅት ዜጎችን ወደ ሀገራቸው መመለስ እንደተጀመረ የጅዳ ቆንስል ጀኔራል አምባሳደር አብዱ ያሲን  አስታውቀዋል።
   ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናት የገቡት ኢትዮጵያውያን በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ  አስፈላጊው ምርመራ እየተደረገላቸው ወደ ማቆያ መወሰዳቸውን የሚያሳይ የምስል መረጃ ጭርምር ደርሶኛል።
   በተመሳሳይ ሁኔታ ከተለያዩ አረብ ሀገራትም በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ምክክር እየተደረገ መሆኑን ያገኘኋቸው ምንጮች ያስረዳሉ  ።
ቸር ያሰማን!!!
Filed in: Amharic