>

ኢትዮጵያ እኮ የቃልኪዳን ምድር የሆነችው በክፉ ቀን የሚደርሱላት ቅን ሰዎችን ስላሉ ነው‼ (ስዩም ተሾመ)

ኢትዮጵያ እኮ የቃልኪዳን ምድር የሆነችው በክፉ ቀን የሚደርሱላት ቅን ሰዎችን ስላሉ ነው‼

ስዩም ተሾመ
የኮሮና ቫይረስ አሜሪካ ውስጥ ምን እያደረሰ እንዳለ ሁላችንም እያየን ነው። ከሁሉም በላይ ደግሞ 50ዎቹ የአሜሪካ ግዛቶች እና የፌደራሉ መንግስት የህክምና መሣሪያዎችን ለመግዛት እርስ በእርስ እየተሻሙ እንደሆነ የኒውዮርኩ አስተዳዳሪ በምሬት ሲገልፅ ይሰማል። አሜሪካ ውስጥ ይህ ሲሆን እዚያም ሆነ በሌላው ሀገር የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን ፈጣሪ የሀገራችሁን ህዝብ እንዲጠብቅ መማፀናችሁ አይቀርም። ምንና እንዴት ማድረግ እንዳለባችሁ ግራ ገብቷችሁ እይጂ በዚህ በጭንቅ ሰዓት የዳር ተመልካች መሆን የሚሻ ሰው የለም። ሲስተር  Shellie Carlson ስሟና ትውልዷ አሜሪካ ይሁን እንጂ ልክ እንደ እኔና እናንተ ልቧ ያለው ኢትዮጵያ ነው። ምክንያቱም ገና የ9ወር ህፃን ሳለች ከእናቷ ከእማማ #Jodie_Collins ወደ ኢትዮጵያ መጥተው መኖር ጀመሩ። እድገቷ ኢትዮጵያ ነው። ከወጣትነት እስከ ጎልማሳነት ትዝታዋ ኢትዮጵያ ነው። እንደ አሁኑ ክፉ ግዜ ሲከሰት ሃሳቧና ጭንቀቷ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ነው። በመሆኑም የአሜሪካ ቱባ ባለስልጣናት ለኮሮና ቫይረስ የሚያገለግሉ የህክምና መሣሪያዎችን ለማግኘት እርስ በእርስ ሲሻሙ እሷ ደግሞ ከአንዱ ሆስፒታል ወደ ሌላው እየዞረች ለኢትዮጵያውያን የህክምና መሣሪያዎች ትለምናለች። በዚህ መልኩ ሦስት ኮንቴይነር ሙሉ የህክምና መሣሪያዎች ሰብስባለች። ቅድም ወዳጄ ገጣሚ Nuredin Issa በውስጥ መስመር መጥቶ እባክህን ተባበረኝ አለኝ። “ሲስተር Shellie ኢትዮጵያን ከኮሮና ቫይረስ ለመታደግ ያሰበሰበችውን የህክምና መሣሪያዎች በመርከብ ለመላክ ብዙ ግዜ ይኸስዳል። የኮሮና ቫይረስ ደግሞ ኢትዮጵያ ገብቷል። ስለዚህ በአውሮፕላን ካርጎ ለመጫን አስበን ገንዘብ አጠረን” አለኝ። ሲስተር Shellieን አናገርኳት… እውነትም ነፍሷ ራሱ ኢትዮጵያዊ ነው። ሲስተር ቅፅል ስም አወጣሁልሽ፤ #ኢትዮጵያዊቷ_ፈረንጅ ብዬሻለሁ አልኳት። ስሜን በደስታ ተቀብያለሁ አለችኝ። ደስ አለኝ ለራሴ “ወዳጄ ልቤ ሆይ…. ኢትዮጵያ እኮ #የቃልኪዳን_ምድር የሆነችው በእንዲህ ያለ ክፉ ግዜ እንደ ሲስተር ያሉ ቅን ሰዎችን ስለሚጥልላት ነው” አልኩኝ። በራሴ የማደርገው ነገር ኖሮኝ አይደለም። እናንተን ተማምኜ ነው። የኮሮና ቫይረስ የጋረጠብንን አደጋ ለመከላከል የበኩላችንን እንድወጣ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮልናል። ይሄን ሊንክ በመጫን የተቻላችሁትን ያህል ድጋፍ አድርጉ። እነዚህ የህክምና መሣሪያዎች ሲመጡ በመጀመሪያ ሐኪሞችና ነርሶችን በኮሮና ቫይረስ እንዳይያዙ ይከላከላል። እነሱ ደግሞ በኮሮና ቫይረስ የተያዙትን ያክሙልናል። ለዚህ ግን የህክምና መሣሪያዎቹ በአስቸኳይ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት አለባቸው። የእናንተ እርዳታና ድጋፍ የሚያስፈልገው እነዚህን የህክምና መሣሪያዎች ለማጓጓዝ ነው። ለሚያደርጉት ድጋፍ ከወዲሁ እጅግ በጣም እናመሰግናለን። ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ሲስተር Shellie Carlson ለኢትዮጵያውያን ያቀረበችውን ልብ የሚነካ ተማፅኖ መመልከት ይቻላል።
Filed in: Amharic