>

ስድስት ተጨማሪ ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል! በድምሩ 35 ደርሷል!!! (ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር)

ስድስት ተጨማሪ ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል! በድምሩ 35 ደርሷል!!!

ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር
ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 74 ሰዎች ውስጥ 6 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን  ይህም በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 35 ደርሷል፡፡
በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡት ውስጥ አምስቱ ከአዲስ አበባ ሲሆን አንድ ከድሬዳዋ ነው።
የመጀመሪያው የ35 ዓመት ወንድ በአዲስ አበባ ከተያዙት ውስጥ ሁለቱ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆን መጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከዱባይ የመጣ ነው፡፡
ሁለተኛው የ30 ዓመት ወንድ በተመሳሳይ ከዱባይ መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ.ም የመጣ መሆኑ ታውቋል።
ሁለቱም አስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት የገቡ ናቸው።
ሶስተኛው የ28 ዓመት ወንድ ከዚህ በፊት በኮሮና ቫይረስ መያዙ ከተገለጸው ሰው ጋር ግንኙነት የነበረው፤
አራተኛውም የ56 ዓመት ወንድ፣የጉዞ ታሪክ የሌለው
 አምስተኛው የ30 ዓመት ወንድ የጉዞ ታሪክ የሌለው ናቸው።
ሌሎች ከእነዚህ ሰዎች ጋር ያላቸው ግንኙነት እየተጣራ ይገኛል፡፡
ስድስተኛዋ ሰው የ33 ዓመት ሴት ስትሆን በድሬዳዋ ከዚህ በፊት በኮሮናቫይረስ መያዙ ከተገለጸው ሰው ጋር ግንኙነት የነበራት መሆኑ ታውቋል።
Filed in: Amharic