>

በህዝባችን ስም የነገዳችሁበት ኣይበቃችሁምን? የዘረፋችሁንስ መቼ ነው የምትመልሱለት???  (ኣስገደ ገብረስላሴ ) 

በህዝባችን ስም የነገዳችሁበት ኣይበቃችሁምን? የዘረፋችሁንስ መቼ ነው የምትመልሱለት???

 

 ኣስገደ ገብረስላሴ 
 * ላለፉት ሰሳልሳና አርባ አመታት  በኣሻጥር ያባከናችሁትና  የዘረፋችሁት የህዝብ ገንዘብ   ዛሬ  ለሂወቱ መዳኛ ይሆነዋልና መልሱለት!  ትናንት ዛሬ   ኣይደለም!!! 
  —
 የተከበራችሁ የህዋሓት ማ/ ኮሚቴ  የነበራችሁና አሁንም ያላችሁ ፣እንዲሁም ለትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች በሙሉ በየኣላችሁበት፤ በኣሁኑ ወቅት በኣለማችን በተለይ ደግሞ በሁሉም መስፈርት የበለጸጉ  አገሮች ሰው ጨራሽ ኮሮና ቫይረስ የሚባል ለካፊና ገዳይ በሽታ  ተሰራጭቶ በአስር ሽ የሚቆጠሩ ዜጎቻቸው ተበልተው ፣ በሞቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻቸው በአረመኔ በሽታ ተለክፈው በሞት አፍ ተራቸው ይዘው ተሰልፈዋል።ወይ ሊዱኑም ይችላሉ።መሪዎቻቸውም  ቫይረሱ የበላቸው ኣሉ (በቫይረሱ ተለክፈው ) እንደ ህዝባቸው  ሊሞቱ ወይ ሊድኑ ተራ ይዘው ይገኛሉ  ።
እነዚህ አገሮች ግን በሽታው ምንም እንኳን ድንገት የወረራቸው ቢሆንም ያላቸው የተማረ የሰው   ግዙፉ እና ቡቁ አቅምም ፣ያላቸው  ግዙፉ የኢኮኖሚ መንጭ በመቀናጀት ለተለከፉ  በሽተኞች ለማዳን በሽታው ተስፍፍቶ ህዝባቸው እንዳይጨርሰው ህዝቡ በመሉ ስራው አቁሞ በቤቱ ተዘግቶ የወረርሽኑ  ወቅት እንዲያሳልፍ ያላቸውን ገንዘብ ፣ሙያ ፣ቁሳቁስ ፣ ሟጥጠው በማውጣት እንደየ አቅማቸው በቢሌን ፣በትርሌን  የሚቆጠር ዶላር ፣ይሮ እያወጡ  ለህዝብ በመከፋፈል እንዲሁም ሌላ ቁሳቁስ ምግብ በቤቱ በማቅረብ የህዝብ እንቅስቃሴ ገድበው ሂወቱ ለማዳን ሌት ተቀን ሲጥሩ እናያለን ።ገና ከወዲሁም እንኳ እንደ ቻይና ፣ ሲንጋፖር ፣ሶቤት ህብረት ገዳይ ወረርሽኑን የመቆጣጠር ምልክት እንመለከታለን ፣እንሰማለን ።
የተከበራችሁ የህዋሓት መሪዎች በእኔ እምነት በሶወስተኛው ኣለም   ልክ እንደ በለጸጉ አገሮች ቡቁ የሰው ሀይልና ገንዘብ ለማቅረብ አቅምም ችሎታም ኣይኖሮንም ።ግን ደግሞ የዚህ ጽሁፍ ሀሳብ ማኸሉ ለህዋሓት መሪዎች ስለሚያደርግ   እኔ እምጠይቃችሁ  መልስም እምፈልግበት ፣እማነሳው ያለሁ ጥያቄም የእኔ ብቻ ሳይሆን የመላው የትግራይ ህዝቦች ጥያቄም  ስለሆነ ፣ ከኮሮና ወረርሽን ቫይረስ  መከላከል በሚመለከት  ኣያይዛችሁ  ጥያቂያችንን ትመሉሱልኝ ዘንድ በትህትና እጠይቃችሁ አለሁ ።
እንደእምንመለከተው  ግማሽ የሚሆን ህዝባችን ከድህነት ወለል  ባለበት በለበት ፣ብቁ ማህበራዊ አገልግሎት ፣ፍትህና መልካም ኣስተዳደር  ተጠቃሚ ባልሆነበት ፣ሌላ ቀርቶ ለተራ በሽታ ማከምያም እንኳ መድሀኒት ፣ንጽህናው የሚጠብቅበት የሚጠጣ ፣የሚታጠበው ውሀ ፣የሚበላ ምግብ በሌለበት፤ ኣሁን ገዳዩ ወረርሽን እንዳይገድልህ  ለሳምንታት፤ወይ ሊቀጥልም ይችላል ቤት ተዘጋ ብላችሁ ያለመቋረጥ ሌት ተቀን ስታውጁ ንሰማለን  ።ይህ  ቤትህ ዝጋ እየተባለ ያለ ህዝብም በከተማም ይሁን በገጠር ስራ የለለው ሳንቲም ትሁን ገቢ የሌለው  የሚታረስ መሬት የሌለው እናንተም በምታምኑበት ከጠቅላላ የትግራይ ህዝበ ብዛት  የተማረም ፣ያልተማረም ከ65 %እስከ 70% የሚሆን እድሜው ከ14 እስከ 46 አመት የሆነ ወጣት ሆኖ የሚበላ የሚላስ ፣የሚሰራው  የሌለው ተዘግቶ የሚበላ የሚጠጣ ካጣ  መሪዎቹ ሊበላ የሚችል ወጣት ነው  ።  ይሽግር በምን መንገድ ነው ልትፈቱት ( ልትመልሱት) ትችሉኣላችሁ ።ሳይውል ሳያድር መልስ ያሰፈልገዋል ።
እኔ የሚደረግ ያለ አዋጅ ለጥንቃቄ መደረግ የሚገባቸው የሚነገሩ ያሉ ሁሉ  ትክክል ነው ።እንዳው መንግስት ላልቷል ። ያወጀው አዋጅ መተግበር ያቃተው ጥርስ የሌለው ነብር ነው የሚል እምነት ያለኝ ።  ግን ኣሁንም እምጠይቀው  የህዝብ ጥያቄ ቢመጣበት በምን መንገድ ሊፈታው ይፈልጋል ?
ወደ ዋናው ኣጀንዳ የዚህ ጽሁፍ  ልመለስ እና ኣርእስቱ የህዝበ ሀፍት በዚሁ ክፉ ዘመን መልሱለት በ1977 ዓ ም በህዝብ ስም የነገዳችሁበት እንዳይደግም  ነው እምለው ያለሁ ።በኣሁኑ ጊዜ በህዝብ ስም መነገድ አይቻልም ።
በኣሁኑ ጊዜ ቫይረሱ ለመከላከል ገንዘብ ቁሳቁስ ፣ያስፈልጋል ጥያቄው የት ይገኝ ነው ?  በእኔ እምነት የትግራይ ህዝብ በትግሉ ያፈራው  በቡዙ ቢሊዮን የሚገመት ገንዘብ ስለነበው   ፤የህዋሓት መሪዎች ደግሞ  ይህ ገንዘብ በህዝብ ስም የልማት ተቋማት መስርተን በዘለቄታ ለህዝብ ጥቅም እናውላቸው ኣለን በማለት ቃለ መሀላ በመግባት ምንም እንኳ ህዝብ የማያውቀው ሳይኖር  የህዋሓት መሪዎች ግን  ቡዙ የንግድ፣የእንድስትሪ ተቋቁመው አትራፊ ሆነው ለ28 አመታት  ገቢያቸው ፣ወጭያቸው የሚይታወቅ በህዋሓት ማ / ኮሚቴ ባለቤትነት እጅ  ሆነው ኖሮዋል ። መጀመሪያ የህዝብ ሀፍት ነው እያሉ የነዚህ ንግድ እና እንድስትሪ ድርጅቶች በየግዜው ለሚቀርቡሏቸው  ጥያቄዎች መልስ   ሲሰጡት የነበሩ ህዝብ ምንም እጁ የለለበት በባለቤትነትም ፍጹም  ባልነበረበት የትግራይ ህዝብ ሀፍት  ናቸው እያላችሁ እየነገዳችሁባቸው ኖሯችኃል። ኣሁን ግን እንደዛ ጊዜ ማጭበርበር ኣይቻልም ?
ከ28 አመት በኃላ ባለፈው አመት የአንድ አመት ትርፍ 22 ቢሌን አለን ብላችኃል ከዛ በፊት ግን  የ27 አመት ትርፍ  ማንም የማያውቀው  እዳ ሊኖራቹሁ ነው።  ኣሁንም  የያዝነው አመትም  በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ኣለ ። ሌላ የትግራይ እርዳታማህበር፣ የደደቢት እና ቁጠባ ባንክ አለ  ።ህዋሓት በባለቤትነት የያዛቸው (ከፍተኛ አክስዮን ) ያለበት ባንክ ፣እንሽራንስ  ገንዘብ  አለ ። ይህ ገንዘብ ሲሰበሰብ ፣ወይ ሲሰላ  እጅግ ቡዙ ገንዘብ ስለሆነ የጠፋ ገንዘብ ጠፍትዋል ኣሁን በእጃቹሁ ያለ ገንዘብ ግን በአሸኳይ  ወደ ህዝብ ሂወት ማዳን  መልሱት ። በተጨማሪም የሚበላ  እህል ፣ማከምያ መድሀኒት ተገዝቶ   ህዝብ ቤቱ  ሆኖ  እየተመገበ  ህመሙ እየተከላከለ እች ክፉ ዘመን እስከ እምታልፍ ቀለብ ይሰጠው ።  ሌላም በትግራይ ክልል ለመጠባበቅያ ምግብ ዋስትና ተብሎ በመካዝኑ ያለ ፣በእርዳታ ድርጅቶች ያለ እህል ፣ቁሳቁስ ለዚሁ አደጋ ለመከላከል ካዋላችሁት በ1977  ዓ ም ዘበነ ድርቅ የፈጸማችሁት ገመና በህዝብ የነበረ ቂም  ( ሊካካስ ) ይችላል ። ካለበለዚያ በዝህች ክፉ ዘመን ግልጽነት ባለበት መንገድ ህዝብችን ገንዘቡ ካልተጠቀመበት ግን ከ 28 አመት በፊት የጠፋ ገንዘቡ ጨምሮ  ከጠየቀ መልሱ አትችሉትም ።በመሆኑ ህዝብ ገንዘቡ መልሱለት። ሂወቱ ይዳንለ ት ።
Filed in: Amharic