>

በኦነጋዊያን በግፍ የታገቱ  እህት ወንድሞቻችን ዛሬ 120 ቀናት (4 ወራት) ሞላቸው!!! (ኤልያስ የኔሁን ገዳሙ)

በኦነጋዊያን በግፍ የታገቱ  እህት ወንድሞቻችን ዛሬ 120 ቀናት (4 ወራት) ሞላቸው!!!

ኤልያስ የኔሁን ገዳሙ
ሸገር ኤፍኤም ራዲዮ ላይ    <<  መናፍስቶች የሚያናግሩት ሸማቂ!  >>   በሚል ርዕስ የተሰራው ፕሮግራም ትልቅ ጥያቄን ፈጥሯል። ይሄውም እውነት ይህ ፕሮግራሙ በሸገሮች በራሳቸው የተሰራ ነው ወይስ መንግስት በሸገር ራዲዮ በኩል ሊያስተላልፈው የፈለገው መልእክት ኖሮ ነው? 
በእነዚህ ታጋች ወገኖቻችን ላይ በአውሬዎቹ  የደረሰውንና ምናልባትም በህይወት ካሉ ወደፊትም ሊያደርስባቸው የሚችለውን የስነልቦና ችግርን ጨምሮ ዘርፈ የህይወት ፈተናን በቀላሉ መገመት ባያቅትም የፓርላማ አባል ነን እያሉ የሚኮፈሱትንና በተለያዩ የስልጣን እርከኖች ላይ የተሰገሰጉ ሴቶች ጨምሮ መንግስት ነኝ የሚለው አካል መንግስትነቱ ለማን እንደሆነ ግራ እስኪገባን ድረስ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሏል።
በርግጥ ቀድሞውንም እንዲህ አይነቶቹ የከፉ ወንጀሎች ሊከሰቱ የቻሉት እና እየተከሰቱም ያሉት ዛሬም የእኛ እና የእነሱ በሚል መርህ የሚመራው ገዢ ቡድን ከለላ ሰጥቶ በሕዝብ ገንዘብ እያንደላቀቀ በሚያኖራቸው ነብሰ በሎች እና ኢሊቶቻቸው በመሆኑ ጊዜውን ጠብቆ ከተጠያቂነት እንደማያስመልጠው ቢታወቅም እስከዚያው ግን እንደሐገርም እንደ ሕዝብም ትልቅ ዋጋ እያስከፈለን ነው።
አዎ እነዚህ 120 የታጋች ወገኖቻችን (ብዙሃኑ ሴት እህቶቻችን) የሰቆቃ ቀናት ወላጆቻቸውን ጭምር ለከፍተኛ የጤና መታወክ መዳረግ ብቻ ሳይሆን በህይወትም ዋጋ እስከማስከፈል ደርሶ የታጋች እናት አእሞሯቸውን መሳታቸው ድርብ ሀዘን መሸከም ያቃተው ወንድም እራሱን በመስቀል ህይወቱን አጥፍቷል።
መንግስት ግን አሁንም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ዝም ብሏል፤ ስለታጋች ሴት ተማሪዎች የት ሄዱ እያለ የሚጠይቀውን ሕዝብም ለማዘናጋት የተለያዩ አዠንዳዎችን ይፈጥራል።
—> በዚህ መሃል ግን ከሁለት ሳምንታት በፊት ሸገር ኤፍኤም ራዲዮ (Sheger FM Radio) ላይ    <<  መናፍስቶች የሚያናግሩት ሸማቂ    >>   በሚል ርዕስ የተሰራው አንድ ፕሮግራም ትልቅ ጥያቄን ፈጥሯል። ይሄውም እውነት ይህ ፕሮግራሙ በሸገሮች በራሳቸው የተሰራ ነው ወይስ መንግስት በሸገር ራዲዮ በኩል ሊያስተላልፈው የፈለገው መልእክት ኖሮ ነው? ለማንኛውም ፕሮግራሙን እንካችሁ። በተለይ ሴት መሆን እዳ ነውና ሁላችንም ልንጮህላቸው ይገባል። (ከኢትዮ ፈርስት)
 <•>
Filed in: Amharic