>

በኮረና ምክንያት የተዳቀቀው ኢኮኖሚ ያስጨነቃቸው  የጀርመን ባለስልጣን ራሳቸውን አጠፉ !! (ቅዱስ ማህሉ)

በኮረና ምክንያት የተዳቀቀው ኢኮኖሚ ያስጨነቃቸው  የጀርመን ባለስልጣን ራሳቸውን አጠፉ !!

ቅዱስ ማህሉ
 
ኮሮና ቫይረስ ያስጨነቃቸው የጀርመኗ ሄስ ግዛት ፋይናንስ ሚንስትር ራሳቸውን አጥፍተው ባቡር ውስጥ ወድቀው ተገኝተዋል። ሚንስትሩ ቶማስ ሻፈር በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ለገባው ህዝብ የሚጠብቀውን ያህል የገንዝብ ድጋፍ ማድረግ ይቻል ይሆን ወይ የሚለው ጥያቄ እንቅልፍ ሲነሳቸው እንደሰነበተ የግዛቱ ፕሪሜር(መሪ) ቮከ ቩፌየ ተናግረዋል። ቮከ በማከልም የፋይናስ ሚንስትሩ “መደንገጥ እና ማዘናቸውን ገልጸዋል። ኮሮና ቫይረስ የአውሮፓን ትልቅ ኢኮኖሚ እና ከዚያም ደግሞ ትልቋን የፋይናስ መዲና የሆነችውን የፍራንክ ፈርት ፋይናስ በበላይ ሲመራት የቆየውን ሰው እንዲህ ካስጨነቀ እና ለሞት ከዳረገው የአፍሪካን ኢኮኖሚ ምን ያህል ሊያመሳቅለው እንደሚችል መገመት አያዳግትም።
የአፍሪካ መሪዎች አለማሰባቸው ጠቀማቸው እንጅ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የህዝቡ ፈተና እና እጣ ፈንታ፣ ምን ይበላ ይሆን፣ ምን ዓይነት ማህበራዊ ምስቅልቅ ይገጥመው ይሆን፣ እንዴትስ ያልፈው ይሆን የሚለውን ወዘተ ማሰብ ቢጀምሩ ከየትኛውም ዓለም በፊት መጀመሪያ በጭንቀት የሚያልቁት የአፍሪካ መሪዎች ነበሩ። ለማንኛውም ከልክ ያለፈ ጭንቀት ለሞት አሳልፎ ይሰጣልና ኮሮናንም ቢሆን በተቻለ መጠን ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን እና ቤተሰባችንን ከመጠበቅ ባለፈ አላስፈላጊ ፍርሃት እና ሽብር ውስጥ መግባት የለብንም።
ሙሉ ዜናው https://bit.ly/2JBft77
Filed in: Amharic