>
5:13 pm - Monday April 18, 7205

"ብዙ ሀገሮችም ልዩ ነን ብለው ተዘናግተው ነበር እኛን ጨምሮ!!!"   [ዶ/ር ኪሩቤል ተስፋዬ ከስፔን ማድሪድ]

“ብዙ ሀገሮችም ልዩ ነን ብለው ተዘናግተው ነበር እኛን ጨምሮ!!!”

 ዶ/ር ኪሩቤል ተስፋዬ ከስፔን ማድሪድ
       የኢትዮጵያንም የስፔንንም የጤና ጥበቃ አቅም በቅርበት እንደሚያዉቅ ባለሙያ ሰሞኑን የታዘብኩትን ላጋራቹ። የዛሬ ሳምንት ድረስ ምንም እንኳ መንግስት ነዋሪዉ እንዲጠነቀቅ ቢናገርም የሚሰማ ሰው አልነበረም ፤ የ ኳስ ጨዋታዎች በየከተማው ነበሩ ፤ ስብሰባዎች ነበሩ፤ዮኒቨርሲቲዎች ክፍት ነበሩ፤ የሚሰማ ሰው አልነበረም ።
.
ህዝቡ ከቻይና አልተማረም ፤ ጎረቤት ካለችው ጣልያንም አልተማረም። የሚይዘው አልመሰለውም ፣እራሱን ልዮ አድርጎ የሚያድነው የመሰለውን ምክንያት ደረደረ።
.
አሁን ሀገሪቷ ከተዘጋጋች ቀናቶች ተቆጠሩ መውጣት የሚቻለው ምግብ ወይ መዳኒት ለመግዛት ነው፤ የ አንቡላንስ ድምፅ በየቦታው ነው፤ ሰው በየቦታው እየሞተ ነው። ፈርተናል ፣ ፈርቻለው ፤ ያስፈራል።
.
ሀገሬም ተመሳሳይ መንገድ መከተሏ ያስጨንቃል፤ ኢትዮጵያውም እስካሁን ምክንያት መደርደራችንን ቀጥለናል። መጀመሪያ ቻይና ሀይማኖት ስለሌላት ተቀጣች አልን ፤ ከዛ ጣልያንን፣ ኢራንን ግብጽን  ሲያስጨንቅ “ኢትዮጵያን የነካ…. ምናምን” እያልን ተመጻደቅን።
“ባክህ ተወው እኛ ሀገር ሙቀት ስለሆነ አይገባም” ማለት ጀመርን ፣ ብራዚል እና አውስትራሊያ ገብቶ አየን ከዛም አልቀረም  ሀገራችን ገብቶ አየን።
” አሁንም ከተያዙት ብዙሀኑ ነጮች ናቸው ኢትዮጵያውያንን አይዝም” የሚል ከንቱ ወሬ ሰማን። ከ 4 ቀን በፊት ሁለት ኢትዮጵያውያን ጣልያን ውስጥ ሞቱ። አሁንም “እዛ ስለኖሩ ነው የሞቱት” የሚል ስለማይጠፉ ከሟቾች አንደኛዋ ከቀናት በፊት ከኢትዮጵያ የሄዱ ነበሩ።
.
እስከመቼ ልዩ እንደሆንን እንዲሰማን ምክንያት እንደረድራለን? ፈጣሪ ልዮ አድርጎ የመጠንቀቂያ ጊዜ ሰቶናል እንጠንቀቅ።
Filed in: Amharic