>

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የዑለማ ም/ቤት የኮሮና ቫይረስ በሽታን አስመልክቶ የተሰጠ ፈትዋ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የዑለማ ም/ቤት የኮሮና ቫይረስ በሽታን አስመልክቶ የተሰጠ ፈትዋ።

1.  በኮሮና ቫይረስ በሽታ የተያዘ ወይም የተጠረጠረ ማንኛውም ሰው ለጁምዓም ሆነ ለጀመዓ ሰላት፣ ለሐይማኖታዊ ት/ት ወደ መስጂድም ሆነ ሕዝብ ወደተሰበሰበበት ቦታ መምጣት የተከለከለ ነው።
2. ማንኛውም ሙስሊም በሽታው አስጊ በሆነበት ሁኔታ ከጁምዓ እና ከጅምዓ መቅረት በሽርዓ የተፈቀደ ሲሆን በየቤቱ መስገድ ይችላል።
3. የጤና ጥበቃ ተቋማት እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የሚሰጡትን ምክር፣ መመሪያ፣ መቀበል እና ስራ ላይ ማዋል ሐይማኖታዊ ግዴታ ነው።
4. የመጅሊስ ኢማሞች፣ ዑለሞችና ዳዒዎች ሙስሊሙን ህዝብ ወደ አላህ እንዲመለስ እና ምህረት እንዲለምን፣ ሰደቃ እና ዱዓ እንዲያደርግ እንዲመክሩ እንጠይቃለን።
አላህ ሰ.ወ. ይህንን በሽታ እንዲያነሳልን፣ ሀገራችንና ህዝባችንን ይጠብቅልን ዘንድ እንለምናለን።
Filed in: Amharic