>

"ባለማስነጠሴ ነፍሴን አተረፍኳት!!!" (ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ)

“ባለማስነጠሴ ነፍሴን አተረፍኳት!!!”

ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ
ዳዊት ተካ
“…….ከዓመታት በፊት “New York” ከተማ ውስጥ ነበርኩ። ትዝ ይለኛል ጭጋጋማ የሆነ ቅዳሜ ነበር። አንዲት ጥቁር ሴት አጠገቤ መጣች። የማስታውሰው “ማርቲን ሉተር ኪንግ አንተ ነህ?” ብላ የጠየቀችኝን ጥያቄ ብቻ ነው! “አዎ ነኝ!” ብዬ መለስኩላት! ከዛ በኃላ የሚታወሰኝ ደረቴ ላይ የሆነ ነገር ሲሰነቀርብኝ ብቻ ነው። ያቺ ጥቁር ሴት ጩቤ ሰክታብኝ ሮጠች!
ወደ ሆስፒታል ወሰዱኝ።
 የ “X ray” ምስሉ የሚያሳየው ደረቴ ላይ የተሰካብኝ ጩቤ ልቤ ላይ ሊደርስ ትንሽ እንደቀረው ነው! ትንሽ
ቢጠጋ ኖሮ በራሴ ደም ተጥለቅልቄ እስትንፋሴ ትቋረጥ ነበር!
አለቀ! አበቃ!”
“….በንጋታው “New York Times” ጋዜጣ በፊት ገፁ ይዞት የወጣው ዘገባ ላይ “ማርቲን ሉተር ኪንግ በዛች ቅፅፈት አስነጥሶ ቢሆን ኖር ይሞት ነበር! ጩቤው ልቡን ለማግኘት ያቺን ታክል ነበር የቀረው!” የሚል ነበር።
“…ቀዶ ጥገና ተደርጎልኝ ጩቤው ከደረቴ ከወጣ በኃላ ከተለያዩ ዓለማት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የማፅናኛ እና የእንኳን አተረፈህ ደብዳቤዎች ተላኩልኝ! ከነዛ ሁሉ ደብዳቤዎች ግን የማረሳው
አንዱን ብቻ ነው!
– ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ደብዳቤ ተልኮልናል! ነገር ግን እረስቼዋለሁ!
–  ከምክትል ፕሬዝዳንቱም እንደዛው ግን
ደብዳቤው ምን እንደሚል አላስታውስም!
–  ከ “New York” ከተማ ገዢም ደብዳቤ ተልኮልኝ ነበር! በአካልም መጥቶ ሆስፒታል ድረስ
ጠይቆኛል! ግን አላስታውስም!
* የማልረሳው ደብዳቤ ግን ይህንን ይላል!…”
“…ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ! እኔ ገና የ 9 አመት ልጅ ነኝ! የቆዳ ቀለሜ ደግሞ ነጭ ነው! አንድ ነገር ልልህ እፈልጋለሁ! ስላላስነጠስክ ደስ ብሎኛል!…” የሚል ነበር!
“…እኔም የምላችሁ ይሄንን ነው! ባለማስነጠሴ ደስተኛ ነኝ! ምክንያቱም ባስነጥስ ኖሮ በ 1960 ጥቁሮች በተከለከሉባቸው ሬስቶራንቶች ገብተን ቡና በማዘዝ እኩል ከነጮች መስተናገድ እንድንችል ዘመቻ አናደርግም ነበር!
በ 1961 “Freedom Riders” የተሰኘውን ቡድን አቋቁመን ነጮች እና ጥቁሮችን የሚለየውን አግላይ የትራንስፖርት መዋቅር ለመቃወም የተከለከልንባቸው ባሶች ውስጥ በመግባት አግላይነትን አንፋለምም ነበር!
እውነትም ባስነጥስ ኖሮ ይህንን ማየት አልችልም ነበር!
አስነጥሼ ቢሆን ኖሮ በ 1963 “ህልም አለኝ” የሚለውን ታሪካዊ ንግግር ማድረግ ባልቻልኩ ነበር! እውነትም ያን ቀን አስነጥሼ ቢሆን ኖሮ እነዛን ለጥቁሮች ነፃነት የታገልናቸውና ፍሬ ያፈሩ መራራ ትግሎችን ማየት አልችልም ነበር!
ስላላስነጠስኩኝ እውነትም ደስ ይለኛል!…. እንደሁላችሁም እኔም መኖር ወይም በህይወት መቆየትን እፈልጋለሁ! ነገር ግን ከዚህ በኃላ ስለዛ ማሰብ አልፈልግም! ከዚህ በኃላም አንዳች ነገር
የምፈራው የለም! ስለምንም ነገር አልጨነቅም! የምፈልገው የፈጣሪን ፍላጎት እና ጥሪ አሳክቶ ማለፍ ነው!….”
እ.ኤ.አ “ሚያዝያ 3 ቀን 1968” Martin Luther King Jr. “I have been to a mountaintop” ከተሰኘው ንግግሩ ላይ
የተወሰደ!
Guess what? ይህንን ታሪካዊ ንግግር ባደረገ በንጋታው ተገደለ!
Filed in: Amharic