>

ልብ ሰባሪ ዜና ከወደ ጣሊያን !!! (ከፍሬ ሰው ደምስ)

ልብ ሰባሪ ዜና ከወደ ጣሊያን !!!

 

ከፍሬ ሰው ደምስ
አንዲት ኢትዮጵያዊት እኔና በአለቤቴ ታመን ሆስፒታል ገብተን ነበር ትላለች።ባለቤቴ አርፏል።ወደ ሆስፒታል ከገባን አልተገናኘንም።እኔን ሲሻለኝ የእሱን መሞት ነግረውኛል።ሁለት ልጆቼ ቤት ናቸው ።እነሱም አሁን በስልክ ሰምተዋል።
ባለቤቴ መቼ እንደሚቀበር አላወኩም የሚሞተው ብዙ ስለሆነ ወረፋው አልደረሰውም።
ምን አልባት ሲቀበር እገኝ ይሆናል።ያው በበሽታው ምክንያት ሦስትና አራት እየተሆነ ነው የምንቀበረው።
አይኽ? ወዳጄ ሙቶ መቀበር ውድ ሲሆን ፣!!!!
አልቅሶ መቅበር ቅንጦት ሲመስል፣ ችግሩ ይህን ያህል ገዝፏል።
የልቅሶ ባህላችን እንኳን እንዲህ ቀረ። ሰላምታችንን አቁመናል። ገበያ መሄድ ትተናል። አቢያተ ክርስቲያናት ተዘግተዋል።
ትምህርት ቤትና የስፖርት ማዘውተሪያዎች የሉም። ቡና ቤቶችና ሱቆች ዝግ ሁነዋል። ዓለም በታሪኳ ያላየቺውን እያስተናገደች ነው ።
ለበሽታው ብቸኛው መድኃኒት እራስን ከሰዎች ማራቅ ብቻ ነው። ፍቅር ውድ ሁኖ ፣ማስመሰልና ጥላቻም ገዝፎ ነበር። አሁን ብቸኝነት መድሓኔት ሁኗል።
የተባልከው ማድረግ ሲያቅትህ በልክህ የሚሆን ችግር ይመጣልሃል። ፍቅርን አሾፍክበት ሰላምታንም አስመሰልክበት እነሱ ዛሬ ውድ ሁነዋል።
ወዳጄ እባክህ ከልብህ ጸልይ !!!
ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ነው።ወሩን ወርኀ መጋቢት ነው። መጪው ሳምንትም ደብረ ዘይት ነው። የማይሆን የሚመስለው ሁሉ ድንገት ይሆናል። ሳትዘናጋ ጸልይ።  በችግር ጊዜ ማንም ለማንም መርዳት አይችልምና። እግዚአብሔር ይርዳህ።
Filed in: Amharic