>

ሁለቱን  ጥፋቶች ሳናቀላቅል እናውግዝ ! (አባይነህ ካሴ)

ሁለቱን  ጥፋቶች ሳናቀላቅል እናውግዝ !

አባይነህ ካሴ
* •~ «የሕክምና ቡድኑ በከተማዋ ነጻ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት የመጣው ባለፈው ቅዳሜ እለት ነው።»
*  ለህክምና የመጣ ቡድን ህክምናውን ብቻ አድርጎ መሄድ አለበት። ነገር ግን ህዝብን ድህነትና የህክምና እጦትን እንደካማ ጎን ተጠቅሞ እምነቱን ድሆች ላይ ለመጫን መሞከር ፍፁም ነውር የሆነ provocative ድርጊት ነው። ለሀይማኖት በንፅፅር የተሻለ ነፃነት አለ። ቦታም መንግስት ፈቅዷል። ሀይማኖታዊ ሰበካዎችን በሀይማኖት ቦታ መወሰን ይገባል።
በእንዋሪ የፕሮቴስታንቶች መገልገያ መቃጠሉ የሚደገፍ አይደለም እና መወገዝ ይገባዋል። ይህ በአብዛኛው ሰው ተደርጓል፣  እየተደረገም ይገኛል።
ሌላ ግን ሳይወገዝ የቀረ ክፉ ሥራ አለ። እናክምህ ብሎ ሕዝብን በለፈፋ ጠርቶ ሊሰማው በማይወድደው “የጌታን ተቀበል” ጩኸት ማደንቆር።  ያ ሕዝብ የታመመው በሥጋ እንጅ በነፍሱማ የከበረ ነው። ጨው እያላሰ በሬውን ወደ መታረድ እንደሚመራ የሥጋ ደዌህን እንፈውስልህ ብሎ አግባብቶ ወደ ገሀነም ሲገፉት እንዴት ዝም ብለህ እሳት ግባ ይባላል?
እውነተኛ አውጋዥ ካለ የመጀመሪያውን ብቻ ሳይኾን ኹለተኛውንም ያውግዝ። እየነጠሉ ይህን ኦርቶዶክሳዊ እየተነኮሱ ከሞጣ እስከ እንዋሪ ማብጠልጠል ፍትሐዊነት አይደለም።
ከውጭ ሀገር የመጣው የሕክምና ቡድን ከእሑድ ጀምሮ በእንዋሪ ጤና ጣቢያ በመገኘት ነፃ የሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ የተለፈፈው ዐዋጅ ያስረዳል። በዚህ መሠረት እውነት ብሎ ከያለበት ሕዝቡ ለሕክምና ቢመጣም በቅድሚያ “ጌታን ተቀበል” የሚል ገጠመው።
ይህን ሕዝብ አትቆጣ ብሎ ውርጅብኝ ልክ ያልኾነውን ያኽል ቃጠሎውም ልክ አይደለም ቢሉ የተመቸ። የሕዝቡ ጥያቄ ችላ ተብሎ ከቀጠለ ግን ችግሩ ወዲህ እንጅ እዚያ አይደለም ወዳጄ።
ሳይሠለጥኑ ሥልጡኑን ሕዝብ እናሠልጥን ማለት ድፍረት ነው። ደጋግሞ እንዳሳየው መደፈርን ደግሞ እሺ በጀ አይልም። ከፈለጉ ስብከታቸውን ለእኔ ቅሰጣ ነው በአዳራሻቸው ማድረግ ይችላሉ ነው ሕዝቡ ያለው። እንዴት በመንግሥት ተቋም ተጠርተን ማተብ በጥሱ እንባላለን ነው ጥያቄው? እንግዲያው አስቀድመን መነሻውን እናውግዝ።
ሰሚ ካለ ሕዝቡ እንዲህ ነው ያለው ፡ – “የሃይማኖት ስብከቱ በከተማዋ በሚገኘው የፕሮቴስታንት የእምነት ተቋም ቅጽር ግቢ ውስጥ ቢሰጥ ችግር የለብንም፤ ከጤና ጣቢያው ጎን ድንኳን ጥለው ስብከት ማካሔዳቸውና የሃይማኖት መጻሕፍት ማደላቸው ግን ቁጣችንን ቀስቅሷል።”
የእነ ወርልድ ቪዥን እራፊ ውሰዱ ብሎ መቀሰጥ፣ ስንዴ እንካችሁ እያሉ መቀሰጥ፣ የጉድጓድ ውኃ ላውጣ ብሎ መቀሰጥ፣ የመስኖ ልማት ብሎ መቀሰጥ፣ የእርከን ሥራ ብሎ መቀሰጥ፣  የሥነ ተዋልዶ ሥልጠና እያሉ መቀሰጥ የመረረው ሕዝብ አሁን ደግሞ እንደዚህ ያለ ድፍረት እንዲያስተናግድ ማን ነው የፈረደበት?
በሕዝባችን ዘንድ በሃይማኖት ቀልድ የለም። በነፍስ ሞትን እንጅ በሥጋ ሞትን አይፈራም። ማኅተቡን ከሚበጥስ አንገቱ ቢቀነጠስ ይቀልለዋል። ችሏችሁ ታግሷችሁ ኖረ አሁን በቃኝ አለ። ሥራ እያስፈታችሁ ቀጠሮ እያስታጎላችሁ ከገጠር እስከ ከተማ አንከራትታችሁ ደግሞ ነፍስህን ጨምርልን የምትሉ አድቡ። ይህንን ሮጣችሁ ለእነ opendoors እያስመዘገባችሁ ችርቻሯችሁን አቁሙ።
Filed in: Amharic