>

ኦሮሞዎች እንዲፈቷቸው ኦፌኮ እየዘመተባቸው ያሉት ሐበሾች እነ ማናቸው?!? (አቻምየለህ ታምሩ)

ኦሮሞዎች እንዲፈቷቸው ኦፌኮ እየዘመተባቸው ያሉት ሐበሾች እነ ማናቸው?!?

 

አቻምየለህ ታምሩ
ራሳቸው ኦሮሞ ሳይሆኑ ሐበሻን ያገባን ኦሮሞ አፋተን ኦሮሞን እንዲያገባ እናደርጋለን የሚሉን የዚህ ዘመን የኦነግ ፕሮግራም አቀንቃኝ ወጣቶች ስለ ሐበሻ የጥላቻ ትምህርት ሲቀስሙ ያደጉ አሳዛኝ ፍጡራን ናቸው። ኦነግ ኦሮሞን ከሌላው በተለይ ከአማራው ለመለየት ሲል ከተጠቀማቸው ትርክቶች አንዱ ኢትዮጵያን ፈረንጆቹ በሚጠሩበት ስያሜ «አቢሲኒያ» እያለ የሚጠራበት ፕሮፓጋንዳው ነው። በቤተ ኦነግ ኦሮሞ ከአማራ መለየት ስላለበት ኦሮሞ አቢሲኒያዊ አይደለም። ኦሮሞ ኦሮሞ እንጂ ሐበሻ አይደለም የሚለው ትርክት የሚወለደው ከዚህ ነው። ኦነጋውያን ራሱን አቢሲኒያዊ ብሎ የሚጠራ አማራም ሆነ ሌላ ኢትዮጵያዊ እንደሌላ ያውቃሉ። ሆኖም ግን ፈረንጆቹ ለመለያየት እንደሚጠቅም ስላስተማሯቸው አማራንና በተለይም የሰሜኑን የኢትዮጵያ ክፍል ሕዝብ ራሱን በማይጠራበት ስያሜ አቢሲኒያውያን እያሉ ይጠሩታል። ይህን ተከትሎም በተለይ ባለፉት 27 ዓመታት ውስጥ «ኦሮሞ ነኝ፤ ሐበሻ አይደለሁም» የሚል ሐሳብ  የኦሮሞ ወጣት ተፈጥሯል።
ለመሆኑ ኦነጋውያን ፈረንጆች ኦሮሞን በተለይም ከአማራው ለመለየት ሲሉ ያስተማሯቸውን «አቢሲኒያዊ አይደላችሁም» በሚለውን ሴራ ውስጥ ያለውን «አቢሲኒያ» የሚለውን የፈረንጆቹ ስያሜ ትርጉምና ታሪክ ያውቁታል? ራሷ ኦሮሞ ሳትሆን  ሐበሻን ያገባን  ኦሮሞ አፋተን ኦሮሞን እንዲያገባ እናደርጋለን ያለችዋ የኦፌኮ የትዳር ክፍል ኃላፊ  ሐበሻ የሚለውን ቃል ትርጉም ብታውቀው ትወደው ነበር፤ ግን የኦነግ ተማሪ ስለሆነችና እንድትደግም እንጂ እንድትመረምር ስላልተማረች ቃሉንና በቃሉ የጠራቻቸቸውን በደፈናው መጥላትን መርጣለች።
አቢሲኒያ የሚለውን ቃል ለፈረንጆቹ ያስተማረው Friar Luis de Urreta የሚባል የዶምኒክ ቄስ ነው። Friar Luis de Urreta በአስራ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጽሐፈ ሔኖክ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገኝ በላቲን ቋንቋ «Historia eclesiastica, politica, natvral, y moral, de los grandes y remotos reynos de la Etiopia, monarchia del emperador, llamado Preste Iuan de las Indias» ሲል በጻፈው መጽሐፍ ውስጥ ሐበሻ የሚለውን ቃል በደቡብም ሆነ በሰሜን የኢትዮጵያ ምድር የሚኖሩ ነገዶች ሁሉ ራሳቸውን የሚጠሩበት ቃል እንደሆነ ይገልጻል።
በመጽሐፉ ገጽ 4 ላይ ኢትዮጵያውያንን ሐበሻ ከሚለው ቃል ላይ ተነስቶ በላቲን ፊደል corrupt አድርጎ በመጻፍ Abissinois ሲል ይጽፍና ምድሩን ደግሞ Abissia ይለዋል። ይህን Abissia የሚለውን የኢትዮጵያ መልክዓ ምድር ሲተነትን ከምድር ወገብ ሶስት ዲግሪ እስከ አስራ ስምንት ዲግሪ፤ ከግሪንዊች ሜሪዲያን አስራ ሶስት እስከ አርባ ስምንት በመለስ ያለውን መሬት እንደሚያጠቃልል ይጠቅሳል። ይህ የኢትዮጵያ ክፍል ኦሮሞ ኋላ ላይ የወረራቸውን ባሌን፣ ሐረርን፣ ወለጋን፣ ጅማን፣ ኢሉባቦርን፣ ወዘተ ያጠቃልላል። ከዚህ በመነሳት ነው እንግዲህ Friar Luis Urreta በላቲን Abissinois ሲል corrupt አድርጎ የጻፈውን እንግሊዞች ቃሉን anglisized ሲያደርጉ ምድሩን ወደ Abyssinia፤ ሕዝቡን ደግሞ Abyssinians ወደሚል ኢትዮጵያውያን ራሳቸውን በማይገልጹበት ቃል የቀየሩት።
Friar Luis Urreta ሐበ ሻ የሚለውን ቃል corrupt አድርጎ ቢጽፈውና እንግሊዞቹ Abyssinia እና Abyssinians የሚለውን ስያሜ እንዲፈጥሩ ምክንያት ቢሆንም የቃሉን ትርጉም ግን ከውስጥም ከውጭም አገኘሁትን ያለው አስቀምጧል። Friar Luis Urreta እንደነገረን ሐበሻ ወይንም እሱ corrupt አድርጎ የጻፈው Abissinois የሚለውን ቃል ኢትዮጵያውያንም፣ አረቦችም፣ ቱርኮችም ይጠቀሙበት ነበር። ኢትዮጵያውያንንም ሆነ አረቦቹንና ቱርኮችን ጠይቄ አገኘሁት ባለው የቃሉ ፍቺ መሠረት ሐበሻ ወይንም እሱ corrupt አድርጎ የጻፈውን Abissinois የሚለውን ቃል ከግብጽ በታች ያለ አገር መጠሪያ ያደርግና ትርጉሙን ሲገልጽ «It means a free and independent people who have never served a foreign masters or a recognized forign king» ይለዋል። እንግዲህ ሐበሻ የሚለው ቃል ትርጉም «a free and independent people who have never served a foreign masters or a recognized forign king» ከሆነ ኢትዮጵያን በተለይም የሰሜኑን ክፍለ ሕዝብ ፈረንጆች በሚጠሩት ስም «አቢሲኒያ» ብለው ካልጠራን ሞተን እንገኛለን የሚሉንና ይህንንም ካላደረጉ ፖለቲካ የሰሩ የማይመስላቸው ኦነጋውያን «ኦሮሞ ሐበሻ አይደለም!» ሲሉ ኦሮሞ ሳይወረው ሐበሻ በመባል ይታወቅ በነበረውን የኢትዮጵያ መሬት በወረራ የያዘውን ኦሮሞን  በውጭ ኃይል ቅኝ ተገዝቶ ነበር ማለታቸው ይሆን? ነው ወደ ቅኝ ግዛት እንመልሰው እያሉን ይሆን?
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሮች ተደርገው በያ ትውልድ የቀረቡት የፈጠራ ትርክቶች እውቀት ያከሉት በትርክቶቹ ዙሪያ በእንግሊዝኛው አጠራር «WH questions» ከሚባሉት ሰባቱ ጥያቄዎች መካከል ቢያንስ ሶስቱን «WH» ጥያቄዎች ብቻ የሚጠቀው ቀለም ቀመስ ቁጥር እምብዛም በመሆኑ ነው። ወያኔና ኦነግ የዘረጉት  የትምህርት ሥርዓት እያፈራው ያለው ባለ ዲግሪ ምሩቅ የሚመረምር ሳይሆን በየአካባቢው ሲነገር የሰማውን እቶፈንቶ አጠናክሮ የሚወጣና ከጋዜጣ headline በላይ የማያነብ second level illiterate ነው። «ሌሎችን አትስሟቸው» የሚል ድንቁር የእውቀት ጾመኛነት የትምህርት መመሪያ ሆኗል። ይህንን ድንቁርና እያስተማሩ የብሔር፣ ብሔረሰብ ልሂቃን በሙሉ የተማረ እየተባለ ሲባል የሰማውን ሳይመረምር በሚደግም ካድሬ ሆነ!  ራሳቸው ኦሮሞ ሳይሆኑ ሐበሻን ያገባን ኦሮሞ አፋተን ኦሮሞን እንዲያገባ እናደርጋለን ያለችው ኦነግ ያበላሻት ወጣትም በሐበሻ መሬት እየኖረች ሐበሻ  ያገባን ኦሮሞ  ማፋታትን ሥራዋ አድርጋ የያዘችው ኦነጋውያን ልዩ ዘር ለመፍጠር የደረቱትን ድንቁርና እየደገመችና fact matter ስለማያደርጋት እንጂ በማይዋሽበት ዘመን እየኖረ የሐበሻን ምንነት አጣርታ አውቃ አይደለም!
Filed in: Amharic