>

OMN እንደ ሁቱ ቴሌቭዥን ኦፌኮ እንደ Interahamwe!!! (ቴዎድሮስ ጸጋዬ)

OMN እንደ ሁቱ ቴሌቭዥን ኦፌኮ እንደ Interahamwe!!!

 

ቴዎድሮስ ጸጋዬ

* “አትጋቡ” ፣ “አትገበያዩ” የኦፌኮ መሪ የምርጫ መፈክር!!!

 

* “ዘር አጥፉ” ፣ ” ዘር አጽዱ ” የOMN መሪ ቃል!!

የሀገራችንን ፈተና በእጅጉ ከሚያከብዱ እውነታዎች መሃል በዚህ ህገመንግስት ተብዬ ሰነድ አማካይነት በከፋ ሁኔታ በአየሩ ላይ በተረጨው የዘረኝነት መርዝ ላይ፣ እንደጃዋር መሀመድ ያለ ሀላፊነት አልባ ዘረኛ፣ እንደበቀለ ገርባ ያለ ዘር አስጨፍጫፊ እኩይና እንደመረራ ጉዲና ያለ ሳያድግ ያረጀ ፖለቲከኛ በፖለቲካ ሜዳው ላይ ትርጉም ያላቸው ተጫዋቾች የመሆናቸው ነገር ነው፡፡
 እነኚህ በየፊናቸው “ግባችን” ካሉት ለመድረስ ሚሊዮኖችን ከማስጨፍጨፍ ወደኋላ የማይሉና ለዚህም ተግባራዊነት የትርክትና የርዕዮተአለም መደላድል የሰሩ፣ የፖለቲካ ፓርቲ ያደራጁ፣ መገናኛ ብዙሀን ያቋቋሙ፣ የጥላቻ መልእክቶችን አለማቋረጥ የረጩና እልቂት ፈጻሚ መንጋ ያዋቀሩ ናቸው፡፡
እነዚህ በየራሳቸው የአገር መከራ የሆኑ ግለሰቦች ለዝያ አንድ ለሆነ እኩይ አላማቸው ሲቀናጁ ደግሞ የጉዳታቸው መጠን በብዙ እጥፍ ያድጋል፡፡ በሀገራችን በአሁን ወቅት ህግን አለአድልዎ የሚያስፈጽምና ሁናቴዎችን
ከእራሱ የፖለቲካ ትርፍ አንጻር ብቻ የማያሰላ መንግስት ቢኖር ኖሮ እነኚህ ግለሰቦች አሁን ይህንን እንድንጽፍ በተገደድንበት ወንጀላቸው ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም በፈጸሟቸው የህግ ጥሰቶች ፍርድ ሊቀበሉ የሚገባቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ግን በመሰረቱ በአስተሳሰብና ግብ ከእነኚህ ግለሰቦች የማይለይ ፣ በኢትዮጵያ ያለው ህገመንግስትም ሆነ የፖለቲካ ስርአትም መሰል ዘር ማጽዳትንና ማጥፋትን የሚወልድ የጥላቻና የልዩነት ስርአት ነውና ለጊዜውም ቢሆን ፍትህ ሲበየን የመመልከት እድል የለንም፡፡
“አትጋቡ ተፋቱ”
በናዝሬት ከተማ ኦፌኮ ባካሄደው ስብሰባ ላይ ፓርቲው ከተረዳን የከራረምነውን እውነተኛ ቀለሙን ጤናማ አእምሮ ላለው ሁሉ በማያሻማ ሁኔታ አሳይቷል፡፡ የዘውግ ብሄረተኞቹ መገናኛ ብዙሀንና ፓርቲዎች ለአስርት አመታት እንዲመጣ የፈለጉትና የጣሩለት ጨፍጫፊ አተያይ ፍሬ የያዘላቸው ይመስላል፡፡ አደባባይ ላይ ባሎች እንዲኖሯት ያደረገችውን ጥሪ ትተን ፣ ከ “ሀበሾችና ነፍጠኞች አትጋቡ፣ የተጋባችሁም ተፋቱ” ያለችው መጨረሻው በማይታወቅ የድንቁርና እንጦሮጦስ ውስጥ የወደቀችው ሴት የእነኚህ ሰዎች
የእጅ ስራ ናት፡፡ የዚህች ሴት አስተሳሰብ የጃዋር መሀመድ ፣ የበቀለ ገርባ ፣ የመረራ ጉዲናና የመሰሎቻቸው በስልጣን ላይ የነበሩ ፣ ያሉና የሌሉ ዘውጌዎች ጨለማ አእምሮ ተጨባጭ ክሳቴ ናት፡፡ ለዚህም ሌላ እማኝ አንጠራም፡፡ ይህ ንግግር በሚነገርበት ወቅት በቀለ ገርባና መረራ ጉዲና አጨብጭበዋል፣ ተፍነክንከዋልና፡፡
  ኦፌኮ በኦርቶዶክሳውያን ላይ በይፋ ባወጀው ጦርነት፣ በመሪው በቀለ ገርባ ያልታረመ አንደበት በኩል የብሄሮች መጋባት ለቋንቋ እድገት እንቅፋት ነው ብቻ ሳይሆን ከቋንቋችሁ ውጪ ካለው ተናጋሪ ጋር አትገበያዩ ሲል ባሰራጨው አስነዋሪ መልእክት፣ በፓርቲው በተለይ በአማራ ብሄር ተወላጆች በጥቅሉ ደግሞ በተቀሩት ኢትዮጵያውያን ላይ በልዩ ልዩ ወቅት በሚታወጀው ጥላቻ ፣ መረራ ጉዲና በአዲስአበቤዎች ላይ በጋበዘው የእየሩሳሌምን አይነት ሽብር ወዘተ ግቡንና አካሄዱን ግልጽ ያደረገ የዘረኞችና የጨፍጫፊዎች ስብስብ ነው፡፡ ነገር ግን ለዚህ የኦፌኮም ሆነ የOMN አይነት አካላት ተደጋጋሚ የአደባባይ ላይ ወንጀሎች ህግ እንዲያስከብሩ በሚጠበቅባቸው ተቋማት የተወሰደ እርምጃ ካለመኖሩም በላይ የምርጫ ቦርድ እንኳ የፈጸሟቸውን ጥፋቶች በተገቢ መጠን ለመገሰጽ ወኔ አላገኘም፡፡
  እዚህ ላይ ትኩረት የሚሹ ሁለት አንኳር ነጥቦች አሉ፡፡
  አንደኛው ፦ ኦፌኮ አሁንም ይህንን እጅግ አደገኛ ውጤት ያለውን ፓርቲው ባደራጀው መድረክ ላይ የተነገረን ነውረኛና ዘረኛ ንግግር በማያሻሙ ቃላት አለማውገዙን ነው፡፡ ይልቅስ አቶ በቀለ ገርባ ለEthio FM በሰጠው ማብራርያ “ሀላፊነት አንወስድም፣ አናስተባብልም፣ የግለሰቦችን የመናገር መብትም እናከብራለን” ሲል ተሳልቋል፡፡
ሁለተኛ ደግሞ ፦  OMN ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው የጨነገፈ ይቅርታ ባይ መግለጫ ላይ ይህንን ነውረኛና ዘረኛ ንግግር “Strange” ሲል እጅጉን አቃልሎ መግለጹ ነው፡፡ የማይማረውና የማይጸጸተው የዚህ እኩይ ስብስብ አፈቀላጤ የሆነው ጃዋር መሀመድም OMN ይቅርታ መጠየቁ ስህተት መሆኑን ጽፏል፡፡ ሁለቱም የኦሮሞ ብሄረተኝነት የወንጀል አስፈጻሚ ተቋማት ያቺ ሴት ያደረገችውን ንግግር በዘረኝነት አልፈረጁም፣ ሊደገም የማይገባና አጥፊ መሆኑን አላመለከቱም፡፡ እንዲያውም ተቃራኒውን አቋም አራምደዋል፡፡ ይህ በአጋጣሚ የሆነ አይደለም ፡፡ የተላለፈው መልእክት ያለሙትን የሚያስፈጽምላቸው፣ የተመኙትን የሚያከናውንላቸው ነውና ነው ። ከOMNም ሆነ ከኦፌኮ ቀዳሚ ታሪክና ድርጊት እንደምንገነዘበው፣ ሰዎቹ ወደፊት ለሚያካሂዱት ዋና ጭፍጨፋ የህዝቡን ስነልቡና እያዘጋጁ፣ የሀገሩን እዝነልቡና እያለማመዱ ነውና፡፡
አስደንጋጭ ተዛምዶ ፤ ሩዋንዳዊ ድባብ !
አሁን ያለንበትን ሁናቴ ስመለከት ታድያ እያዘንኩና እየሰጋሁ በRuanda ከዘግናኙ ዋና ጭፍጨፋ በፊት የነበረውን ድባብ ለማሰብ እገደዳለሁ፡፡ ያ ፍጅት በአንዲት ሌሊት ተወልዶ አላደረም፡፡ ያ አሰቃቂ የዘር ፍጅት እውን እንዲሆን ቢያንስ 3 ዋና ዋና ሀይላት በወሳኝነት ተጣምረው ሰርተዋል፡፡
አንደኛ ፦ አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ OMN እየተጫወተ ያለውን አይነት ሚና ወስደው የተንቀሳቀሱ እንደነ RTLM ያሉ የቴሌቪዥን ጣብያዎችና ሌሎች የሬድዮ ስርጭት መርሀ ግብሮች ነበሩ፡፡ በኋላ የተከተለውን እንኳን ሊያደርጉት ሊያስቡትም የሚጨንቅ ጭፍጨፋ ተቀባይነት ወዳለው ብቻ ሳይሆን መፈጸሙ የሚያኮራ ጀብድ ወደመሆን እንዲሸጋገር የፕሮፖጋንዳ ንጣፉን የሰሩትና መመርያዎች ያስተላለፉት የOMN አቻ የሆኑት እነኚህ መገናኛ ብዙሀን ናቸው፡፡ በእነኚህ ጣብያዎች በኩልም ልክ አሁን OMN እያደረገ እንዳለው ብዙ ሆነን ሳለ ተጨቆንን የሚልን ትርክት አለማቋረጥ በማስተጋባት፣ ሁቱ ባልሆኑትና በአመለካከት በተለዩ ሁቱዎች ላይ ሰው መሆናቸውን የሚገፍፍ Dehumanizing ፕሮፖጋንዳ በመንዛት የጅምላ እርድ የደገሱባቸው እነኚህ ጽልመታውያንና ኩርማናውያን ናቸው፡፡ ብቻቸውን ግን አልነበሩም፡፡
 ሁለተኛ ፦ የጊዜው የRuanda ገዢ ፓርቲ የወጣቶች ክንፍና የተባለውን ሁሉ የሚተገብር አእምሮ ድፍን መንጋ Interahamwe በተልእኮ ፈጻሚነትና በፍጹም ቅንጅት ፍጅቱ እንዲከሰት አስፈላጊውን ሁሉ አድርጓል፡፡ ለእነኝያ Hutu power ለእነኚህ ደግሞ QeErrOO Power የመሰባሰብያና የመጨፍጨፍያ ሀረጋቸው መሆኑን ልብ ይሉአል፡፡ ኦፌኮ ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ ይህንን የፊታውራሪነት ሚና መውሰዱን በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡ ታድያ ይህ የፍጅት እቅድ በተሟላ ሁናቴ እንዲፈጸም ሶስተኛ ቁልፍ ተዋናይም ነበረ፡፡ በJuvenal Habyarimana የሚመራ፣ ፍትህ የማያውቅ፣ ባለጣምራ ሚዛን፣ ህግ የማስከበር ግዴታውን ያልተወጣ ብቻ ሳይሆን የታቀደው እንዲፈጸም ምቹ ሁኔታ የፈጠረ፣ የእነዚህ ሁለት ቡድኖች የርዕዮትም ሆነ የግብ ተጋሪ መንግስት ነበራት Ruanda፡፡ እዚህ ላይ፣ የሽመልስ አብዲሳን የ“ሰብረናቸዋል” ቀረርቶ፣ “እኛ ዝሆን ነን፣ እንገዛለን፣ እንበላለን፣ እንሰብራለን” ይሉትን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ያስታውሱአል፡፡
እንግዲህ ልብ በሉ ፤  እነኚህን አስቀድሜ የጠቀስኳቸውን በRuanda የዘር ጭፍጨፋው እንዲከሰት ያደረጉትን ተቀናጅ ቡድኖች ሁሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ብንፈልጋቸው እምብዛም ሳንለፋ በፖለቲካውም ሆነ በመገናኛ ብዙሀኑ ምህዳር ላይ ፊት ለፊት ተሰይመው እናገኛቸዋለን፡፡
ምን እናድርግ?
  አዎ ያሳስባል፤ ሊያምኑት ይቸግራል፤ ነገር ግን እውነቱን ተጋፍጦ በጊዜ መፍትሄ ማፍለቅ ያሻል፡፡ በኢትዮጵያችን ውስጥ ሩዋንዳን መቀመቅ ያወረዳት ጭፍጨፋ እንዲከሰት ያስቻሉ ሁሉም መሰል ቡድኖች ተሟልተዋል፡፡ ጨፍጭፉ የሚል ቴሌቪዥን ጣብያ፣ አትጋቡ አትገበያዩ የሚል የፖለቲካ ፓርቲ፣ ማናቸውንም አረመኔያዊ ተግባራት ሊፈጽም ፍላጎቱንና ዝግጁነቱን ደጋግሞ ያሳየ መንጋ፣ ይህንን በቸልታ የሚያይና ዜጎቹን የማይከላከል መንግስት ቦታ ቦታቸውን ይዘዋል፡፡ ምስስሎሹ ያስደነግጣል፡፡ ተዛምዶው በእጅጉ ያሰጋል፡፡ እነኚህን የእልቂትና የጨለማ ሀይላት በቁርጠኝነት ለመፋለምም በኢትዮጵያዊ ማንነትና ኢትዮጵያዊ ብሄረተኝነት ብርሃናማና አቃፊ አጀንዳ ዙርያ አሁንና ዛሬ መሰባሰብ ለነገ ቀርቶ ለበኋላ የሚሸጋገር አይደለም፡፡ ይህንን ግልጽ ወንጀል ከፈጸመ በኋላ OMNን የማይዘጋ አገዛዝ ጥርጥር በሌለው ሁኔታ የመልእክቱም የውጤቱም ተጋሪ ነው፡፡ መንግስት ተብሎ ሊጠራ የሚያበቃ ክብር፣ ቅቡልነትም ሆነ የሞራል ብቃት ሊኖረው አይችልም፡፡
ወገን፤ የምናንቀላፋበት ጊዜ አልሆነም፡፡
Filed in: Amharic