>
5:13 pm - Tuesday April 19, 8783

ባልደራስ የአዲስ አድማስ ጋዜጣ አሳታሚን እንደሚከስ አስታወቀ !!! (ኢትዮጲስ)

ባልደራስ የአዲስ አድማስ ጋዜጣ አሳታሚን እንደሚከስ አስታወቀ !!!

ኢትዮጲስ
 እስክንድርነጋ …… << በአዲስ አድማስ ጋዜጣ፣ ባልደራስን ጨምሮ 13 ድርጅቶች ምክክር ይዘዋል የተባለው ነጭ ውሸት ነው። ባልደራስ ከጨፍጫፊዎች ጋር አይደራደርም።  ጨፍጫፊዎች ሆይ፦ ህግ ፊት እንድትቀርቡ እንታገላለን። ቃላችን ነው‼>> በጉዳዩ ለሁሉም ግልፅ ይሁን፦
አንዱ ዘላቂ ድርጅታዊ አቋማችን ይኸው ብቻ ነው‼
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ
አዲስ አድማስ ጋዜጣ በዛሬ የካቲት 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ዕትሙ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ)፣የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ጥምረት ሊመሰርቱ እንደሆነ ዘግቧል። ይሁን እንጂ ዘገባው ነጭ ውሸት ነው ሲል ባልደራስ አስታውቋል። የአብን ከፍተኛ አመራሮችም ጉዳዩ ሀሰት መሆኑን ገልፀዋል።
በመሆኑም ጋዜጣው በፍጥነት ስህተቱን የማያርምና ይቅርታ የማይጠይቅ ከሆነ ባልደራስ የአዲስ አድማስ አሳታሚ ላይ ሕጋው ክስ እንደሚመሰርት አስጠንቅቋል።
“ባልደራስ ከሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር እየፈጠረ ያለው መቀናጀት እና በሀገሪቱ ፖለቲካ ላይ ይዞት የመጣው አዲስ የኃይል አሰላለፍ ያስደነገጣቸው ቡድኖች በሕዝቡ ላይ ብዥታ ለመፍጠር ያስወሩት ነጭ ውሸት ነው” ሲል ባልደራስ አብራርቷል።
“ባልደራስ ሕዝብን ካስጨፈጨፉ ኃይሎች ጋር በህግ ፊት እንጂ በጠረጴዛ ዙርያ ለምምክክር አይቀመጥም” በማለትም ከኦነግና ከኦፌኮ ጋር ሊቀናጅ እንደማይፈልግ አስታውቋል።
አዲስ አድማስ ዛሬ ማለዳውን ጉዳዩን በጋዜጣ አትሞ ያስነበበ ሲሆን ከቀትር በኋላ ደግሞ ቅሬታውን አጢኖ ከማስተባበል ይልቅ በገጸ ድሩ ዘገባውን በድጋሜ አስነብቧል።
Filed in: Amharic