>

አዲስ አበባ ውስጥ ጀሞ ሁለት አካባቢ እንዲህ ሆነላችሁ! (ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)

አዲስ አበባ ውስጥ ጀሞ ሁለት አካባቢ እንዲህ ሆነላችሁ!

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ሰላም ባይኖርም ሰላም ልበላችሁ ውድ አንባቢያን፡፡

ነገሩ የተፈጸመው ቅዳሜ የካቲት 21 ቀን 2012ዓ.ም ነው፡፡ ጀሞ ሁለት በሚባለው አካባቢ  አንዲት አነስተኛ ቡና ቤት ውስጥ የተከሰተ አስፀያፊ ድርጊት ነው፡፡ ባለቡና ቤቷ ለስምንት ዓመታት በሥራ ፍለጋ ያለ ሥራ ስትንከራተት ቆይታ አክስት አጎቶቿ ተባብረው አንዲት ቡና ቤት ይከፍቱላታል፡፡ በዚያ መተዳደር ከጀመረች ጥቂት ወራት አለፉ፡፡

ባፈው ቅዳሜ እንዲህ ሆነ፡፡ የሠፈር ሰዎች በቡና ቤቷ ደጃፍ ላይ ቁጭ ብለው ይዝናናሉ፡፡ የሚናገሩት በአማርኛ ነው፡፡ በአጋጣሚ ደግሞ የተከፈተው ዘፈን ተራው ሆኖ አማርኛ ነው፤ ቡና ቤቶች ዘፈን እያፈራረቁ ነው የሚያዘፍኑት – በባለጊዜ ተረኞች ካልተገደዱ በስተቀር፡፡ ያኔ ያካባቢው ቄሮዎች ይሰባሰቡና “ሆ!” እያሉ መጥተው “ናፍጠኞታ! ናፍጠኞታ!” በማለት ቡና ቤቱን በድንጋይ ሩምታ ያደበላልቁታል፡፡ እንዲህ ያደረጉት ሴትዮዋ አማራ መስላቸው ነው፡፡ እርሷ ግን በጊዜው አነጋገር ትግሬ ናት፡፡ በትግሬነቷ ግን አልተጠቀመችም እንደመረጃ ምንጬ፡፡

ዕብዶቹ በድንጋይ ቡና ቤቱን ማተረማመስ እንደጀመሩ ሴትዮዋ ደምበኞቿን ገፋፍታ በጓሮ በር አስወጣችና የሚሆነውን ለማየት ቤቷ ውስጥ በድንገጤ ፈዝዛ ቁጭ አለች፡፡ እነዚያ ቄሮዎች በኦሮምኛ አማራን እየተሳደቡና እየተራገሙ ፍሪጁን፣ በርና መስኮቶችን፣ በቤት ውስጥና በግቢው ውስጥ ያለውን ዕቃ በሙሉ ሰባብረውና የዘረፉትንም ዘርፈው ወደመጡበት ተመለሱ፡፡ አንድም ገላጋይ አልነበረም፡፡ ሁሉም ለባለጊዜዎቹ ያጎበደደ ነውና፡፡

ሴትዮዋ ህግ ያለ መስሏት ልታመለክት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄደች፡፡ እንደሄደች ላገኘችው ፖሊስ የደረሰባትን ግፍና በደል ስትነግረው በነገር ጥልልፍ ትግሬ መሆኗን ያወቀው ፖሊስ በተሰባበረ አማርኛ  “አንቺ ወያኔ ነሽ ኢንዴ… ነፍጠኛ አይደላሽ ኢንዴ… ነፍጣኛ ናትኮ ነው ያሉት ልጆቹ፡፡ ላናጋሩ ሁለታቹም አንዲ ናቹ…ምንም ሊናራግ አኒችልም…” በማለት አሹፎባትና ስቆባት አመናቅሮ እንደመለሳት የመረጃየ ምንጭ በምሬት ገልጾልኛል፡፡ ይህ መረጃ በነገራችን ላይ የአካባቢው የቡና ማጣጫ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ አክራሪ ኦሮሞ ሀገራችንን እንዴት እየተጫወተባት እንደሆነ ከዚህ መረዳት ይቻላል፡፡ ከሚዘገበው ደግሞ የማይዘገበው እጅግ የበለጠ ነው፡፡

ይህች ናት ኢትዮጵያ፡፡ ነገሮች በብርሃን ፍጥነት እየተበለሻሹ ነው፡፡ የትናንትናው የነመረራ የትዳር አፍርሱ ጉዳይ ደግሞ እጅግ የሚገርም ነው፡፡ “አማራን ፈትታችሁ እኔን አግቡኝ” የምትል ጉድ እንደተፈጠረች በግልጽ እያየናት ነው፡፡ ይህ ሀፍረት የሚሉት ነገር በሀገር ጠፍቷል፡፡ 

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡

Filed in: Amharic